በመቐለ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል መመለሱን ሰምተናል።
መብራት የመጣው ዛሬ ምሽት ነው።
PHOTO : ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
መብራት የመጣው ዛሬ ምሽት ነው።
PHOTO : ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ምሽቱን የመቐለ ከተማ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።
በከተማይቱም መደበኛ እንቅስቃሴ ነው ያለው።
የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይልም ተመልሷል።
እንዚህን ፎቶ ያጋራው ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በከተማይቱም መደበኛ እንቅስቃሴ ነው ያለው።
የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይልም ተመልሷል።
እንዚህን ፎቶ ያጋራው ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የሰሜን ኢትዮጵያ አየር ክልል ተዘግቷል"
ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የአለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት የተዘጉ መሆናቸው ተገልጿል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የአየር ክልል ለማንኛውም በረራ የተዘጋ ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ይህንን ተላልፎ በረራ የሚፈጽም ማንኛውም አውሮፕላን እንዳይኖር ን አሳስቧል።

#UPDATE
ከዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጥዋት 2 ሰዓት ጀምሮ የመቐለ፣ ሽሬ ፣ አክሱም እና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን ተገለፀ።
ይህን የገለፀው የኢትዮጵያ ሲቨል አቪዬሽን ባለስልጣን ነው።
በተመሳሳይ ሁሉም የሚመለከታቸው አካሎች (ኤርሜንስ) በተገቢው የመገናኛ ዘዴ በ (ኖታም) አንዲያውቁት መደረጉን አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ከዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጥዋት 2 ሰዓት ጀምሮ የመቐለ፣ ሽሬ ፣ አክሱም እና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን ተገለፀ።
ይህን የገለፀው የኢትዮጵያ ሲቨል አቪዬሽን ባለስልጣን ነው።
በተመሳሳይ ሁሉም የሚመለከታቸው አካሎች (ኤርሜንስ) በተገቢው የመገናኛ ዘዴ በ (ኖታም) አንዲያውቁት መደረጉን አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE
የ2013 የትምህርት ዘመን ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይጀመር የነበረው "የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት" ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
ምክንያት ?
በኮቪድ-19 የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ እቅድ ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አስፈላጊ ዝግጅቶች በተሟላ ደረጃ እስኪጠናቀቁ ድረስ ነው።
ነገር ግን ለክልላዊ እና ለብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የክለሳ ትምህርት ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
Via Addis Ababa Press Secretary

ዛሬ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ ሰጥቷል።
ፌዴራል ፖሊስ በትግራይ ክልል በሚጠብቀው 22 ተቋማት ላይ ህወሓት ጥቃት እንደፈፀመበት ገልጿል።
የተቋማት ጠባቂዎችን ከማጥቃት ጀምሮ ዝርፊያ መፈፀሙን አሳውቋል።
ጥቃት የተፈፀመባቸው የፌዴራል ፖሊስ አባላት አሁን ላይ ከሰሜን ዕዝ ጋር ሆነው የህግ ማስከበር ስራ እየሰሩ ናቸው ብሏል።
የፖሊስ አባላቱ ከተፈፀመው ጥቃት እንዲያመልጡ የትግራይ ክልል ህዝብ ከለላ ከመስጠት ጀምሮ ጥበቃ ሲያደርግላቸው ነበር።
ከዚህም በተጨማሪ "ህወሓት" በተለያዩ በትልልቅ ከተሞች በተለይ ዋና ዋና ከተሞች "የሽብር ጥቃት" ሊፈፅም የሚችል ኃይል ማሰማራቱን አረጋግጠናል ብሏል።
ከፊሎቹ ተይዘዋል ፤ ከፊሎች ደግሞ እየታደኑ ይገኛሉ ሲል ፖሊስ ገልጿል።

'በትግራይ ክልል የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ'
አዋጁን የሚያስፈፅሙ ግብረ ኃይል እንዲንቀሳቀሱ እውቅና ከሚሰጣቸው ሰዎች እና ተሽከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ሰው ወይም ተሽከርካሪ መመሪያው ተፈፃሚ በሚሆንበት ቦታ ሁሉ ከምሽት 2 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት መንቀሳቀስ አፈቀድለትም።
ከግብረ ኃይሉ ፍቃድ ውጭ ማንኛውም ሰልፍ ፣ በአደባባይ ወይም በቤት ውስጥ ስብሰባ ማድረግ እንዲሁም 4 እና ከዛ በላይ ሆኖ በቡድን መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ተብሏል።
ከመከላከያ ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ሌሎች ፍቃድ ከተሰጣቸው የፀጥታ አካላት ውጪ ማኛውም የጦር መሳሪያ ሆነ ጉዳት የሚያደርሱ የተለያዩ እቃዎችን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

የነዳጅ ምርቶች ላይ የግብይት ሠዓት ገደብ ተጣለ!
የነዳጅ ምርቶች ዝውውር፣ ስርጭት እና ግብይትን በጥብቅ ለመከታተል እና ለመቆጣጠር እንዲቻል የግብይት ሠዓት ገደብ መጣሉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አስታወቀ።
በዚህም፦
በሁሉም በአዲስ አበባ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከዛሬ 27/02/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ፤
በሁሉም የክልሎች የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ብቻ እንዲሠሩ የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል።

#Tigray
ከመቐለ ከተማ ወደ ሌሎች የትግራይ ክልል ከተሞች እና አካባቢዎች የትራንፖርት እንቅስቃሴ ዛሬ ጀምሯል።
ትራንስፖርት ቢጀመርም ከመቐለ ከተማ ወደ ትግራይ የተለያዩ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በመሉ ከከተማው ፖሊስ ልዩ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።
የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት አሁንም እንደተቋረጠ ነው።
ፎቶውን ያጋራው ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ ነው።

#መቐለ
ትላንት በመቐለ ከተማ የጦር አውሮፕላን ሲያንዣብብ ነበር በዚህ በርካቶች መደናገጥ እና ፍራቻ ውስጥ ገብተው ነበር።
በዛሬው ዕለት ነዋሪው ወደ የእለት ተእለት ኑሮው ተመልሷል።
በከተማዋ ውስጥ ያሉ ባንኮች ዝግ ሲሆኑ ነዋሪው ከትናንት በተሻለ ሁኔታ ከተማዋ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
በተጨማሪ መቀሌ የሚገኙ የንግድ ተቋማትና የገበያ ማዕከላት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በአሁኑ ወቅት ወቅት በከተማዋ አንዳንድ የነዳጅ ማደያ ጣብያዎች አገልግሎት እየሰጡ ቢሆንም በከተማዋ የቤንዚን እጥረት አለ።
መቐለ ከተማ በአንፃራዊ ሁኔታ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ብትገኝም ማህበረሰቡ ጦርነቱ በፈጠረው ውጅንብር ስጋት ላይ ነው።
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንዲወስዱ የሚጠብቁ ተማሪዎች በአፄ ዮሃንስ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ቀጥለዋል።
ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት በትምህርት ገበታቸው ላይ የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ግን ትምህርታቸው ተዋርጧል።
በቅርቡ ተመራቂ ተማሪዎቹን የተቀበለው የመቐለ ዩኒቨርስቲ ለተማሪዎቹ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ይህን መረጃ ያካፈለው በመቐለ የሚገኘው #የቢቢሲ ጋዜጠኛ ነው።

#DrAbiyAhmed
ጠ/ሚ ዶክተር አቢይ አህመድ ፥ "ኢትዮጵያ ለወንጀለኛ አካላት ቦታ የላትም" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው የትግራይ ሕዝብ ሆነ ማንኛውም ዜጋ የወንጀለኞች መሸሸጊያ አይሆንም ብለዋል፡፡ አንቀጽ 51 በመጥቀስ የፌደራል መንግስቱ ህገመንግስቱን ያስከብራል ብለዋል።
እንዲሁም መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት በፈጸመው ቡድን ላይ የህግ የበላይነትን ለማስከበር እርምጃዎችን ይወስዳል ብለዋል፡፡
ወንጀል የፈጸሙ አካላትን ከተሸሸጉበት በማስወጣት መላው የሃገሪቱ ህዝብ ዘላቂ ወደሆነ ብልጽግና ጎዳና እንመራለን ብለዋል። (ኤፍቢሲ)

#JoeBiden
ጆ ባይደን ከ270 በላይ ድምፅ አግኝተው 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለመሆን እየተቃረቡ ነው።
ባይደን ቁልፍ በተባሉ ግዛቶች እየመሩ ይገኛሉ። (SBS)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጆ ባይደን ከ270 በላይ ድምፅ አግኝተው 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለመሆን እየተቃረቡ ነው።
ባይደን ቁልፍ በተባሉ ግዛቶች እየመሩ ይገኛሉ። (SBS)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BidenHarris
"... ቆጠራው ሲጠናቀቅ እኔ እና ካማላ ሀሪስ (ምክትላቸው) አሸናፊነታችን ይፋ እንደሚደረግ አልጠራጠርም" - ጆ ባይደን
* ከሰዓታት በፊት የተናገሩት (AlAIN)

TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ትግራይ ቴሌቪዥን በ "ሰበር ዜና" የፌዴራል መንግስቱ አውሮፕላኖች መቐለ አካባቢ ድብደባ እንዳካሄዱ ገልጿል። የትግራይ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን፥ "ድርጊቱ ህዝቡን ለማንበርከክ ነው፣ ህዝቡ ግን በዚህ አይንበረከክም ፤ ትግሉን ይቀጥላል" ሲል ገልጿል። የደረሰው ጥቃት ምን እንደሆነ እና ቦታው አልተገለፀም። ከፌዴራል መንግስት በኩል እስካሁን ስለዚህ ጉዳይ የተሰጠ…
#UPDATE
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የህወሓት ኃይል ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት ተጠናቋል ሲሉ በኢቲቪ ላይ ቀርበው ተናገሩ።
የአየር ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በተለያዩ ስፍራዎች የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማውደም መቻሉን ገልፀዋል።
እነዚህ ሮኬቶች እስከ 300 ኪሎ ሜትሮች ድረስ መወንጨፍ የሚችሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሮኬቶቹን 'ወንጀለኛው ቡድን' የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ በመቐለ ከተማና አካባቢዋ በነበረው የከባድ መሳሪያ ማስቀመጫ ላይ የአየር ኃይሉ እርምጃ እንዲወስድ ተደርጓል ሲሉ አሳውቀዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግርኛ መግለጫ ፦
ጠ/ሚ ዶክተር ዐብይ አህመድ መንግሥት በትግራይ ክልል ላይ እየወሰደ ባለው እርምጃ የአየር ጥቃቶች ሊኖሩ ይችላሉ ብለዋል።
የአየር ጥቃቱ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ እንዳልሆነ እና "አደገኛ" ብለው የጠሩትን ኃይል የያዛቸውን ቦታዎች ኢላማ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
"በዚህ ሁኔታ ያልታሰበ አደጋ እንዳይመጣ ነዋሪዎች በከተማ አካባቢ ተሰብስባችሁ መንቀሳቀስ እንድትቀንሱ አሳስባለሁ" ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዶ/ር አብይ መንግሥታቸው በህወሃት ላይ የከፈተውን ጦርነት ህገ መንግሥቱን የማስከበር ሂደት ነው ካሉ በኋላ "ተገደን የገባንበት ጦርነት ነው" ብለዋል።
ዶ/ር አብይ ፥ "የተከበርከው ህዝብ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ተኝቶ እያለ አጥቅተዋል። ዓለም እያለ ጥቃት ፈፅመዋል" ሲሉ ተናገረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ "ሁሉም ህወሓት አይደለም ጠላታችን ፤ በህወሓት ውስጥ ያለ ሃይል ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። (BBC)