TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Ministry of Agriculture ~ #አረንጓዴ_አሻራ
ቤንሻንጉል #አረንጓዴ_አሻራ
CBE Jimma District be Jimma Kito Furdissa #አረንጓዴ_አሻራ
የአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ #አረንጓዴ_አሻራ
#አረንጓዴ_አሻራ በሀገር ደረጃ እስካሁን በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን 232 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን ያስታወቁት በወላይታ ሶዶ ከተማ ከአካባቢው የህብረተስብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ባሉበት ወቅት ነው።

#አሁን በደረሰን መረጃ በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ በኦሮሚያ 132 ሚሊዮን ፣ በደቡብ 45 ሚሊዮን፣ በትግራይ ስምንት ሚሊዮን 400ሺህ አማራ 38ሚሊዮን እና አዲስ አባባ ከሶስት ሚሊዮን በላይ የተከናወኑ ይገኙበታል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ዛሬ ጥዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ለመትከል የታቀደው 200 ሚሊዮን ቢሆንም እስካሁን የተከናወነው ከዚህ በላይ መድረሱን ነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ለማወቅ የተቻለው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ #ከፍተኛ_ጥንቃቄ_ይደረግ

ፌስታሉን ካልሰበሰብነዉና ካላነሳነዉ ሌላ ዘመቻ ያስፈልገናል 200 ሚሊዮን ፌስታል ለመልቀም ~ የሚተክል ያስተዉል፤ ጉዳዩ ጥንቃቄ ያሻዋል!!

#ሼር #share

Via #ዝንቅ
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ

23 ሚሊዮን የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን በዛሬው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ላይ አሻራቸውን አሳርፈዋል። የችግኝ ተከላው አስተባባሪ ኮሚቴ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ በተከላው 23 ሚሊዮን የሚገመት የተለያየ የህብረተሰብ ክፍል ተሳትፏል ብሏል። በዛሬው ዕለትም ከ353 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ችግኝ መተከሉን አስተባባሪ ኮሚቴው ገልጿል።

ዕለቱ ህዝቡ የመሪውን ጥሪ ወደ ተግባር ለመቀየር ቀና አመለካከት እንዳለው ያሳየበት መሆኑም ነው በመግለጫው የተነገረው። የችግኝ ተከላው ከልጅ እስከ አዋቂ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና የውጭ አገራት ኤምባሲ ሰራተኞች ጭምር የተሳተፉበት ነው።

በእያንዳንዱ የችግኝ ተከላ ቦታ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ መደረጉም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንዲተከል እገዛ ማድረጉ ተገልጿል። ዝናብ፣ ጭቃና የቦታ ርቀት እንዲሁም የችግኝ እጥረት በዛሬው ዕለት ያጋጠሙ ችግሮች ሲሆኑ በአጭር ጊዜ ለመፍታት በተወሰደ መፍትሔ ከታሰበው በላይ ማሳካት ተችሏል ነው የተባለው።

Via #ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በትላንትናው ዕለት የአረንጓዴ አሻራ ቀን የተመዘገበውን ስኬት አስመልክተው ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ኅብረተሰቡ በዕለቱ ለመከወን የተያዘውን እቅድ በማለፍ ላስገኘው አመርቂ ውጤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማም የመዲናዋ ነዋሪዎች በትላንትናው ዕለት የአረንጓዴ አሻራ እለት ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ ከትናንት በስቲያ በተካሄደው አገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በየክልሉ የተተከሉትን ችግኞች ብዛት የሚያሳይ ካርታ፡-