TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትናንት ከሌሊቱ 6 ሠዓት በደረሰ የእሳት አደጋ ንብረት መውደሙን የእሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

አደጋው በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ራስ ደስታ አከባቢ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ ስፖንጅ ፋብሪካ ውስጥ የደረሰ ነው።

በአደጋው ከ500 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ማውደሙን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

አደጋውን ለመቆጣጠር 62 የአደጋ ሠራተኞች እና 12 ተሽከርካሪዎች ተሰማርተው በተደረገው ርብርብ 25 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ ተችሏል።

የእሣት አደጋው መንስኤ አልታወቀም።

PHOTO : TIKVAH FAMILY (AB)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ስፖርት ተቋማት ከፌደራል ስፖርት ተቋማት ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችሉም የሚል ብዥታ ፈጥሮ የነበረ የውሳኔ ደብዳቤ መሻሩን የEthioFM 107.8 ጋዜጠኛ ታደለ አሰፋ አሳውቋል።

ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን በቀን 9/2/2013 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ "የመረጃ ክፍተት" ያለው በመሆኑ ተሽሯል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚቀመጡ የአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ትምህርት ይጀምራሉ።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ዘላለም ፤ ኮቪድ-19 ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራታቸው የመልቀቂያ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ቀድመው ትምህርት ይጀምራሉ ብለዋል።

የፊታችን ሰኞ ትምህርት የሚጀመርባቸው ትምህርት ቤቶች ላይ የፀረ ተዋህሲ ርጭት መካሄዱ እና የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል።

የሙቀት መለኪያ እና ጭምብል በሁሉም ትምህርት ቤቶች በመሰራጨት ላይ መሆኑም ተገልጿል።

የ8ኛ እና 12 ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች 45 ቀን ከተማሩ በኋላ ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማና በዙሪያዋ ያሉ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ትምህርት የሚጀምሩት ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ/ም እንደሆነም የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።

ቢሮው እንዳስታወቀው ቅዳሜ የትምህርት ቀን እንደሚሆንና አንድ ተማሪ በሳምንት ሶስት (3) ቀን ትምህርት መማር ይጠበቅበታል። (etv)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ONLF

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ሶስት (3) ከፍተኛ አመራሮቹ መታሰራቸውን የፓርቲው ቃለ አቀባይ የሆኑት አብዱልከድር ሀሰን ኢርሞጌ አዳኒ ለBBC ሶማሊኛ ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት ፦

- መሃመድ ጂግሬ ገመዲድ (የቆራሄ ዞን ሊቀመንበር)
- ተማም መሃመድ ማህሙድ (የቆራሄ ዞን ም/ሊቀመንበር)
- መሃመድ ኢብራሂም ሙርሳል (የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና ለረዥም አመታት በስራ አስፈፃሚነት የሰሩ) ናቸው።

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ኡመር ፋሩቅ ወርፋም ለቢቢሲ ሶማሊኛ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸው አረጋግጠዋል።

ኦብነግ ፣ ከክልሉ መንግሥት እና ከፌደራል መንግሥት ጋር ውይይቶች እየተካሄዱ መሆኑን ገልጿል ፤ ችግሩ በድርድር እንደሚፈታም ተስፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

More : telegra.ph/ONLF-10-22

Via BBC
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#PASSPORT

በOnline ላይ ፖስፖርት ለማደስና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት ጥቅምት 11 ይጀምራል ቢባልም ዛሬም ድረስ አልተጀመረም።

ውድ የቲክቫህ አባላት የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የኦንላይን (online) አገልግሎቱ የሚሰጥበት 'ሊንክ' ይፋ ሲያደርግ ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጉራ ፈርዳ ወረዳ 12 ሰዎች ተገደሉ ! ጥቅምት 8/2013 ምሽት 3:00 ገደማ ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ "ማንነታቸው ያልታወቀ" የተደራጁ ወንጀለኞች ባደረሱት ጉዳት የ12 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ እና በ5 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነብዩ ኢሳያስ አሳውቀዋል። ኮሚሽነር ነብዩ፥ የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ተጨማሪ የፀጥታ አካላት ወደ አካባቢው…
በጉራ ፈርዳ ወረዳ ከሰኞው የቀጠለ ጥቃት ተፈፅሞ ሰዎች መገደላቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

ከሁለት ቤት ውስጥ ብቻ ከ10 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏል ብለዋል አባላቶቻችን።

ዛሬ ጥቅምት 12/2013 ዓ/ም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ለእርዳታ ከመጡ 12 ሰዎች መካከል 6ቱ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናት መሆናቸውን የቲክቫህ አባል የሆነ ሀኪም ገልጿል።

መልዕክታቸውን ያደረሱ የአካባቢው ቲክቫህ አባላት፥ ፓሊስ "ማንነታቸው ያልታወቁ" ይላል ይህ ትክክል አይደለም ጥቃት ፈፃሚዎቹ በግልፅ የሚታወቁ ናቸው ብለዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር በጉራ ፈርዳ ወረዳ ውስጥ ከጥቅምት ስምንቱ ምሽት ጥቃት በተጨማሪ ትላንት ረቡዕ በድጋሚ ጥቃት ስለመፈፀሙ ለአሀዱ ሬድዮ አረጋግጧል።

የፀጥታ መዋቅሩ የጥቅምት ስምንቱን ችግር እያረጋጋ ባለበት ወቅት ነው ትላንት በተመሳሳይ ወረዳ ጊኒቃ በምትባል ቀበሌ በድጋሚ ጥቃት መፈጸሙን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ያረጋገጡት።

ከታጠቁ አጥፊ ሃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 16 ግለሰቦች እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ውለዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው። የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ 500 ግለሰቦች ከአከባቢው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡

ጥቃት ፈፃሚዎች እነማን ናቸው ? በምን ምክንያት ጥቃቱን ፈፀሙ የሚለው ጉዳይ ገና በመጣራት ላይ እንዳለ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

አስተዳደሩ ስለትላንቱ ጥቃት መጠን አልገለፀም።

(Ahadu Radio,Tikvah Family GuraFerda)

PHOTO : TIKVAH FAMILY (GuraFerda)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በህብር ጣናን እንታደግ"

ጥቅምት 9/2013 ዓ/ም የጀመረው የአንድ (1) ወር የእምቦጭ አረምን ከጣና ሐይቅ የማስወገድ ሀጋራዊ ዘመቻ አራተኛ ቀኑን ይዟል፡፡

ዘመቻው ከሚከናወንባቸው 30 ቀበሌዎች መካከል 20 ቀበሌዎች ላይ እስካሁን አረሙን የማስወገድ ዘመቻው ሙሉ በሙሉ ተጀምሯል፡፡

እንቦጭ አረምን በማስወገድ ዘመቻው ሌሎችን በጎ ፈቃደኞች ሳይጨምር በአማካይ በቀን 400 አርሶ አደሮች በ1 ቀበሌ እንደሚሰማሩ የዘመቻ እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ሥራው ሲጀመር ግን በአንድ ቀበሌ ከታቀደው በላይ አርሶ አደሮች በዘመቻው ተሳታፊ መሆናቸውን ተገልጿል።

Via Amhara Communication
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጉራ ፈርዳ ወረዳ ከሰኞው የቀጠለ ጥቃት ተፈፅሞ ሰዎች መገደላቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል። ከሁለት ቤት ውስጥ ብቻ ከ10 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏል ብለዋል አባላቶቻችን። ዛሬ ጥቅምት 12/2013 ዓ/ም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ለእርዳታ ከመጡ 12 ሰዎች መካከል 6ቱ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናት መሆናቸውን የቲክቫህ አባል የሆነ ሀኪም ገልጿል። መልዕክታቸውን…
#UPDATE

በ2 ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት አልፏል !

በጉራፈርዳ ወረዳ በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንድ የፖሊስ አባልና አራት አመራሮች እንደሚገኙበት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው ጥቅምት 8 እና ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለት ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና 5 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

1 ሺህ 480 አባወራዎች ተፈናቅለው በቢፍቱ ከተማ የተጠለሉ ሲሆን ጊዜያዊ እርዳታ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ (FBC)

PHOTO : TIKVAH FAMILY (GuraFerda)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,676
• በቫይረሱ የተያዙ - 575
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 754

በአጠቃላይ በሀገራችን 91,693 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,396 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 45,260 ከበሽታው አገግመዋል።

306 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ ጥቅምት 12 የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ መግለጫ አውጥቷል።

ቢሮው በመግለጫው ፦

- የፌዴራሉ መንግስት የትግራይ ህዝብ ድርሻ የሆነውን የድጎማ በጀት መከልከሉ ባስታወቀበት ማግስት ፣ ከበረሃ አንበጣ መንጋ ጋር እየተናነቀ ያለውን የትግራይ ህዝብ ዓመት ሙሉ የለፋበት ቡቃያ የአንበጣ ሲሳይ እንዲሆን በይኖበታል ብሏል።

- ጸረ-አንበጣ መድሓኒት በአውሮፕላን እንደረጨ የሃሰት መረጃ አስተላልፏል ሲል ወቅሷል።

- ከዓለም ኣቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም ለጋሽ አገሮች ለገበሬዎች ሲሰጥ የቆየውን የሴፍቲኔት ፕሮግራም ማለት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ወራት መላክ የነበረበት 285 ሚልዮን ብር እንደከለከለ ጥቅምት 10/2013 ዓ/ም በይፋ ኣሳውቀዋል ሲል ገልጿል፡፡

- የመቐለ ከተማ የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ፣ ገረብ ግባ ግድብ ፕሮጀክት ኩንትራት ወስዶ እየሰራ ያለውን የቻይና ኩባንያ (CHAINA GEZHOUBA GROUP COMPANY LIMITED) የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት 2 ዲዛይነሮች ከቻይና ተነስተው በትራንዚት ወደ መቐለ ከተማ እንዳይመጡ ጥቅምት 12/2013 ዓ/ም ቦሌ ዓለምኣቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ አግቶ አስቀርታቸዋል ብሏል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የገንዘብ ሚኒስቴር ለትግራይ ወረዳ ፣ ከተማና ቀበሌ የድጎማ በጀት የሚተላለፍበት አሠራር ዝግጅት አጠናቅቂያለሁ አለ።

በሚኒስቴሩ የተዘጋጀው የበጀት ድጎማ አሠራር በሚቀጥለው ሣምንት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል።

በዚህም በጀቱ በወረዳ፣ ከተማና ቀበሌ አስተዳደር አካላት የባንክ ሂሳብ በኩል እንደሚተላለፍ ተገልጿል።

አስተዳደር አካላቱ የባንክ ሂሳብ ማስተላለፊያ ደብተር ካላቸው በዚያው በኩል ከሌላቸው ደግሞ አዲስ የባንክ ሂሳብ በመክፈት በጀቱ እንዲደርሳቸው ይደረጋል ነው የተባለው።

ሚኒስቴሩ የትግራይ ሕዝብ እንደ ሌሎቹ የአገሪቱ ክልል ሕዝቦች የትምህርት ፣ የጤና ፣ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፣ የምግብ ዋስትና እንዲሁም ሌሎች መሠረታዊ የሆኑ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል ብሏል። (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEBE

የ6ኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን አስመልክቶ ፓለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ለምርጫው የተዘጋጁ ቁሳቁሶችን በኤግዚቢሽን ማዕከል እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡

በዛሬው ዕለት የፓርቲዎች ማዕከል ቢሮ ቁልፍ ርክክብ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዚህ ቀደም የሚዲያ አካላት ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

PHOTO : TIKVAH FAMILY (A.A)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia