TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

በአራዳ ወረዳ 10 ክላስተር 2 ቀጠና 3 የግሪክ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ቀን 11 ስአት ከ20 ላይ ከማድ ቤት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የቤትቁ 105 እና 104 ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወደመ።

የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ባለስልጣን በፍጥነት በመድረሱ እሳቱ ወደሌሎች ቤቶች ሳይዛመት መግታት ተችላል።

በቃጠሎው በሰው ህይወት ላይ አደጋ አልደረስም።

ምንጭ፦ የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ፦

"ለምዝገባ የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር (Tin No.) ግዴታ ያስፈልጋል ፤ ካልሆነ ምዝገባ ማድረግ አትችሉም" እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ MoSHE እንደማያውቀው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማምሻውን ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ምዝገባ የሚመለከተው MoSHE ብቻ ነው።

ስለዚህ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችሁ ስትመለሱ ለምዝገባ ምንም አይነት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) #አያስፈልጋችሁም

ይህን መረጃ ለሌሎች አሳውቁ!

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Audio
መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ሰጠ !

መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ከሰሞኑን በትግራይ መገናኛ ብዙሃን "ወቅታዊ የአቋም መግለጫ" በሚል ርዕስ ስር ሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በሚመለከት የወጣው መግለጫ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ገልጿል።

ሚኒስቴሩ "መግለጫውን ያወጣው አካል ስህተቱን በይፋ እንዲያርም አጥብቀን እንጠይቃለን" ብሏል።

መከላከያ ሚኒስቴር ማንኛውም አካል የሰራዊቱን ተልዕኮ በሚያደናቅፍ መልኩ መግለጫ ከመስጠት እና አላስፈላጊ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ እንዲቆጠብ አሳስቧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰጠውን መግለጫ ከላይ ያዳምጡ (11.3 MB) ፤ ድምፁ የተወሰደው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ👆

" ... የሃገር መከላከያ ሰራዊት ስምሪት እና ተልዕኮ በምንም መልኩ በአንድ አካል ወይም ቡድን ስር የማይወድቅ ህጋዊና ህገ መንግስታዊ በሆነ አግባብ ብቻ የሚመራ መሆኑን እያስታወቅን መግለጫውን ያወጣው አካል ስህተቱን በይፋ እንዲያርም አጥብቀን እንጠይቃለን።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እና የኮሚሽኑ ባለሙያዎች በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ስር የሚገኘው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥቅምት 20/2013 ዓ/ም በመገኘት በታሳሪዎች አያያዝ ሁኔታ ላይ ክትትል ማድረጋቸው ተገልጿል።

• ጃዋር መሐመድ
• በቀለ ገርባ
• ሀምዛ ቦረና
• ደጀኔ ጣፋ
• ሸምሰዲን ጣሃ
• ጋዜጠኛ መለስ ድሪብሳ
• እስክንድር ነጋ
• ስንታየሁ ቸኮልን
• ቀለብ ስዩም
• አስካለ ደምሌ በተጨማሪም እነ ጄነራል ክንፈ ዳኘው እና ሌሎች ታሳሪዎች የሚገኙበትን የእስር ሁኔታ ጐብኝተዋል ፣ ታሳሪዎች እና ኃላፊዎችን ለየብቻ አነጋግረዋል፡፡

ከኢሰመኮ የተላከውን መግለጫ ከላይ ይመልከቱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገቡ ተመራቂ ተማሪዎች በቂ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት መዘጋጀቱን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ለኢዜአ ገልጿል።

ከጥቅምት 23 ጀምሮ ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

ተማሪዎች እንዳይጉላሉ ሲባል ከመናኸሪያ እስከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ ድረስ የማጓጓዝ አገልግሎት ትብብርን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚሰጠ ተገልጿል።

የተማሪዎቹን የትራንስፖርት አገልግሎት ከፀጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጅት መደረጉ ተልጿል።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል በጉዞ ወቅት ተማሪዎች አስገዳጅ የጤና መመሪያዎችን ሊተገብሩ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሱዳን ገቡ!

በግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል መሐመድ ፋሪድ የሚመራ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑካን ቡድን ሱዳን ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ኻርቱም ሲደርስ የሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሉቴናንት ጄኔራል መሐመድ ኦስማን አል-ሁሴይን እንደተቀበሉት የሱዳን ዜና አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ DW ዘግቧል።

የግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በሁለቱ አገሮች የጸጥታ እና ወታደራዊ ትብብር ላይ ይመክራሉ ተባቧል።

ሱዳን እና ግብጽ የሚሳተፉበት የኅዳሴ ግድብ ድርድር ባለፈው ማክሰኞ ሲጀመር የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን ወደ ካይሮ አቅንተው ነበር።

በጉዟቸው ከግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል ሲሲ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

የደቡብ ሱዳን የመከላከያ እና ጡረተኛ ወታደሮች ጉዳይ ምኒስትር አንጌሊና ጄኒ ቴኒ ትናንት ወደ ካርቱም አቅንተው ነበር።

ምኒስትሯ በካርቱም ቆይታቸው ከሱዳን የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል ቡርኻን ተገናኝተው እንደተወያዩ ተዘግቧል።

ከአንጌሊና ጄኒ ቴኒ በተጨማሪ ሱና እንደዘገበው የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የአገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትሮች ፣ የአገሪቱ የፖሊስ አዛዥ ፣ የጸጥታ እና ደሕንነት መሥሪያ ቤት መሪዎች ወደ ሱዳን ተጉዘዋል። (DW)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,386
• በበሽታው የተያዙ - 380
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 804

በአጠቃላይ በሀገራችን 96,169 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,469 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 52,517 ከበሽታው አገግመዋል።

335 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“ቅዳሜን ለሀገሬ አርሶ አደር”

የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች አንበጣ መንጋ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከልና አርሶ አደሩን ለመታደግ ዛሬ በሁለት (2) አቅጣጫዎች ዘምተው ነበር።

ደጋፊዎቹ ፥ “ቅዳሜን ለሀገሬ አርሶ አደር” በሚል መሪ ቃል ነው ወደ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በረኸት ወረዳ እና ወደ ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አድዓ ወረዳ የተጓዙት።

በቆይታቸውም በአንበጣ መንጋ ምክንያት በከፍተኛ የህልውና ስጋት ላይ ከወደቀው አርሶ አደር ጎን ተሰልፈው የደረሱ ሰብሎች በማጨድ፣ የታጨዱትን በመሰብሰብና ምርቱን ወደ ጎተራ በማስገባት ድጋፍ አድርገዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ፥ "ክለቡ ህዝባዊ እንደመሆኑ ለወገኖቹ ቀድሞ የሚደርስ የወገን አለኝታ ነው ፤ ትናንትም ከህዝብ ጎን ነበር ፤ ዛሬም ከህዝብ ጋር ነው ፤ ወደፊትም ከህዝብ ጎን ሆኖ ይቀጥላል" ብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
100 የሚሆኑ ኤርትራውያን ወታደሮች፣ ሴቶች፣ህፃናት ፣ወጣቶች፣ ተማሪዎች ድንበር አቋርጠው በዛላንበሳ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

ስደተኞቹ የኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይ ስላልተቀበላቸው ለ1 ወር የሚሆን ጊዜ በዓዲግራት በመቆየታቸው እያማረሩ ነው።

ከስደተኞቹ መካከል አንዷ ሳደም ለቪኦኤ ተከታዩን ብላለች፦

"ወደ ኢትዮጵያ ከገባው 20 ቀን ሆኖኛል። በዛላንበሳ በኩል ነው የገባሁት ፤ ዛላንበሳ ተቀብለው ወደ አዲግራት ላኩን።

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለ12 ቀናት ከቆየን በኃላ የኮሮና ምርመራ ተደርጎልን ነፃ መሆናችን ተረጋግጦ በአንድ ት/ቤት እንገኛለን።

እኛ ወደኢትዮጵያ ከገባን በኃላ ህግ ተቀይሯል። ወታደሮችና የመንግስት ሰራተኞች ስላልሆናችሁ አንቀበልም አሉን። እኛ ዜጎች ነን ተመችቶት ከሀገሩ መውጣት የሚፈልግ የለም። ስላልተመቸን ነው የወጣነው!

እኔ ቴክኒክ ት/ቤት ተመርቄ ወላጆቼ ለማገዝ በተዘጋጀሁበት ጊዜ ሳዋ መሄድ አለብሽ ተባልኩ ፤ እኔም ሰዋ ሄጄ ወታደር መሆን ስላልፈለኩ ወደ ኢትዮጵያ መጣሁ።

የግድ ሳዋ መሄድ አለብኝ? የግድ ሁላችንም መቀበል አለባቸው"

ስደተኛዋ ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ከገባች ጀምሮ ለተደረገላት አቀባበል ለትግራይ ህዝብ አድናቆቷን ገልፃለች።

ሌላ ስሙ ያልተገለፀ ስደተኛ፦

"እኔ በዛላንበሳ በኩል ነው ወደኢትዮጵያ የገባሁት ሁለት ሳምንት በዓዲግራት ቆይተናል። የስደተኞች ጉዳይ ወታደርና የመንግስት ሰራተኛ ብቻ ነው የምንቀበለው ብለዋል።

በአንድ ቀን ከ8-9 ነው የሚቀበሉት። እኔ የ27ኛው ዙር የሳዋ ሰልጣኝ ነኝ። ያረፍንበት ቦታ ትምህርት ቤት በመሆኑ ትምህርት እየተጀመረ ስለሆነ ወዴት እንደምንሄድ ግራ ገባን።

የዓዲግራት እናቶች ከቤታቸው እንጀራ በመሸከም እኛን እንዳይከፋን እያገዙን ነው።"

(ብርሃነ VOA)

@tikvahethiopia
ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን አዲስ አበባ ገቡ።

የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ በሚኖራቸው ቆይታ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የአቶ ልደቱ አያሌው ጤና አሳስቦናል" - ኢዴፓ

ትላንት የቀድሞ የኢ.ዴ.ፓ ም/ፕሬዘዳንት ወ/ሮ ሶፊያ ይልማና የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ሳህሉ ባዬ ከሌሎች አመራር አባላት ጋር በመሆን በቢሸፍቱ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው አቶ ልደቱ አያሌው ጠይቀዋል።

ከአቶ ልደቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ የአቶ ልደቱ የጤና ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማክሰኞ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ላንድማርክ ሆስፒታል የህክምና ቀጠሮ ያላቸው ቢሆንም ወደ ሆስፒታሉ ስለመወሰዳቸው ምንም ማረጋገጫ እንደሌላቸው መግለፃቸውን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አረጋግጠዋል። (ኢዴፓ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ትላንት የኢትዮጵያ ኣትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት ኮ/ል ደራርቱ ቱሉ ትራንስ ኢትዮጵያ (ትእምት) ለለተሰንበት ግደይ ባዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መድረክ ተገኝተው ነበር።

ኮ/ል ደራርቱ በቶክዮ ኦሎምፒክ አገራቸውን ወክለው የሚሳተፉ የትግራይ አትሌቶችን አነጋግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኮ/ል ደራርቱ ላሳዩት ቆራጥ አመራር የእውቅና ሽልማት እና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

#ትእምት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደ/ፅዮን ገ/ሚካኤል ከኢትዮጵያ ኣትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት ኮ/ል ደራርቱ ቱሉ ጋር ተገናኝተዋል።

በቆይታቸው ስፖርታዊ ጉዳዮችን አንስተው የተወያዩ ሲሆን ዶ/ር ደ/ፅዮን ኮ/ል ደራርቱን ትራንስ ኢትዮጵያያ (ትእምት) ለለተሰንበት ግደይ ባዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መድረክ በመገኘታቸው አመስግነዋል።

እንዲሁም በቶክዮ ኦሎምፒክ አገራቸውን ወክለው ለሚሳተፉ የትግራይ አትሌቶችን ለማነጋገር ወደ ትግራይ በመምጣታቸው በትግራይ ክልል መንግስት ስም አመስግነዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ፥ የትራንስ ኢትዮጵያ (ትእምት) ውጤት የሆነችውና በሀገሯ ልጅ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ለ12 አመታት ተይዞ የነበረውን የ5 ሺ ሜትር ርቀት ሩጫ የዓለም ሪከርድ እንድታሻሽል "የአንቺ አሻራ ትልቅ" ሲሉ ኮ/ል ደራርቱን አሞካሽተዋቸዋል።

በመጪው ሀምሌ በቶክዮ የሚካሄደውን የኦሎምፒክ ውድድር ከትእምት ኩባንያዎች የተመረጡ 15 የትግራይ ስፖርተኞች አገራቸውን ወክለው ይሳተፋሉ።

#ትእምት

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,901
• በበሽታው የተያዙ - 414
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 935

በአጠቃላይ በሀገራችን 96,583 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,478 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 53,452 ከበሽታው አገግመዋል።

336 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ፦

የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡

የድርድሩን ቀጣይ አካሄድ ላይና የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ሰፊ ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሶስቱም ሀገራት ሁለት ሁለት ባለሞያዎችን ከሦስቱ ሀገራት በመሰየም በድርድር አካሄድ እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት የሰየማቸው ባለሞያዎች ተጨማሪ ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ ሪፓርት ለውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲያቀርቡ መግባባት ላይ ተደርሷል።

የባለሙያዎች ስብሰባ ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን የደረሰበትንም ጉዳይ በጥቅምት 24 ለሚካሄደው የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ድርድር ያቀርባል

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia