TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 32 ነው ሲል አሳውቋል።

ጥቃት የተፈጸመበት ቀበሌ ከወረዳ ከተማ በ75 ኪሎ ሜትር የሚርቅ መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንደተናገረው በጥቃቱ 32 ሰዎች (23 ወንድ እና 9 ሴት) ሲገደሉ ፤ 10 ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።

ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ 200 ሰዎች ተፈናቅለዋል ያለ ሲሆን እነሱን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው ሲል ገልጿል።

በጥቃቱ መኖሪያ ቤቶች እና አንድ ትምህርት ቤት ተቃጥሏል።

ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ፥ "ጥቃቱን የፈጸመው አካል ኦነግ ሸኔ ነው፤ ከጀርባ በመሆን ህወሃት እየደገፈው ይገኛል" ብለዋል።

በሌላ በኩል ኢሰመኮ ስለጉሊሶ ወረዳው ጥቃት ፦

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የፌዴራል ሰራዊት ከአካባቢው ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የታጠቁና ያልታጠቁ በቁጥር 60 የሚሆኑ ቡድኖች 32 የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎችን ማንነታቸውን መሰረት በማድረግ ግድያ መፈፀማቸውን ገልጿል።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ነው ብለዋል፡፡

ዜጎቹ ከቤታቸው ወደ ትምህርት ቤት ተወስደው ግድያ እንደተፈጸመባቸው ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

የጥቃቱ አድራሾች ለፍርድ እንዲቀርቡም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል፡፡

የፌዴራል መንግስት አመራሮች ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሰራዊት እንደሆኑ መናገራቸው የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ሴቶችና ሕፃናት የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡

የፌዴራል መንግስትና የክልል ባለስልጣናት ግድያው #በገለልተኛ_ቡድን እንዲጣራ እንዲያደርጉ እና የሰላማዊ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ አስፋላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia