TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CrisisGroup

ዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው ውጥረት አይሎ "ወደ ግጭት" ሊሸጋገር ይችላል ማለቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ክራይሲስ ግሩፕ በ2ቱ አካላት መካከል ያለው አለመግባባት ተባብሶ ወዳልተፈለገ ደረጃ ከመድረሱ በፊትም መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን አማራጮች ሰንዝሯል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-10-30

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ክራይሲስ ግሩፕ በፌዴራል እና በትግራይ ክልል ጉዳይ ፦

• ዓለም አቀፉ ማህብረሰብ ኢትዮጵያ የገባችበት አጣብቂኝ እንዳይባባስ ከፈለጉ ብሔራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ የበኩላቸውን ሚና መወጣት አለባቸው።

• የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት እንዲሁም የአውሮፓ ሕብረት የፌደራል መንግስት ከትግራይ መንግስት ጋር ወደ ውይይት እንዲመጣ ጫና መፍጠር አለባቸው።

• የትግራይ ክልል መንግስት የፌደራል መንግስት እንደ ትንኮሳ የሚመለከተውን መግለጫ ማውጣት እንዲያቆም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ማሳደር ይኖርበታል።

• ለኢትዮጵያ ቅርብ የሆኑት ቻይና እንዲሁም የባህረ ሰላጤው አገራትም ሁለቱ አካላት ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመጡ ጫና መፍጠር አለባቸው።

• በሁለቱ አካላት ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀ መንበር የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ወደ ድርድር እንዲመለሱ ጥረት ማድረግ አለባቸው።

* ችግሮቹ መፍትሄ የማያገኙ ከሆነ በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር ሁለተኛ በሆነችው አገር ኢትዮጵያ 'ጦርነት' ተከስቶ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ሲል ክራይሲስ ግሩፕ ገልጿል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በዋጫ ከተማ 6 ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተያዘ።

ገንዘቡ ጥቅምት 18፣ 2013 በረከት በየነ የተባለ ግልሰብ ከ92 ሺህ ብሮች መሃል 6ሺ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደራማሎ ቅርንጫፍ ገቢ ለማድረግ ይዞ ሲመጣ ነው የተያዘው።

የደራማሎ ፖሊስ ጽህፈ ቤት ህብረተሰቡ በግብይት ወቅት በሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዳይታለል ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጀነራል ሞላ ሀይለማርያም በስራ ላይ ናቸው !

በማህበራዊ ሚዲያ የምድር ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል ሞላ ሀይለማርያምን በሚመለከት እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን 'ኢትዮጵያ ቼክ' አሳውቋል።

የጀነራል ሞላ ሀይለማርያም የስራ ባልደረቦች ጨምሮ ሌሎች ምንጮች እንደገለፁት ዛሬ ከሰአት ጭምር ጀነራሉ በስራቸው ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በመተከል ዞን 15 ግለሰቦች በሠላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ ተባለ።

እኚህ ግለሰቦች የጸረ-ሠላም ኃይሎችን ተልዕኮ በመፈጸም ሲሳተፉና ሲተባበሩ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

ከህብረተሰቡ ጋር እየተካሄደ ባለ ውይይት እና በተደረሰ የጋራ መግባባት ነው በማንዱራ ወረዳ 1 እና በወምበራ ወረዳ 14 ሰዎች እጃቸውን የሰጡት ብሏል የክልሉ መንግስት።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በሶማሊያ ሴክተር ስድስት (6) የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ሀይል በበልጉድድ ዙሪያ በጎርፍ ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች እገዛ አድርጓል።

ርክክቡ የተከናወነው፣ የ5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ም/አዛዥ ለሰው ሃብት አገልግሎት ሌ/ኮ ገ/ሂወት ኪዳኑ ፣ በኪስማዮ የታችኛው ጁባ ላንድ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱረሽድ አብዱላሂ እና የበልጉድድ አስተዳዳሪ አቶ መሃድ መታን በተገኙበት ነው፡፡

በሌላ በኩል ፦

በኢፌዴሪ አየር ሀይል የሰሜን አየር ምድብ አባላት ፣ በግደጅ ቀጣናቸው አካበቢ ለሚገኙ አቅመ ደካማ አርሶ አደሮች ሰብል በመሰብሰብ እገዛ አድርገዋል።

የሰራዊት አባላቱ የደረሰ ሰብል አጭደው የሰበሰቡት በአይናለም ከተማ ለሚገኙ ሁለት የአቅመ ደካማ አርሶ አደሮች ነው፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አቶ ልደቱ አያሌው አዳማ በሚገኘው ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር።

የአቶ ልደቱ አያሌው የዛሬ ቀጠሮአቸው በጠበቆቻቸው የቀረበውን የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያና የቀረበውን የዋስትና መብት መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር።

ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄ ላይም ሆነ የመጀመርያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 11 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4 ሰአት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የዛሬውን ዝርዝር የፍርድ ቤት ውሎው ከላይ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አዳነ ታደሰ ያጋሩትን ያንብቡ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በተውፊቅ መስጊድ፣ በበኒ ወይም ኑር መስጊድ የፈረንሳዩን ፕሬዜዳንት ማክሮንን ኢስላም ጠል ንግግሩን የሚቃወም ሰልፍ ተደርጓል።

የተቃውሞ ሰልፉ በሶሻል ሚዲያ የተጠራ መሆኑ ተገልጿል።

በኒ መስጊድ በነበረው ሰልፍ ባነሮች ፣ ቲሸርቶች ፣ ከቁርአን እና ከሀዲስ የወጡ የተለያዩ አባባሎች እና መልዕክቶች ነበሩ።

ሰልፉ ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር ተገልጾልናል።

ሙስሊም ወጣቶች መንገድ እንዳይዘጋ እንዲሁም መኪና እንዳይቆም፣ ሰዎችም እንዳይጉላሉ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

በሰልፉ ላይ በፅሁፍ የተላለፉት መልዕክቶች በእንግሊዘኛ፣ በአማርኛ ፣ በአረብኛ እንዲሁም በፈረንሳይኛ የተዘጋጁ እንደነበሩ ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነው ጁነይድ መሀመድ ተናግሯል።

በሌላ በኩል ፦

በዛሬው ሰልፍ ላይ የአሜሪካውን ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሞነኛ ንግግር የሚቃወሙ ድምፆችም ተሰምተዋል።

ፕሬዜዳንቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ በተልይ ደግሞ በህዳሴ ግድቡ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ ፣ የማይገባና የኢትዮጵያውያን ልብ የሚያደማ ንግግር ከመናገር እንዲቆጠብ የሰልፉ ተካፋዮች መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FederalPoliceCommission

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ 300 ሺህ ብር የሚጠጋ ነባሩንና አዲሱን ሐሰተኛ የገንዘብ ኖት መያዙን ኤፍ ቢ ሲ (fbc) ዘግቧል።

ፖሊስ ነባሩን የገንዘብ ኖት ከ2 ተጠርጣሪዎች ሐሰተኛ የሆነ ባለ መቶና ባለ አምሳ 174 ሺህ 350 ብር ይዟል፡፡

ከ1 ግለሰብ ደግሞ ከ200 መቶ ሺህ በላይ ሐሰተኛ አዲሱ ባለ መቶና ባለ ሁለት መቶ የብር ኖት መያዙን ነው የገለጸው፡፡

እንዲሁም ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት 14 ሺህ 800 ሐሰተኛ ባለ መቶ እና ባለ ሃምሳ የአሜሪካ ዶላር ይዟል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,866
• በበሽታው የተያዙ - 488
• ህይወታቸው ያለፈ - 7
• ከበሽታው ያገገሙ - 960

በአጠቃላይ በሀገራችን 95,789 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,464 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 51,713 ከበሽታው አገግመዋል።

327 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

በዎላይታ ዞን ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በመሞከር ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩ ፖለቲከኞች መካከል 5ቱ በዋስ እንዲፈቱ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ውስኗል።

አምስቱ ፓለቲከኞች እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ብር ዋስ ነው ከእስር እንዲወጡ የተወሰነው።

ከ5ቱ መካከል የዎብን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጎበዜ አበራና የዎላይታ ዞን ገቢዎች መምሪያ የገቢ አሰባሰብ ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መብራቱ ጳውሎስ ይገኙበታል።

አቶ ዳጋቶ ኩምቤና ሌሎች 9 ተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄ ፖሊስ ምርመራ አላጠናቀኩም በማለቱ ውድቅ ሆኗል።

ፍርድ ቤት ፖሊስ ምርመራውን በአስር (10) ቀናት ውስጥ እንዲያጠናቅቅ ማዘዙን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአራዳ ወረዳ 10 ክላስተር 2 ቀጠና 3 የግሪክ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ቀን 11 ስአት ከ20 ላይ ከማድ ቤት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የቤትቁ 105 እና 104 ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወደመ።

የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ባለስልጣን በፍጥነት በመድረሱ እሳቱ ወደሌሎች ቤቶች ሳይዛመት መግታት ተችላል።

በቃጠሎው በሰው ህይወት ላይ አደጋ አልደረስም።

ምንጭ፦ የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ፦

"ለምዝገባ የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር (Tin No.) ግዴታ ያስፈልጋል ፤ ካልሆነ ምዝገባ ማድረግ አትችሉም" እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ MoSHE እንደማያውቀው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማምሻውን ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ምዝገባ የሚመለከተው MoSHE ብቻ ነው።

ስለዚህ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችሁ ስትመለሱ ለምዝገባ ምንም አይነት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) #አያስፈልጋችሁም

ይህን መረጃ ለሌሎች አሳውቁ!

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Audio
መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ሰጠ !

መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ከሰሞኑን በትግራይ መገናኛ ብዙሃን "ወቅታዊ የአቋም መግለጫ" በሚል ርዕስ ስር ሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በሚመለከት የወጣው መግለጫ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ገልጿል።

ሚኒስቴሩ "መግለጫውን ያወጣው አካል ስህተቱን በይፋ እንዲያርም አጥብቀን እንጠይቃለን" ብሏል።

መከላከያ ሚኒስቴር ማንኛውም አካል የሰራዊቱን ተልዕኮ በሚያደናቅፍ መልኩ መግለጫ ከመስጠት እና አላስፈላጊ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ እንዲቆጠብ አሳስቧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰጠውን መግለጫ ከላይ ያዳምጡ (11.3 MB) ፤ ድምፁ የተወሰደው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ👆

" ... የሃገር መከላከያ ሰራዊት ስምሪት እና ተልዕኮ በምንም መልኩ በአንድ አካል ወይም ቡድን ስር የማይወድቅ ህጋዊና ህገ መንግስታዊ በሆነ አግባብ ብቻ የሚመራ መሆኑን እያስታወቅን መግለጫውን ያወጣው አካል ስህተቱን በይፋ እንዲያርም አጥብቀን እንጠይቃለን።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እና የኮሚሽኑ ባለሙያዎች በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ስር የሚገኘው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥቅምት 20/2013 ዓ/ም በመገኘት በታሳሪዎች አያያዝ ሁኔታ ላይ ክትትል ማድረጋቸው ተገልጿል።

• ጃዋር መሐመድ
• በቀለ ገርባ
• ሀምዛ ቦረና
• ደጀኔ ጣፋ
• ሸምሰዲን ጣሃ
• ጋዜጠኛ መለስ ድሪብሳ
• እስክንድር ነጋ
• ስንታየሁ ቸኮልን
• ቀለብ ስዩም
• አስካለ ደምሌ በተጨማሪም እነ ጄነራል ክንፈ ዳኘው እና ሌሎች ታሳሪዎች የሚገኙበትን የእስር ሁኔታ ጐብኝተዋል ፣ ታሳሪዎች እና ኃላፊዎችን ለየብቻ አነጋግረዋል፡፡

ከኢሰመኮ የተላከውን መግለጫ ከላይ ይመልከቱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia