#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,725
• በበሽታው የተያዙ - 355
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 989
በአጠቃላይ በሀገራችን 98,746 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,512 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 58,103 ከበሽታው አገግመዋል።
332 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

"ጥቃቱ ሲቪሎችን ታርጌት ያደረገ አይደለም" - ዶ/ር አብይ አህመድ
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በትግራይ ክልል በተፈፀመው የአየር ጥቃት ራዳሮች ፣ ሮኬቶች ፣ ሚሳኤሎች ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ መደረጉን ተናገሩ።
"ጥቃቱ ሲቪሎችን ታርጌት ያደረገ አይደለም" ሲሉ ገልፀዋል።
ሚሳኤሎች፣ ራዳሮች፣ የሮኬቶች ቦታዎች በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ተገዙ፤በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ይጠበቁ የነበሩ ናቸው ብለዋል።
ትጥቆቹ የትና ምን አካባቢ እንዳሉ በዝርዝር ሙሉ እውቀት አለን ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የአየር ኃይሉ ከዚህ ቀደም በነበረ መንገድ ብቻ ሳይሆን በቀንም በማታም ሊያጠቁ የሚችሉ እና በሰው የማይነዱ ዘመናዊ መሳሪዎችን ስለታጠቀ ሲቪሎች ላይ ጉዳት ሳያጋጥም ተፈላጊ ቦታ ላይ ጥቃት መፈፀም ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

'የአየር ኃይል ጥቃት'
በመቐለ ፣ ዓዲግራት ፣ ሽረ ፣ አክሱም አካባቢ ያሉ የከተማ ነዋሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።
በማንኛውም ሰዓት ላይ "የአየር ጥቃት" ሊፈፀም ስለሚችል ነዋሪዎች በኤርፖርቶች፣ የትጥቅ ዴፖዎች፣ የነዳጅ ዴፖዎች አካባቢ እንዳይቀርቡ አስጠንቅቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም "ቆቦ" አካባቢ የተከማቹ መድፎች እና ታንኮች እንዳሉ ገልፀው ከፍተኛ መሳሪያ የተከማቸባቸው ቦታዎች በቀንም ሆነ በማታም ጥቃት ይፈፀምባቸዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በአካባቢው ያለ ህዝብ እንዲሁም ሚሊሻ እራሱን እንዲያርቅ አሳስበዋል።

"የሰላም ጥሪ"
የዓለም አቀፍ የሰላም እና የልማት ማዕከል (PDCI) በትግራይ ክልል ውስጥ በተከሰተው ግጭት የተፈጠረውን ውጥረት ሁሉም ወገኖች እንዲያበርዱ አጥብቆ ጠይቋል።
በአፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
* PDCI በአማርኛ ፣ በትግርኛና በእንግሊዘኛ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል። (SBS)

#NewsAlert
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግስት ትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባ እና ጊዜያዊ መንግስት (አስተዳደር) እንዲቋቋም ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ ፀደቀ፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬው እለት አስቸኳይ ስብሰባውን አካሄዷል፡፡
በስብሰባው በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ👆
ጊዜያዊ አስተዳደር ለክልሉ ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚ አካል የተሰጡትን ተግባሮች እንደሚኖሩት ተገልጿል።
በተለይም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፦
ሀ) አስፈፃሚ አካሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፤
ለ) የጊዜያዊ አስተዳደሩን ኃላፊዎች ይመድባል፤
ሐ) ሕግና ሥርዓት መከበሩን ያረጋግጣል፤
መ) አግባብ ባለው ህግ መሰረት በክልሉ ምርጫ የሚከናወንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
ሠ) የክልሉን እቅድና በጀት ያፀድቃል፤
ረ) በፌዴራል መንግስቱ ሚሰጡ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ተብሏል።
የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት
ጥቅምት 28/2013 ዓ/ም

ሰላም የሚወርደው መቼ ነው ?
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠ/ሚ አብይ አህመድ ምላሽ ፦
"...ይህ ግጭት የሚቆመው ህግን ስናስከብር ብቻ ነው።
የትግራይ ህዝብ ፣ የትግራይ ልዩ ኃይል እና የትግራይ ሚሊሻ መገንዘብ ያለበት ጥፍር የነቀሉ፣ ሰው የገደሉ፣ ሀብት የዘረፉ ወንጀለኞች ተለቅመው ወደ ህግ ሲቀርቡ በዛው ሰዓት ሁሉም ነገር ያበቃል፤ ይቆማል።
ይህ ፀብ ከጥቂት ስግብግብ ጁንታዎች ጋር እንጂ ከማንም ጋር ባለመሆኑ ሙሉ ግጭቱ እና ሁኔታው የሚቆመው እነዚህ ኃይሎች ለህግ ሲቀርቡ እና ህግ በሁላችንም ላይ የሚሰራ መሆኑን ስናረጋግጥ ነው።"
* ከዚህ በተጨማሪ እርቅ፣ ሰላም፣ ውይይት የሚለውን ሀሳብ ስለሚያነሱ አካላትን በተመለከተም ሀሳቡን እንደማይቀበሉት አረጋግጠዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ስለሰላም ፣ ለፍቅር ፣ ስለአንድነት ፣ ስለአብሮነት ያደረግናቸው ሙከራዎች ሁሉ እንደድካም እና እንዳለመቻል ነው የተቆጠሩት ብለዋል። "ደከም ሲል እርቅ ፤ ጠንከር ሲል ገዳይ ከሆነ ኃይል ጋር በሁለት መለዮ መጫወት አይቻልም" ሲሉ ተደምጠዋል።

#EthiopianAirlines
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት እጅግ ዘመናዊ የኤርባስ ኤ 350 አውሮፕላኖችን መረከቡን አሳውቋል።
ይህንን በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ያስተላለፉት መልዕክት ከላይ ተያይዟል።
በነገራች ላይ አየር መንገዱ ከኤር ባስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር አዳዲሶቹ አውሮፕላኖች ጭኖ ያመጣውን የእርዳታ እቃዎች ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው እለት መለገሱንም አሳውቋል።

#BREAKING
CNN ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።
ባይደን በፔንሲልቬኒያ ግዛት ማሸነፋቸው ተገልጿል።

#JoeBiden
የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፥ ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው "የእንኳን ደስ አሎት" መልዕክት በትዊተር ገፃቸው አስተላልፈዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፥ ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው "የእንኳን ደስ አሎት" መልዕክት በትዊተር ገፃቸው አስተላልፈዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KamalaHarris
ካማላ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
እንዲሁም ጥቁር እና እሲያ አሜሪካዊ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ታሪክ ሰርተዋል።
ካማላ ሃሪስ ከሕንድ ከሆኑት እናታቸው እና ከጀማይካ ከሆኑት አባታቸው በካሊፎርኒያ ነበር የተወለዱት።
የ55 ዓመቷ ካማላ ሃሪስ ከጆ ባይደን ጋር በመሆን አሜሪካንን ለመጪዎቹ 4 ዓመታት ይመራሉ። [BBC]
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ካማላ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
እንዲሁም ጥቁር እና እሲያ አሜሪካዊ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ታሪክ ሰርተዋል።
ካማላ ሃሪስ ከሕንድ ከሆኑት እናታቸው እና ከጀማይካ ከሆኑት አባታቸው በካሊፎርኒያ ነበር የተወለዱት።
የ55 ዓመቷ ካማላ ሃሪስ ከጆ ባይደን ጋር በመሆን አሜሪካንን ለመጪዎቹ 4 ዓመታት ይመራሉ። [BBC]
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia
የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,028
• በበሽታው የተያዙ - 455
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 845
በአጠቃላይ በሀገራችን 99,201 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,518 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 58,948 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
306 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,028
• በበሽታው የተያዙ - 455
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 845
በአጠቃላይ በሀገራችን 99,201 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,518 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 58,948 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
306 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_ዜና ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ተሸነፉ። ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነ ተመርጠዋል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ጆ ባይደን ማናቸው?
ጆ ባይደን የቀድሞ የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል።
የባይደን ደጋፊዎቻቸው የውጪ ጉዳይ ፖሊስ አዋቂ ናቸው ይሏቸዋል።
ጆ ባይደን የፖለቲካ ሕይወታቸው የጀመረው ከ47 ዓመታት በፊት ነበር።
ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን ጥረት ማድረግ የጀመሩት ደግሞ ከ33 ዓመታት በፊት እ.አ.አ. 1987 ጀምሮ ነው።
በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት አላቸው።
* የጆ ባይደን ውጭ ፖሊሲ ጉዳይ ፦
ባይደን ዶናልድ ትራምፕ ያበላሹትን የውጭ ግንኙነት አስተካክላለሁ ፤ አሜሪካ ያስቀየመቻቸውን ወዳጆቿን ልብ እጠግናለሁ ብለዋል።
ከኢራን እና ከቻይና ጋር የሚከተሉት ፖሊሲም ትራምፕ ጋር የሚቃረን ነው።
ይህ መረጃ ከBBC የተወሰደ ነው።

#BidenHarris2020
ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አሕመድ ለጆ ባይደን እና ካማላ ሃሪስ 'የእንኳን ደስ አላችሁ' መልዕክት በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ አስተላልፈዋል።
"ኢትዮጵያ በቅርበት አብራችሁ ለመስራት በመጠባበቅ ላይ ናት" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አሕመድ ለጆ ባይደን እና ካማላ ሃሪስ 'የእንኳን ደስ አላችሁ' መልዕክት በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ አስተላልፈዋል።
"ኢትዮጵያ በቅርበት አብራችሁ ለመስራት በመጠባበቅ ላይ ናት" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ መከላከያ ሰራዊቱ ፦
- ዳንሻን
- ባከርን
- ከሽራሮ አስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው ብለዋል።
መከላከያ "በከሀዲ ቡድኑ" እጅ ያሉ ከባድ መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ አውድሟልም ብለዋል።
ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ፥ "የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብ እንዳይጎዳ ለማድረግ እና ጽንፈኛውን ኃይል ከህዝብ ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ ነው" ብለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጀ መሀመድ ተሰማ፥ ሰራዊቱ ሀገርን ከጥፋት የማዳን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ያጠናቅቃል አሉ።
የኢትዮጵያን ዕድገት ማይፈልጉ ታሪካዊ የሆኑ ጠላቶች የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንዳያደናቅፉ የሀገሪቱ የፀጥታ ሀይሎች በተጠንቀቅ በቆሙበት ባሁኑ ሰዓት ላይ የናት ጡት ነካሾች ሀገሪቱን በመድፈር ውጊያ ከፍተውብናል ብለዋል።
ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ፥ "ይህ ጦርነት ሀገርን ለውጭ አሳልፎ የሚሰጥና ፅንፈኛው ሀይል የስልጣን ጥማቱን ለማርካት የገባበት ነው" ሲሉ ተናገራዋል።
በአሁን ሰዓት ይህን ውጊያ ለመመከት መላው የፀጥታ ኃይሎች እየተዋጉ ወንጀለኞችን ወደ ህግ ለማቅረብ ፍልሚያ ላይ ይገኛሉ ሲሉ አስረድተዋል።
ዳይሬክተሩ ሜ/ጄ መሀመድ ፥ "ሠራዊቱ ፅንፈኛውን ሀይል በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር በማዋልና ለህግ በማቅረብ የአካባቢው ሕዝብ ከነበረበት ጭቆና ነፃ እንደሚወጣ እናረጋግጣለን" ብለዋል።