#UPDATE
ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገቡ ተመራቂ ተማሪዎች በቂ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት መዘጋጀቱን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ለኢዜአ ገልጿል።
ከጥቅምት 23 ጀምሮ ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።
ተማሪዎች እንዳይጉላሉ ሲባል ከመናኸሪያ እስከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ ድረስ የማጓጓዝ አገልግሎት ትብብርን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚሰጠ ተገልጿል።
የተማሪዎቹን የትራንስፖርት አገልግሎት ከፀጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጅት መደረጉ ተልጿል።
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል በጉዞ ወቅት ተማሪዎች አስገዳጅ የጤና መመሪያዎችን ሊተገብሩ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሱዳን ገቡ!
በግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል መሐመድ ፋሪድ የሚመራ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑካን ቡድን ሱዳን ገብቷል።
ልዑካን ቡድኑ ኻርቱም ሲደርስ የሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሉቴናንት ጄኔራል መሐመድ ኦስማን አል-ሁሴይን እንደተቀበሉት የሱዳን ዜና አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ DW ዘግቧል።
የግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በሁለቱ አገሮች የጸጥታ እና ወታደራዊ ትብብር ላይ ይመክራሉ ተባቧል።
ሱዳን እና ግብጽ የሚሳተፉበት የኅዳሴ ግድብ ድርድር ባለፈው ማክሰኞ ሲጀመር የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን ወደ ካይሮ አቅንተው ነበር።
በጉዟቸው ከግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል ሲሲ ተገናኝተው ተወያይተዋል።
የደቡብ ሱዳን የመከላከያ እና ጡረተኛ ወታደሮች ጉዳይ ምኒስትር አንጌሊና ጄኒ ቴኒ ትናንት ወደ ካርቱም አቅንተው ነበር።
ምኒስትሯ በካርቱም ቆይታቸው ከሱዳን የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል ቡርኻን ተገናኝተው እንደተወያዩ ተዘግቧል።
ከአንጌሊና ጄኒ ቴኒ በተጨማሪ ሱና እንደዘገበው የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የአገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትሮች ፣ የአገሪቱ የፖሊስ አዛዥ ፣ የጸጥታ እና ደሕንነት መሥሪያ ቤት መሪዎች ወደ ሱዳን ተጉዘዋል። (DW)

#DrLiaTadesse
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,386
• በበሽታው የተያዙ - 380
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 804
በአጠቃላይ በሀገራችን 96,169 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,469 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 52,517 ከበሽታው አገግመዋል።
335 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

“ቅዳሜን ለሀገሬ አርሶ አደር”
የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች አንበጣ መንጋ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከልና አርሶ አደሩን ለመታደግ ዛሬ በሁለት (2) አቅጣጫዎች ዘምተው ነበር።
ደጋፊዎቹ ፥ “ቅዳሜን ለሀገሬ አርሶ አደር” በሚል መሪ ቃል ነው ወደ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በረኸት ወረዳ እና ወደ ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አድዓ ወረዳ የተጓዙት።
በቆይታቸውም በአንበጣ መንጋ ምክንያት በከፍተኛ የህልውና ስጋት ላይ ከወደቀው አርሶ አደር ጎን ተሰልፈው የደረሱ ሰብሎች በማጨድ፣ የታጨዱትን በመሰብሰብና ምርቱን ወደ ጎተራ በማስገባት ድጋፍ አድርገዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ፥ "ክለቡ ህዝባዊ እንደመሆኑ ለወገኖቹ ቀድሞ የሚደርስ የወገን አለኝታ ነው ፤ ትናንትም ከህዝብ ጎን ነበር ፤ ዛሬም ከህዝብ ጋር ነው ፤ ወደፊትም ከህዝብ ጎን ሆኖ ይቀጥላል" ብሏል።

100 የሚሆኑ ኤርትራውያን ወታደሮች፣ ሴቶች፣ህፃናት ፣ወጣቶች፣ ተማሪዎች ድንበር አቋርጠው በዛላንበሳ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።
ስደተኞቹ የኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይ ስላልተቀበላቸው ለ1 ወር የሚሆን ጊዜ በዓዲግራት በመቆየታቸው እያማረሩ ነው።
ከስደተኞቹ መካከል አንዷ ሳደም ለቪኦኤ ተከታዩን ብላለች፦
"ወደ ኢትዮጵያ ከገባው 20 ቀን ሆኖኛል። በዛላንበሳ በኩል ነው የገባሁት ፤ ዛላንበሳ ተቀብለው ወደ አዲግራት ላኩን።
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለ12 ቀናት ከቆየን በኃላ የኮሮና ምርመራ ተደርጎልን ነፃ መሆናችን ተረጋግጦ በአንድ ት/ቤት እንገኛለን።
እኛ ወደኢትዮጵያ ከገባን በኃላ ህግ ተቀይሯል። ወታደሮችና የመንግስት ሰራተኞች ስላልሆናችሁ አንቀበልም አሉን። እኛ ዜጎች ነን ተመችቶት ከሀገሩ መውጣት የሚፈልግ የለም። ስላልተመቸን ነው የወጣነው!
እኔ ቴክኒክ ት/ቤት ተመርቄ ወላጆቼ ለማገዝ በተዘጋጀሁበት ጊዜ ሳዋ መሄድ አለብሽ ተባልኩ ፤ እኔም ሰዋ ሄጄ ወታደር መሆን ስላልፈለኩ ወደ ኢትዮጵያ መጣሁ።
የግድ ሳዋ መሄድ አለብኝ? የግድ ሁላችንም መቀበል አለባቸው"
ስደተኛዋ ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ከገባች ጀምሮ ለተደረገላት አቀባበል ለትግራይ ህዝብ አድናቆቷን ገልፃለች።
ሌላ ስሙ ያልተገለፀ ስደተኛ፦
"እኔ በዛላንበሳ በኩል ነው ወደኢትዮጵያ የገባሁት ሁለት ሳምንት በዓዲግራት ቆይተናል። የስደተኞች ጉዳይ ወታደርና የመንግስት ሰራተኛ ብቻ ነው የምንቀበለው ብለዋል።
በአንድ ቀን ከ8-9 ነው የሚቀበሉት። እኔ የ27ኛው ዙር የሳዋ ሰልጣኝ ነኝ። ያረፍንበት ቦታ ትምህርት ቤት በመሆኑ ትምህርት እየተጀመረ ስለሆነ ወዴት እንደምንሄድ ግራ ገባን።
የዓዲግራት እናቶች ከቤታቸው እንጀራ በመሸከም እኛን እንዳይከፋን እያገዙን ነው።"
(ብርሃነ VOA)
@tikvahethiopia

ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን አዲስ አበባ ገቡ።
የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ በሚኖራቸው ቆይታ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ በሚኖራቸው ቆይታ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የአቶ ልደቱ አያሌው ጤና አሳስቦናል" - ኢዴፓ
ትላንት የቀድሞ የኢ.ዴ.ፓ ም/ፕሬዘዳንት ወ/ሮ ሶፊያ ይልማና የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ሳህሉ ባዬ ከሌሎች አመራር አባላት ጋር በመሆን በቢሸፍቱ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው አቶ ልደቱ አያሌው ጠይቀዋል።
ከአቶ ልደቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ የአቶ ልደቱ የጤና ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ማክሰኞ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ላንድማርክ ሆስፒታል የህክምና ቀጠሮ ያላቸው ቢሆንም ወደ ሆስፒታሉ ስለመወሰዳቸው ምንም ማረጋገጫ እንደሌላቸው መግለፃቸውን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አረጋግጠዋል። (ኢዴፓ)

ትላንት የኢትዮጵያ ኣትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት ኮ/ል ደራርቱ ቱሉ ትራንስ ኢትዮጵያ (ትእምት) ለለተሰንበት ግደይ ባዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መድረክ ተገኝተው ነበር።
ኮ/ል ደራርቱ በቶክዮ ኦሎምፒክ አገራቸውን ወክለው የሚሳተፉ የትግራይ አትሌቶችን አነጋግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኮ/ል ደራርቱ ላሳዩት ቆራጥ አመራር የእውቅና ሽልማት እና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
#ትእምት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮ/ል ደራርቱ በቶክዮ ኦሎምፒክ አገራቸውን ወክለው የሚሳተፉ የትግራይ አትሌቶችን አነጋግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኮ/ል ደራርቱ ላሳዩት ቆራጥ አመራር የእውቅና ሽልማት እና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
#ትእምት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደ/ፅዮን ገ/ሚካኤል ከኢትዮጵያ ኣትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት ኮ/ል ደራርቱ ቱሉ ጋር ተገናኝተዋል።
በቆይታቸው ስፖርታዊ ጉዳዮችን አንስተው የተወያዩ ሲሆን ዶ/ር ደ/ፅዮን ኮ/ል ደራርቱን ትራንስ ኢትዮጵያያ (ትእምት) ለለተሰንበት ግደይ ባዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መድረክ በመገኘታቸው አመስግነዋል።
እንዲሁም በቶክዮ ኦሎምፒክ አገራቸውን ወክለው ለሚሳተፉ የትግራይ አትሌቶችን ለማነጋገር ወደ ትግራይ በመምጣታቸው በትግራይ ክልል መንግስት ስም አመስግነዋል።
ዶ/ር ደብረፅዮን ፥ የትራንስ ኢትዮጵያ (ትእምት) ውጤት የሆነችውና በሀገሯ ልጅ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ለ12 አመታት ተይዞ የነበረውን የ5 ሺ ሜትር ርቀት ሩጫ የዓለም ሪከርድ እንድታሻሽል "የአንቺ አሻራ ትልቅ" ሲሉ ኮ/ል ደራርቱን አሞካሽተዋቸዋል።
በመጪው ሀምሌ በቶክዮ የሚካሄደውን የኦሎምፒክ ውድድር ከትእምት ኩባንያዎች የተመረጡ 15 የትግራይ ስፖርተኞች አገራቸውን ወክለው ይሳተፋሉ።
#ትእምት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቆይታቸው ስፖርታዊ ጉዳዮችን አንስተው የተወያዩ ሲሆን ዶ/ር ደ/ፅዮን ኮ/ል ደራርቱን ትራንስ ኢትዮጵያያ (ትእምት) ለለተሰንበት ግደይ ባዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መድረክ በመገኘታቸው አመስግነዋል።
እንዲሁም በቶክዮ ኦሎምፒክ አገራቸውን ወክለው ለሚሳተፉ የትግራይ አትሌቶችን ለማነጋገር ወደ ትግራይ በመምጣታቸው በትግራይ ክልል መንግስት ስም አመስግነዋል።
ዶ/ር ደብረፅዮን ፥ የትራንስ ኢትዮጵያ (ትእምት) ውጤት የሆነችውና በሀገሯ ልጅ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ለ12 አመታት ተይዞ የነበረውን የ5 ሺ ሜትር ርቀት ሩጫ የዓለም ሪከርድ እንድታሻሽል "የአንቺ አሻራ ትልቅ" ሲሉ ኮ/ል ደራርቱን አሞካሽተዋቸዋል።
በመጪው ሀምሌ በቶክዮ የሚካሄደውን የኦሎምፒክ ውድድር ከትእምት ኩባንያዎች የተመረጡ 15 የትግራይ ስፖርተኞች አገራቸውን ወክለው ይሳተፋሉ።
#ትእምት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,901
• በበሽታው የተያዙ - 414
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 935
በአጠቃላይ በሀገራችን 96,583 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,478 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 53,452 ከበሽታው አገግመዋል።
336 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ፦
የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡
የድርድሩን ቀጣይ አካሄድ ላይና የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ሰፊ ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል።
ሶስቱም ሀገራት ሁለት ሁለት ባለሞያዎችን ከሦስቱ ሀገራት በመሰየም በድርድር አካሄድ እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት የሰየማቸው ባለሞያዎች ተጨማሪ ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ ሪፓርት ለውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲያቀርቡ መግባባት ላይ ተደርሷል።
የባለሙያዎች ስብሰባ ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን የደረሰበትንም ጉዳይ በጥቅምት 24 ለሚካሄደው የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ድርድር ያቀርባል

TIKVAH-ETHIOPIA
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ድረገፁን ይፋ ሊያደርግ ነው። በየጊዜው የቲክቫህ አባላት ቁጥር መጨመር እንደ ከዚህ ቀደሙ ከአባላቶች ጋር በምቹ ሁኔታ ለመገናኘት አስቸጋሪ አድርጎታል። አዲሱ ድረገፅ የቲክቫህ አባላት ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ በየአካባቢያቸው ያለውን ጉዳይ በራሳቸው የሚያሳውቁበት ነው። በተጨማሪ በየወረዳው ያሉ የችግሮች ፣ የመብት ጥሰቶች ፣ በየተቋማቱ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አባላቶች…
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይፋ በሚያደርገው ድረገፅ ፦
- አባላት እስከ ወረዳ ደረጃ ምዝገባ ያከናውናሉ።
- እያንዳንዱ አባል በድረገፁ ላይ ማንነቱ ሳይታይ ስላለበት ክልል እና ወረዳ በራሱ መረጃ ያሰራጫል።
- አንድ ሰው ፖስት የሚያደርገው ያለበት ወረዳ ነዋሪዎች ብቻ ያዩታል። እነሱም ስለጉዳዩ መረጃ ይሰጣሉ፣ እውነታውን ይፈትሻሉ፣ ያረጋግጣሉ። ከነሱ ወረዳ ውጭ መልዕክቱ አይታይም።
- መረጃ የሚሰጡት በወረዳቸው ስላሉ ጉዳዮች ብቻ ይሆናል (ይህ የተሳሳተ መልዕክት ለመለየት እና ለራሳቸው የፖለቲካ ትርፍ ሲሉ ከሌላ አካባቢ ፣ ወይም ከውጭ ሆነው በሀሰተኛ አካውንት ተፅኖ የሚፈጥሩትን ይከላከላል)
- ሆን ተብሎ ከሚሰሩ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች የፀዳ ይሆናል። የአንዱ ወረዳ ነዋሪ የሌላው መረጃ ላይ በዘመቻ ተፅእኖ የመፍጠር አቅም የለውም።
- በሶሻል ሚዲያ የሚስራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እራሳቸው አባላት ባሉበት አካባቢ ምላሽ ይሰጡበታል።
- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችም በልዩ ሁኔታ ስላሉበት ሁኔታ እንዲያሳውቁ ነፃ መድረክ ይሆናል።
- ድረገፁ የዜጎች ድምፅ የሚሰማበት ፣ የመብት ጥሰቶች ሲኖሩ የሚገለፁበት፣ በየአካባቢው ያሉ ችግሮች ይፋ የሚወጡበት፣ የፀጥታ ችግሮች የሚጠቆሙበት ፣ ለህዝብ ጥያቄም የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲሰጡበት ግፊት የሚደረግበት ይሆናል።
- የወጣቶች ጥያቄ በቀጥታ በወጣቶቹ ይቀርባል፤ ለዚህም ምላሽ እንዲሰጥ ግፊት ያደርጋል።
- ድረገፁ ላይ አባላት መልዕክት ከማሰራጨት ባለፈ የተደራጁ መረጃዎችን በየዕለቱ ያገኙበታል።
- ዋናው ቻናል ላይ እስከ ወረዳ የተጣሩ መረጃዎች ከድረገፁ ተወስደው ይቀርቡበታል።
- የበጎ አድራጎት ስራዎችም በዞን እና ወረዳ ደረጃ ይሰራሉ።
- ለወጣት አባላቶች የስራ እድል ለማመቻቸት በቂ መረጃ ይሰበሰብበታል።

ዶ/ር ቴድሮስ ራሳቸውን አገለሉ !
የWHO ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኛታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለብቻ ማግለላቸው (ኩዋራንቲን) ማድረጋቸው ተገለፀ።
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ በቅርበት ያገኙት ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ስለተረጋገጥ ራሳቸውን ለብቻ አግልለዋል።
በአሁኑ ሰዓትም ጤናቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ አንደሚገኝ እና ምንም አይነት የቫይረሱ ምልክት እንደሌለባቸው አስታውቀዋል።
ሆኖም ግን በዓለም ጤና ድርጅት ፕሮቶኮል መሰረት ለቀጣይ ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩ ያስታወቁት ዶክተር ቴድሮስ፥ ስራቸውንም ከቤታቸው ሆነው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ aljazeera.com (FBC)

በጉሊሶ ወረዳ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ሰዎች ተገደሉ !
ትላንት ጥቅምት 22 በኦሮሚያ ክልል ግንቢ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃናቱ በተባለ ቀበሌ እስካሁን ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በታጣቂዎች መገደላቸውን የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።
ጥቃት የፈፀሙት ታጣቂዎች በቁጥር ከሃምሳ (50) እስከ ስልሳ (60) የሚደርሱ መሆናቸውን ከሞት የተረፉ ሰዎች ተናግረዋል።
ላለፉት 3 ወራት ሰፍሮ የቆየው የመከላከያ ሰራዊት ከረፋዱ 6 ሰዓት አካባቢው ለቆ እንደወጣም ነዋሪዎች ገልፀዋል።
መከላከያው ከወጣ በኃላ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የመከላከያ ካምፕን በመቆጣጠር ከፍተኛ ጥይት ሲተኩሱ መዋላቸውን ነዋሪዎች አሳውቀዋል።
በሌላ በኩል በፅሁፍ መልዕክታቸውን ያስቀመጡ የቲክቫህ አባላት እንደገለፁት ጥቃቱ በከባድ መሳሪያዎች ጭምር የተፈፀመ ነው።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይህን ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት የፈፀመው ኦነግ ሸኔ ነው ብሏል ፤ የገቡብት ገብተን እርምጃ እንወስዳለን ሲል ዝቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአካባቢውን አባላትና ከጥቃቱ የተረፉትን ሰዎች እያነጋገረ ነው ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመሳለን።
በተጨማሪ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሰዎች ለተለያዩ ሚዲያዎች የሰጧቸው አስተያየቶች እያሰባሰብን ነው ፤ አደራጅተን እናሳውቃለን።
በርካቶች እየተደጋገመ የመጣውን ጥቃት እና የንፁሀን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ እያወገዙ ይገኛሉ ፤ ቁጣቸውንም እየገለፁ ይገኛሉ።
@tikvahethiopiaBOT

በምዕራብ ወለጋ በአንድ ስፍራ ጥቃት ከተፈፀመ በኃላ እስካሁን ምን ያህል ንፁሃን እንደተገደሉና እንደቆሰሉ በመንግስት አልተገለፀም።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት መገለጫ አውጥቷል። ክልሉ በመግለጫው ለጥቃቱ ተጠያቂ ያደረገው 'ኦነግ ሸኔ' ን ነው።
የክልሉ መንግስት በጥቃቱ ለተሰው ወገኖች ሀዘኑን ገልፆ ፤ ለቤተሰቦቻቸው መፅናትን ተመኝቷል።
ከአማራ ሚዲያ ማዕከል የተገኘው መረጃ በጥቃቱ እስካሁን ከ60 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ20 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
ቁጥሩ ግን ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ፥ "አይደለም ከኦነግ ሸኔ ጥቃት የሚከላከለን ቀርቶ አስክሬን የሚያነሳ መንግስት አጥተናል" ብለዋል።
እስካሁን ድረስ ወደ ስፍራው መከላከያ ሰራዊትም ሆነ የመንግስት አካል አልደረሰም ተብሏል።

#AmharaProsperityParty
የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ትላንት ምሽት በጉሊሶ ወረዳ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት መፈፁሙን አረጋግጫለሁ ብሏል።
የጥቃቱን መጠን እና ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፌዴራል እና ክልል መንግስት ጋር በመሆን እያጣራ እንደሆነ አሳውቋል።
ፓርቲው ፥ "በተፈፀመው ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት የአማራ ህዝብና ድርጅታችን የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ክፉኛ አዝኗል፣ ተቆጥቷል" ሲል በመገለጫው ገልጿል።
ሙሉ የመግለጫውን ሀሳብ ከላይ አንብቡ !