TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሶማሊያ በኢትዮጵያ ያሉትን አምባሳደሯን መጥራቷን ተከትሎ አምባሳደር አብዱላሂ ዋርፋ ወደ #ሞቃዲሾ ማቅናታቸው ተሰምቷል። በሌላ በኩል ደግሞ ፤ የሶማሊያ ሁለቱ የፌደራል ፓርላማ ምክር ቤቶች በአሁን ሰዓት አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ላይ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል። ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ የወደብ እና…
#Somalia #Somaliland
" የሶማሊያ ደካማ መንግስት ይሄን ታሪካዊ ስምምነት ለማስቆም ምንም አይነት ሕጋዊነት የለውም " - አብዱላሂ አርሼ (የሶማሊላንድ ባለስልጣን)
የቀድሞ የሶማሊላንድ " የሀገር ውስጥ " ሚኒስትር አማካሪ እና በአሁን ሰዓት በሶማሌላንድ " የሀገር ውስጥ " ሚኒስቴር የሚዲያ እና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አብዱላሂ አርሼ የሶማሊያን መንግሥት " ደካማ መንግሥት " ሲሉ ጠርተው በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ ሪፐብሊክ መካከል የተፈረመውን #ታሪካዊ_ስምምነት ለማስቆም ምንም አይነት ሕጋዊነት የለውም ብለዋል።
" የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና የሰጠው የሶማሊያ ስርዓት እንደ ወቀደ መንግስት ነው፣ ሞቃዲሾ ውስጥ የአስተዳደር ስርዓት የለም። " ሲሉ ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል።
ኢስማኤል ሺርዋክ የተባሉ የሶማሊላንድ ዲፕሎማት ደግሞ ፤ " ሀገራችን አንድ እርምጃ ወደፊት ስትሄድ ሶማሊያ በታሪክ ግልፅ የሆነ ጥላቻ አሳይታለች። " ያሉ ሲሆን " ሶማሌላንድ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (#UAE) ስምምነት ላይ ሲደርሱ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል፣ ነገር ግን ምንም አይነት ውጤት አላመጣም። " ብለዋል።
" እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር የዜጎቻችንን ጥቅም መሰረት አድርገን የሚያስፈልገውን እንወስናል " ሲሉ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ለሁለቱ የፌዴራል ም/ቤት አባላት ንግግር ማድረጋቸው የተሰማ ሲሆን የሶማሊላንድ እና የኢትዮጵያን የትብብር ስምምነት ሰነድ ተቃውመዋል።
" አንድም ኢንች የሶማሊያ ግዛት በማንም ሊፈረም አይችልም ፤ሉዓላዊነታችንንና የግዛት አንድነታችንን እንጠብቃለን ፤ በዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት እናስከብራለን፤ እያንዳንዱን ኢንች መሬት እንጠብቃለን፤ ሶማሊያ የሶማሊያውያን ነች ፤ ይሄ የመጨረሻው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" አቶ መለስ ዜናዊ በሶማሊያ ውስጥ የገቡት ጣልቃ ገብነት የአልሸባብን መነሳት አስከትሏል " ሲሉ የተደመጡት ፕሬዜዳንቱ " የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እርምጃም ያሸነፍነውን አልሸባብ ዳግም እንዲነሳሳ ሌላ ዕድል የሚሰጥ ነው " ብለዋል።
" የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጥር 1 ከያዙት መንገድ እንዲመለሱ " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ያላቸው አማራጭ አንድ ብቻ ነው እሱም በሰላም መኖር ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
የሶማሊንላንድ ባለልስጣናት ስምምነቱን የደገፉ ሲሆን በሶማሊያ ባለስልጣናት ላይም ጠንክራ ትችት እየሰነዘሩ ይገኛሉ። ስምምነቱን የማስቆም ምንም አይነት አቅም የላቸውም ሲሉ እየተደመጡ ናቸው።
@tikvahethiopia