TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አባታዊ የሰላም ጥሪ "

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበር ተክለሃይማኖት ሰሞኑን በተለይ በጎንደርና አካባቢው ፤ በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን አካባቢ በተፈጠረው አለመረጋጋት እና የሰው ህይወት መውደቅ እጅግ ማዘናቸውን ገልፀዋል።

አባታዊ የሰላም ጥሪም አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ፦

" ከእልቂት የሚያተርፈው ፀላዔ ሠናያት የሆነው ዲያብሎስ ብቻ ነው።

እሳትን በእሳት ማጥፋት አይቻልምና ስንናገር ስንራመድ ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲኖረን በብርቱ እማፀናለሁ።

ይህም ጠብና እልቂት የሞራል ውድቀት ፣ የኃጢያት አውራ ተብሎ ከመመዝገብ ውጭ ስምና ታሪክ አይሆነንምና ሁላችንም ለሰላም እንድንቆም እለምናለሁ።

የእኛን ድጋፍ የሚፈልጉ በሰሜን ፣ በምስራቅ ፣ በምዕራብ ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ብዙ ወገኖች ሳሉ ሌላ ችግር በመጨመር አገርን ወደ አዘቅት መስደድ ፍፁም የተወገዘ ግብር ነው።

በሞቱት ወገኖች እጅግ አዝናለሁ።

አብያተ እምነትም የሰው ልጆች የምስጋና የነፍስ መማፀኛ ናቸው እንጂ የእሳት ግብር የሚሰጣቸው አይደሉምና ይህንን ድርጊት ተገቢ አለመሆኑን እገልፃለሁ።

እርስ በእርስ በመጣላት ላይ ሀገርም እያፈረስን ነው። ተጣልቶ ለመታረቅም ሀገር ያስፈልገናልና ሀገራችንን ልንሳሳላት ይገባናል።

ሁላችንም #ለሰላም_እንድንቆም ፤ መንግስትም ከሰው እና ከእግዚአብሔር የተቀበለውን አደራ ፈጥኖ እንዲያስፈፅም ፣ የሃይማኖት አባቶችም ትውልድን የማነጽ ተግባራቸውን በርትተው እንዲቀጥሉ አደራ ጭምር ጠይቃለሁ። " ብለዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia