TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EMA

የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለሚዲያዎች የሰጡት ቃለምልልስ ከምርጫ በፊት እንዳይሰራጭ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ።

ቃለምልልሱ በዚህ በጥሞና ወቅት መተላለፍ የለበትም ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፥ ምንም እንኳን ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች ላይ ያተኮረና የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልሆነ ቢታወቅም በዚህ ጥሞና ወቅት ሊተላለፍ አይገባም ብለዋል።

የቃለ መጠይቁ መተላለፍ ብዥታ እንዳይፈጥር ሲባል ከምርጫው በፊት መተላለፍ እንደሌለበት አቶ መሀመድ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ቃለ መጠይቁ እንዳይተላለፍ የተፈለገው መንግስት በዚህ ዓመት የተሻለ ምርጫ እንዲካሄድና ፍትሀዊ እንዲሆን ፍላጎት ስላለው መሆኑን ተናግረዋል።

ስለዚህ ቃለ መጠይቁን ለማስተላለፍ ማስታወቂያ እየሰሩ ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ለማስተላለፍ የተዘጋጁ ከወዲሁ #እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

በተመሳሳይ የማሕበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስሉ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ያሉ አካላትም ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው ብለዋል።

መገናኛ ብዙሃንም ቢሆኑ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በመጠናቀቁ ቅስቀሳ መሰል ዘገባዎችን ከማስተላለፍ ሊጠነቀቁ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ይገልፃል።

@tikvahethiopia