TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #Eurobond ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም። ገንዘብ ሚኒስቴር የክፍያ መጠኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል እንደሚቻል ገልጿል። ክፍያውን ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች በፍትሃዊነት እኩል ለማስተናገድ ነው ብሏል። @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #Eurobond
ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለድ በወቅቱ ያልከፈለችው ለምንድነው ?
ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም።
የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ለሽያጭ የቀረበው ከ9 ዓመት በፊት በ2007 ዓ.ም ነበር።
ኢትዮጵያ ይህንን ቦንድ ሸጣ ከገዢዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኘች ሲሆን ብድሩ የሚመለሰው በ10 ዓመት ውስጥ ነው።
እስከዚያው ድረስ መንግሥት በዓመት ሁለት / 2 ጊዜ የሚፈጸም የ6.625 በመቶ ዓመታዊ ወለድ ለቦንዱ ገዢዎች ይከፍላል።
ኢትዮጵያ ባለፈው ሰኞ ዕለት 33 ሚሊዮን ዶላር ወለድ መክፈል የነበረባት ቢሆንም ክፍያውን ሳትፈጽም ቀናት አልፈዋል።
" የክፍያ መጡኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል ይቻላል ፤ ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች እኩል ለማስተናገድ ነው " - ገንዘብ ሚኒስቴር
የብድር ቦንዱን አስመልክቶ ትላንትና ከቦንድ ገዢዎች ጋር የገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በነበሩበት ውይይት ተደርጎ ነበር።
ይህን በተመለከተ ገንዘብ ሚኒስቴር ምን አለ ?
- ኢትዮጵያ #የታኅሣሥ_ወርን ወለድ ያላስተላለፈችው ክፍያውን ለማዘግየት ወስና ነው። ይህም ለገዢዎቹ ተገልጿል።
- ኢትዮጵያ #ወለዱን_ለመክፈል የሚያስችል ገንዘብ አላት።
- ክፍያውን የማዘግየት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ሁሉንም የውጪ አበዳሪዎች በፍትሐዊነት ለማስተናገድ ሲባል ነው።
- አበዳሪዎች #በፍትሐዊነት ለመመልከት አለመቻል በዕዳ ሽግሽግ ላይ ከሌሎች የውጭ አበዳሪዎች ጋር የሚደረገውን ውይይት አደጋ ላይ ይጥለዋል። ወለዱ ቢከፍል መስተገጓጎል ሊያጋጥም ይችላል።
- በቅርቡ ከኦፊሴላዊ አበዳሪዎች ጋር የብድር ክፍያ ሽግሽግን በተመለከተ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
- #የቦንድ_ገዢዎችን ጨምሮ ሌሎች አበዳሪዎችም ተመሳሳይ አይነት የብድር ክፍያ ማስተካከያ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ከሁሉም አበዳሪዎች ጋር በሚኖር ግንኙነት ላይ #ወጥነት እና #እኩልነትን ለማረጋገጥ ያስፈልጋል።
የብድር እፎይታ ....
* ኢትዮጵያ ላለባት ብድር #የብድር_እፎይታ ለማግኘት በ " ቡድን 20 " የጋራ ማዕቀፍ በኩል የዕዳ ሽግሽግ ለማድረግ ውይይት ስታካሂድ ቆይታ ነበር።
* ባለፈው ኅዳር ወር በቻይናና በፈረንሳይ በሚመራው የፓሪስ ክለብ አማካኝነት የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
* በዚህ ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ለአበዳሪዎቿ መክፈል የሚጠበቅባትን ብድር እና ወለድ 2 ዓመት ገደማ አትከፍልም።
* ይህ የዕዳ ክፍያ ሽግሽግ በየዓመቱ የሚከፈለውን 1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዕዳ በጊዜያዊነት የሚያስቀር ነው።
ኢትዮጵያ የዚህን አይነቱን ስምምነት የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንዱን ከገዙ የግል ባለሀብቶች ጋርም ለመፈጸም ትፈልጋለች።
የዋናው ብድር የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘምና በየዓመቱ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔው ከ6.625 በመቶ ወደ 5.5 በመቶ ዝቅ ማድረግ ሀሳብ አላት።
መንግሥት የብድር አከፋፈሉ ላይ ማስተካከያ ማድረግ የፈለገው ከሌሎች አገራት ጋር በሚያደርገው የብድር ሽግሽግ ላይ አበዳሪዎችን በተመሳሳይ መልኩ ማስተናገድን በተመለከተ ስጋት እንዳይነሳ በማሰብ መሆኑን አሳውቋል።
መንግሥት የብድር አከፋፈል ማስተካከያው ላይ ከቦንዱ ገዢዎች ጋር በተቻለ ፍጥነት ስምምነት ላይ መድረስ ጠንካራ ፍላጎት አለው።
የቦንዱ ገዢዎች ጋር ያለው ስሜት ምንድነው ?
° ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለዱን በቀኑ እንደማትከፍል ማስታወቋ በቦንዱ ገዢዎች ዘንድ በመልካም አልተወሰደም።
° የቦንዱ ገዢዎች ኮሚቴ የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ አላስፈላጊ እና አሳዛኝ አድርጎ እንደሚመለከተው ገልጿል።
° የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔውን የማያጥፍም ከሆነ ከፍ ያለ ዳፋ ይኖረዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ባለፈው #ሰኞ መክፈል የነበረባትን ወለድ ለቦንድ ገዢዎች ለማስተላለፍ የ14 ቀናት የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቷታል።
በእነዚህ በተሰጡ ቀናት ውስጥ ወለዱን የማትከፍል ከሆነ ውልን አለማክበር (#technical_default) እንደሚገጥማት የዘርፉ ባለሞያዎች ተናግረዋል።
" ፊች " የተሰኘው የአገራትን ብድር የመክፈል አቅም ደረጃ የሚያወጣ አሜሪካ ተቋም ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ ዕዳ የመክፈል ደረጃ ከነበረበት " ሲሲ " (CC) ደረጃ ወደ " ሲ " (C) ዝቅ ማድረጉን አስታውቋል።
ተቋሙ ለዚህ ደረጃ ምደባ የጠቀሰው አንዱ ምክንያት ኢትዮጵያ የቦንዱን ወለድ በቀኑ አለመክፈሏል ነው ያለ ሲሆን በ14 ቀናት ውስጥ ክፍያው ካልተፈጸመ ይህንን ደረጃ በድጋሚ ዝቅ እንደሚያደርገው ገልጿል።
Credit - BBC AMAHRIC / REUTERS
@tikvahethiopia