#GULISO
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ከተማ 02 ቀበሌ ባለፈው ሳምንት አርብ/በደመራው ዕለት/ አንድ የመከላከያ አባል ሁለት ሰዎችን ገደለ፤ አንድ አቆሰለ ሲሉ የተጎጂ ቤተሰቦች ተናግረዋል። ድርጊቱ መፈፀሙን ያመኑት የዞኑ የፀጥታ እና የአስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ገልፀዋል፤ አድገላጊው የህግ እርምጃም ይወሰዳል ብለዋል። የግለሰቡ ድርጊት የመከላከያ ሰራዊቱን የሚወክል አይደለም ሲሉ የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አብዩ ምህረቱ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#Guliso
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፥ "የጸጥታ አካላት ትላንት ጥቃት ወደተፈጸመበት አካባቢ ተሰማርተዋል ፤ እርምጃም እየወሰዱ ነው" ብለዋል።
በቀጣይም መንግስት የሕዝቡን ደኅንነት የመንግሥትነቱን ሥራ ይሠራል ሲሉ ገልፃዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ፥ "ሕዝቡ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የጸጥታ አካላት፣ ምሁራንና ሌሎችም መንግሥት ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ የሚወስደውን ርምጃ በመደገፍ የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ" ብለዋል።
በሌላ በኩል ፦
ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በንፁሃን ላይ #ማንነትን መሰረት እያደረገ በሚፈፀመው ተደጋጋሚ ጥቃት ሀዘናቸውን እና ቁጣቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ መንግስት በየጊዜው ንፁሃን ሞት በኃላ መግለጫ ከማውጣትና አዘንኩ ከማለት በቅድሚያ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ እንዳለበት በጥብቅ እያሳሳቡ ይገኛሉ።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia