TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AmharaProsperityParty

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ትላንት ምሽት በጉሊሶ ወረዳ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት መፈፁሙን አረጋግጫለሁ ብሏል።

የጥቃቱን መጠን እና ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፌዴራል እና ክልል መንግስት ጋር በመሆን እያጣራ እንደሆነ አሳውቋል።

ፓርቲው ፥ "በተፈፀመው ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት የአማራ ህዝብና ድርጅታችን የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ክፉኛ አዝኗል፣ ተቆጥቷል" ሲል በመገለጫው ገልጿል።

ሙሉ የመግለጫውን ሀሳብ ከላይ አንብቡ !

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ተጨማሪ ፦

የጉሊሶ ወረዳ ነዋሪዎች ለ "አብመድ" እንደተናገሩት ፥ የጅምላ ጥቃቱን የፈፀመብን ኦነግ ሸኔ የተባለ የታጠቀ ቡድን ነው ብለዋል፡፡

ጥቃቱ በአንድ አካባቢ በሚኖሩ "አማራዎች" ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የታጠቀው ቡድን ትናንት ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ 200 አባዎራዎች እና ሌሎች ነዋሪዎችን ከሰበሰበ በኋላ ተኩስ በመክፈት የንጹሃንን ህይወት መቅጠፉን ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት፡፡

ከጥቃቱ የተረፉትም ከአካባቢው ሸሽተው እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም የተነሳ የሟቾች እንዲሁም አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸውን ቁጥር በትክክል መግለፅ እንደማይችሉ ተናግረዋል።

ቡድኑ በአካባቢው የሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከ120 በላይ ቤቶችን ማቃጠሉን ገልፀዋል።

አሁን ላይ የጸጥታ ኃይል ወደ አካባቢው ተሰማርቶ ሁኔታውን እያረጋጋ ነው።

በሌላ በኩል ፦

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፥ "በትላንትናው እለት ማታ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ጋንቃ በተባለው ቀበሌ ባዜጎቻችን ላይ የሽብር ጥቃት ተፈፅሟል" ብለዋል።

በሽብር ጥቃቱ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፥ "በዚህ የሽብር ጥቃት ዉድ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅኩ የተፈጠመውን የሽብር ጥቃት አጥብቄ አወግዛለሁ፡፡" ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ በ"ኦነግ ሸኔ" አሸባሪ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ላረጋግጥ እወዳለሁ ሲሉ ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ በምዕራብ ወለጋ ትናንት የተገደሉት ሰዎች ለስብሰባ በተጠሩበት ስፍራ መሆኑን #ለBBC አረጋግጠዋል።

አቶ ጌታቸው እንደተናገሩት ከሆነ በሐሰተኛ መልኩ ነዋሪዎች ለስብሰባ ከተሰበሰቡ በኋላ በተወረወረባቸው ቦምብ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

"በ ኦነግ ሸኔ ስም የሚንቀሳቀስው ቡድን ትናንት በስበሰባ ስም ሰዎችን ከሰበሰቡ በኋላ ቦምብ ወርውረውባቸው ጉዳት መድረሱን የሚጠቁም መረጃ ነው ያለን" ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ፥ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው መረጃ አጣርቶ የሚልክ ቡድን ወደ ሥፍራው ተልኳል ብለዋል።

በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች አሃዝ ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ እየተፈጸመ ባለው ማንነትን መሠረት ባደረገው ጥቃት እጅግ ማዘናቸው ገለፁ።

እየተፈፀመ ያለው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሕዝቡ እንዲደናገጥ ፣ እንዲፈራ እና በስሜት ያልተገባ ርምጃ እንዲወስድ የታለመ ነው ብለዋል።

መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ያላቸውን ጥፋቶች በቅድሚያ መረጃ ሰብስቦ ርምጃ በመውሰድ ሲያከሽፍ ቆይቷል ሲሉ ገልጸዋል።

ነገር ግን ያለፈው ሥርዓት ያወረሰንን ቀዳዳዎች ሁሉ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ደፍኖ መጨረስ አልተቻለም ብለዋል።

ዶ/ር አብይ፥ "የጥፋት ኃይሎች ከውጭ ላኪዎቻቸውና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በሚገኙ ባልጠሩ አድር ባዮች ትብብር በሕዝባችን ላይ አሳዛኝ ጥቃት እያደረሱ ነው። ሁኔታው እንደ መሪም እንደ ዜጋም ልብ ይሰብራል።" ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Guliso

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፥ "የጸጥታ አካላት ትላንት ጥቃት ወደተፈጸመበት አካባቢ ተሰማርተዋል ፤ እርምጃም እየወሰዱ ነው" ብለዋል።

በቀጣይም መንግስት የሕዝቡን ደኅንነት የመንግሥትነቱን ሥራ ይሠራል ሲሉ ገልፃዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ፥ "ሕዝቡ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የጸጥታ አካላት፣ ምሁራንና ሌሎችም መንግሥት ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ የሚወስደውን ርምጃ በመደገፍ የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ" ብለዋል።

በሌላ በኩል ፦

ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በንፁሃን ላይ #ማንነትን መሰረት እያደረገ በሚፈፀመው ተደጋጋሚ ጥቃት ሀዘናቸውን እና ቁጣቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት በየጊዜው ንፁሃን ሞት በኃላ መግለጫ ከማውጣትና አዘንኩ ከማለት በቅድሚያ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ እንዳለበት በጥብቅ እያሳሳቡ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#1

አብመድ : ጥቃቱ ሲፈፀም የፀጥታ አካል አልነበረም ? ፖሊስ ፣ መከላከያ ሰራዊት ፣ ሌላ የአስተዳደርና ፀጥታ መዋቅር ?

የአካባቢው ነዋሪ : "የለም፤ ኮማንድ ፖስት ነበር 3 ቀን እና 4 ቀን ይበልጠዋል ተነስቷል። እንዴት እንደተነሳ ግራ ገብቶናል ተነስቶ ሲሄድ ነው ይኼኛው ይገባው።"

#2

የአካባቢው ነዋሪ : "መከላከያው ጥዋት ወጥቶ ከሰዓት እነዛ 'ኦነግ ሸኔ' ጨፍረው ገቡ። ከገቡ በኃላ 11 ሰዓት አካባቢ የሚፈልጉትን ነገር አደረጉ።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነገ ጥቅምት 24/2013 አሜሪካውያን ቀጣይ መሪያቸውን የሚመርጡበት ወሳኝ ቀን።

ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣናቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ ? ወይስ ይቀጥላሉ ? የሚለው የሚለይበት ቀን።

ሪፐብሊካን ፓርቲ ወክለው ከዴሞክራቱ ጆ ባይደን ጋር አንገት ለአንገት የተናነቁት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቁርጣቸውን የሚያውቁት ነገ ጥቅምት 24/2013 ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,726
• በበሽታው የተያዙ - 359
• ህይወታቸው ያለፈ - 11
• ከበሽታው ያገገሙ - 953

በአጠቃላይ በሀገራችን 96,942 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,489 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 54,405 ከበሽታው አገግመዋል።

353 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 32 ነው ሲል አሳውቋል።

ጥቃት የተፈጸመበት ቀበሌ ከወረዳ ከተማ በ75 ኪሎ ሜትር የሚርቅ መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንደተናገረው በጥቃቱ 32 ሰዎች (23 ወንድ እና 9 ሴት) ሲገደሉ ፤ 10 ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።

ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ 200 ሰዎች ተፈናቅለዋል ያለ ሲሆን እነሱን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው ሲል ገልጿል።

በጥቃቱ መኖሪያ ቤቶች እና አንድ ትምህርት ቤት ተቃጥሏል።

ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ፥ "ጥቃቱን የፈጸመው አካል ኦነግ ሸኔ ነው፤ ከጀርባ በመሆን ህወሃት እየደገፈው ይገኛል" ብለዋል።

በሌላ በኩል ኢሰመኮ ስለጉሊሶ ወረዳው ጥቃት ፦

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የፌዴራል ሰራዊት ከአካባቢው ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የታጠቁና ያልታጠቁ በቁጥር 60 የሚሆኑ ቡድኖች 32 የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎችን ማንነታቸውን መሰረት በማድረግ ግድያ መፈፀማቸውን ገልጿል።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ነው ብለዋል፡፡

ዜጎቹ ከቤታቸው ወደ ትምህርት ቤት ተወስደው ግድያ እንደተፈጸመባቸው ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

የጥቃቱ አድራሾች ለፍርድ እንዲቀርቡም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል፡፡

የፌዴራል መንግስት አመራሮች ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሰራዊት እንደሆኑ መናገራቸው የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ሴቶችና ሕፃናት የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡

የፌዴራል መንግስትና የክልል ባለስልጣናት ግድያው #በገለልተኛ_ቡድን እንዲጣራ እንዲያደርጉ እና የሰላማዊ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ አስፋላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"የአቶ ልደቱ አያሌው ጤና አሳስቦናል" - ኢዴፓ ትላንት የቀድሞ የኢ.ዴ.ፓ ም/ፕሬዘዳንት ወ/ሮ ሶፊያ ይልማና የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ሳህሉ ባዬ ከሌሎች አመራር አባላት ጋር በመሆን በቢሸፍቱ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው አቶ ልደቱ አያሌው ጠይቀዋል። ከአቶ ልደቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ የአቶ ልደቱ የጤና ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ማክሰኞ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ላንድማርክ…
#UPDATE

ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው ህክምና እንዲያገኙ ዛሬ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ይህንን ተከትሎ አቶ ልደቱ ነገ ህክምና እንደሚያገኙ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለBBC አማርኛ ክፍል ተናግረዋል።

አቶ አዳነ ስለ አቶ ልደቱ የጤና ሁኔታ ተከታዩን ብለዋል ፦

"በእውነት ምንም ሳልደብቅ መናገር የምፈልገው ነገር ቢኖር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ የህመም ስሜት ይታይባቸዋል። ሰውነታቸው ትንሽም ቢሆን ቀነስ ብሏል።

በእርሳቸው ህመም ሰው እንዲጨነቅ ስለማይፈልጉ በጣም ካልባሰባቸው በስተቀር ህመማቸውን እና ስቃያቸውን ለሰው መናገር አይፈልጉም።

በዚህ ሳምንት በሶስቱ (3) ቀናት ያየነው ነገር ግልጽ ህመም እየተሰማቸው እንደሆነ ፤ በህይወታቸውም ላይ አደጋ እንዳይደርስ እየሰጉ እንደሚተኙ ነው። ከዚያ በፊት ህመም አይሰማኝም አታስቡ አትጨቁ ነበር የሚሉት።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ፦

አዲስ አበባ ላይ የመደበኛ ፓስፖርት አገልግሎት ከህዳር 1 ቀን 2013 ዓ/ም ይጀምራል።

ለመሆኑ አሁን በonline ላይ ምን አገልግሎት ነው ማግኘት የሚቻለው ?

- ቪዛ ማራዘም
- የመኖሪያ ፍቃድ ማደስ እና መጠይቅ
- ፓስፖርት ማሳደስ
- ለአዲስ ፓስፖርት ቀጠሮ ማስያዝ

አዲስ "ፓስፖርት" ለማግኘት የኦንላይን (online) ቀጠሮ ማስያዝን በተመለከተ ፦

• ተገልጋዩ ዶክተመቱን በኦንላይን ይልካል
• ተገልጋዩ እስኪመጣ INVEA ዶክመቱን ያጣራል
• ተገልጋዩ በባንክ ከፍሎ በተባለው ቀን ይሄዳል
• በዚህ ሂደት በቀጠሮ ቀን ተገልጋዩ ይስተናገዳል

የኦንላይ ፓስፖርት ማደሻ እንዲሁም ቀጠሮ ማስያዣ ድረገፅ የቱ ነው ?

ይኸው: www.ethiopianpassportservices.gov.et

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed #BekeleGerba

በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጀዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ የደህንነት ስጋት አለን በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የልደታ ምድብ ችሎት የተከሳሾች የንብረት እግድ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው።

ይሁን እንጂ ከተከሳሾች መካከል አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት አልተገኙም።

ፍርድ ቤቱም አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ለምን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ በጠየቀበት ወቅት፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከሳሾቹ የደህንነት ስጋት አለብን በሚል ምክንያት አለመቅረታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ውስጥ የተከሰሱት አቶ ሐምዛ ቦረና፤ "አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ 'አገሪቱ አሁን ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋት ስላለን በዚህ ቀጠሮ መገኘት አንችልም' ብለዋል" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

"አሁን ባለው ሁኔታ አይደለም ጉዳት ይቅርና ሙከራ [የግድያ] ቢደረግብን አገሪቱ ወደ ከፋ አደጋ ውስጥ ስለሚያስገባት ለአገሪቱ በማሰብ ወደ ፍርድ ቤት ከሚደረግ ጉዞ እራሳችንን ቆጥበናል" ስለማለታቸው አቶ ሐምዛ ቦረና ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አሁን አገሪቱ ውጥረት ውስጥ እያለች በንብረት ጉዳይ ላይ ለመከራከር ፍርድ ቤት መመላለስ 'ለእኛ ሃፍረት' ነው በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን አቶ ሐምዛ፤ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለን ወክለው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ በንብረት እግዱ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሕዳር 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል። (BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...ለተፈፀመው ጥቃት መንግስት ተጠያቂ ነው" - የአማራ ምሁራን መማክርት

በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ውስጥ በአማራዎች ላይ በተፈፀመው ጥቃት መንግስት ተጠያቂ ነው ሲል የአማራ ምሁራን መማክርት በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

የምሁራን መማክርቱ እንዳለው ጥቃቱን ማንም ይፈፅመው ማን መንግስት የማስቆም ግዴታ አለበት።

በአማራ ላይ የተቃጠውን ጥቃት መንግስት ማስቆም ካልቻለ ኢትዮጵያን ወደ ማትመለስበት ችግር ይከታታልም ብሏል።

"መንግስት የህዝቦችን ደህንነትን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት ቢያውቅም ችላ በማለቱ በተለይም በአማራ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ቀጥለዋል። ይሄም የአማራን ህዝብ በከፍተኛ ደረጃ አስቆጥቷል፤ መንግስት ጉዳዩን በውል ሊረዳው ይገባል" ሲል ገልጿል።

መንግስት የአማራን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ተጨባጭ ሥራ ሰርቶ ማሳየት ይገባዋል ተብሏል።

አማራ ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት የአንበሳው ድርሻ እንደተጫዎተ ቢታወቅም አሁን ላይ አንገቱን ቀና እንዳይደረግ ከሁለተኛም ዜጋ ባነሰ ሁኔታ እንዲሆን እያደረገ ነው፤ ይሄ ኢትዮጵያን ያፈርሳል፤ መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግሩን ከማውገዝ ባለፈ ሊከላከል ይገባልም ብሏል፡፡

ችግሩ ሰፍቶ ሁላችንም ወደማያባራ እልቂት ከመዳረጉ በፊት ሊታሰብበት እነደሚገባ አመላክቷል፡፡

የፌድራል መንግስት ድርጊቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ በማመን እርምጃ መውሰድ እንዳለበት የምሁራን መማክርቱ ገልጿል። (AMMA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን አዲስ አበባ ገቡ። የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ በሚኖራቸው ቆይታ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ገልጿል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በኢትዮጵያ ለ2 ቀን ያደረጉትን ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።

ዛሬ ጠዋት ወደ ካርቱም ተመልሰዋል።

ሌ/ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ፣ የግብርና የኢንቨስትመንት ስራዎችን መጎብኘታቸው ኤፍ ቢ ሲ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦኛል" - አውሮፓ ህብረት

የአውሮፓ ሕብረት ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው #BBC ዘግቧል።

የሕብረቱ ምክትል ፕሬዝደንትና የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል ባወጡት መግለጫ ነው የሕብረቱን አቋም ያንፀባረቁት።

"ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው" ያለው መግለጫው ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች እና ጎረቤት አገራት ውጥረት ለመቀነስ መጣር እንዳለባቸው አሳስቧል።

ሁሉም ቡድኖች "ግጭት ቀስቃሽ ቃላት" መጠቀም ማቆም እንዳለባቸውና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን መግታት እንዳለባቸው አሳስቧል። "ይህ መሆን ካልቻለ ግን ጉዳቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናውም ነው" ብሏል።

መግለጫው ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር አገር አቀፍ ውይይቶች እንደሚያስፈልጉ አትቷል። በዚህ ውይይት ላይ ሁሉም የፖለቲካ ተዋናዮች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

ለኢትዮጵያ ሕዝብ መፃዒ ተስፋና ብልፅግና ብሔራዊ መግባባት እንጂ ግጭት መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል ምክትል ፕሬዝደንቱ በመግለጫቸው ገለፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia