TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያት የከዱ (የኮበለሉ) አባላት እና የፖሊስ አመራሮች መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን #ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጁ መሰረት እስከ ግንቦት 30/2010 ዓመተ ምህረት ድረስ ከሰራዊቱ የከዱ አባላትና አመራሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

የኮበለሉት የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ከነሀሴ መጨረሻ ጀምሮ በመጪዎቹ ስድስት ወራት በምህረት አዋጁ መሰረት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በኮሚሽኑ የህግ ጉዳይ ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር #ፋሲል_አሻግሬ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ በከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ በፌደራል ፖሊስ ዋናው መስሪያ ቤት እንዲሁም በወንጀል መከላከል ዘርፍ ዳይሬክቶሬቶች በመገኘት ሪፖርት ማድረግ የሚችሉ ሲሆን፥ በክልል የሚገኙት ደግሞ ለክልላቸው ፍትህ ቢሮ ሪፖርት በማድረግ በምህረቱ ተጠቃሚ መሆኑን እንደሚችሉ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ አባላት እና አመራሮች ከዚህ ቀደም የወሰዱትን ደብዳቤ ተመላሽ በማድረግ በምትኩ ሌላ የስንብት ደብዳቤና የስራ ልምድ ማግኘት እንደሚችሉ ታውቋል።

የምህረቱ ተጠቃሚ የሆኑ አባላት የወሰዱትን የመንግስት ንብረት ሪፖርት ለሚያደርጉበት ተቋም በመመለስ የነጻነት የምስክር ወረቀት መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።

ሆኖም በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ ፖሊሶች ወደ ስራ ቦታ እንደማይመለሱ የስራ አመራር ውሳኔ እንዳሳለፈ ኮማንደር ፋሲል አሻግሬ አስታውቀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahehiopia