TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፤ በ2014 ዓ.ም እና 2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ውጤት ያመጡ እና በፖሊስ የሙያ ዘርፍ ሀገራቸውን ለማገልገል #የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ተቋሙ ለ4  አመታት በ " ፖሊስ ሳይንስ ዲግሪ " አስተምሮ በመኮንንነት (ረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ) በማስመረቅ በተለያዩ የፌደራል ፖሊስ የስራ ክፍሎች አስመድቦ ለማሰራት እንደሚፈልግ ነው የገለፀው።

በተጨማሪ በ "ፎረንሲክ ሳይንስ ዲግሪ" አስተምሮ በመኮንንነት (ረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ) በማስመረቅ በፎረሲክ ምርመራ የላብራቶሪ ሙያተኝነት (ኤክስፐርት) በማስመደብ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በተቋሙ በ  " ፖሊስ ሳይንስ ዲግሪ " ለመማር የሚያስፈልጉ የመመልመያ መስፈርቶች ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩ ሲሆን ከነሱም ውስጥ ፦

- አመልካቾች ከማንኛውም ወንጀል ነፃ ስለ መሆኑ ከሚኖርበት ወረዳ ፖሊስ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።

- ለፖሊስ አካል ብቃት ስልጠና ብቁ የሆነ አካላዊ አቋምና አዕምሮ ጤንነት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።

- በ2014 ዓ/ም እና 2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር መቁረጫ ውጤት ያላቸው  የትምህርት ማስረጃቸውንም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

- የ #ሪሚዳል_ትምህርት ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ከሆነም ማስረጃ ማቅረብ አባቸው።

- አመልካቾች እድሜያቸው ከ18 እስከ 28 ዓመት መሆን አለበት።

- ቁመት ለወንድ 1.65 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 1.55 እና ከዚያ በላይ፣
ሲሆን የተስተካከለ የሰውነት ክብደት 18.5-24.9 kg/m) ያለቸው ሊሆኑ ይገባል።

- ከተመረቁ በኋላ 7/ሰባት/ አመት በተማረበት የፖሊስ ሙያ በየትኛውም የአገሪቱ ክልልና የፖሊስ የስራ መደቦች ላይ ተመድቦ ለመስራት ፍቃደኛ መሆን አለበት።

- ሴት አመለካቾች ከእርግዝና ነፃ መሆን አለባቸው።

- ሁሉም አመልካቾች ከዚህ በፊት የፖሊስ ወይም የመከላከያ ሰራዊት ስልጠና ያልወሰዱ መሆን ያለባቸው ሊሆኑ ይገባል።

ለ " ፎረንሲክ ሳይንስ ዲግሪ " ከላይ ያሉት አብዛኛው መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው ፦
- ዜግነት #ኢትዮጵያዊ
- የ12ኛ ክፍል #በተፈጥሮ_ሳይንስ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በ2014 ዓ/ም እና በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መቁረጫ ውጤት ያላቸው
- በተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዳል ትምህርት ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሊሆኑ ይገባል።

በሁለቱም የዲግሪ ትምህርት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን የሚቀላቀሉት በራሱ በተቋሙ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ ሲችሉ ብቻ ነው።

የት እና እስከመቼ መመዝገብ ይቻላል ?

ማመልከት የሚቻለው እስከ ጥቅምት 22/2016 ዓ/ም ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ነው።

ተማሪዎች በአካባቢያቸው በሚገኝ በሁሉም የክልል እና የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች በአካል በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ።

ለመዝገባው የትምህርት ማስረጃቸውን የ8ኛ ፣ የ10ኛና 12ኛ ክፍል ካርድ እና ትራንስክርፕት ኦርጅናል ከማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ይዘው መቅረብ አለባቸው።

#ደመወዝ / #ክፍያን በተመለከተ

ዕጩ መኮንኖች በትምህርት ላይ በሚቆዩበት ጊዜያት ከ3 ወር የሙከራ (recruit) ጊዜ ቆይታ በኋላ እስከሚመረቁ ድረስ የኪስ ገንዘብ/ደመወዝ ታስቦ ይከፈላቸዋል ተብሏል።

ስልክ ካስፈለጋችሁ ፡ 0116735564

(ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ከላይ በምስሉ ያንብቡ)

@tikvahethiopia