TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሊታረም ይገባል‼️ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት ስፍራ ናቸው። ለሀገር ለውጥ ትልቁን ድርሻ በሚወስዱት ተቋማት ውስጥ ሆኖ #ዱላ መያዝ እና #ድንጋይ መወራወር ብሎም እርስ በእርስ መጋጨት ተገቢ አይደለም።

ይታረም‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዝነናል!! ድጋሚ ይህን #ዱላ በተማሪዎች እጅ ላይ እናያለን ብለን አልጠበቅንም። ችግር እንኳን ቢኖር በንግግር መፍታት እየተቻለ በዚህ በሰለጠነ ዘመን ዱላን እንደመፍትሄ ሲውሰድ ማየት ያሳዝናል።

የድሀዋ ሀገራችን ልጆቿ እናተው ናችሁ፤ ተዋደዱላት እንጂ በፍፁም #አትጣሉባት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትላንት በለገጣፎ ለገዳዲ ምን ሆነ

ሰሞኑን በለገጣፎ ለገዳዲ የከተማው አስተዳደር ህገ ወጥ ናቸው ባላቸው የመኖሪያ ቤቶች ላይ የማፍረስ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም ሚዲያዎች ወደአካባቢው በመሄድ ሁኔታው ሲዘግቡት ነበር።

በትላንትናው ዕለት የmereja.com ጋዜጠኛ እና የካሜራ ባለሞያ ሁኔታውን ለመዘገብ ወደ ለገጣፎ ለገዳዲ አምርተው #አሳዛኝ ክስተት ገጥሟቸው ተመልሰዋል።

የተፈጠረውን ክስተት በዝርዝር ለማስረዳት፦

Mereja.com ባልደረባ የሆኑ አንድ ጋዜጠኛ(ጋዜጠኛ ፋሲል) እና አንድ የካሜራ ባለሞያ በለገጣፎ ለገዳዲ የተወሰደውን እርምጃ ለመዘገብ ወደ አካባቢው ይሄዳሉ። ስራቸውን እንዳጠናቀቁም ፖሊስ ይመጣና መታወቂያ ይጠይቃቸዋል፤ ጋዜጠኛው እንዲሁም የካሜራ ባለሞያ በፖሊስ በተጠየቁት መሰረት መታወቂያቸውን ይሰጣሉ። ፖሊስም መታወቂያቸውን ኮፒ አድርጎ ይመልስላቸዋል። ከዚህ በኃላ ፖሊስ ስራውን ያለፍቃድ መስራት እንደማችሉ ይነግራቸዋል፤ ፖሊስ ረዘም ያለንግግር ከጋዜጠኛ ፋሲል ጋር ያደርጋል በመጨረሻም መግባባት ላይ ይደረስና የተያዘባቸው እቃ ተመልሶ እንዲሄዱ ይፈቀድላቸዋል።

ጋዜጠኛ ፋሲል እና የካሜራ ባለሞያው ጉዞያቸውን ወደአዲስ አበባ ለማድረግ ታክሲ ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ቁጥራቸው ከ10-15 የሚደርሱ #ገጀራ እና #ዱላ የያዙ ወጣቶች በጋዜጠኛ ፋሲል ላይ ደብደባ መፈፀም ይጀምራሉ። ይህ በሚሆንበት ሰዓት የካሜራ ባለሞያው ራሱ ለማዳን ከአካባቢው ለመሰወር ችሏል።

አስገራሚው ነገር ወጣቶቹ በጋዜጠኛ ፋሲል ላይ #ድብደባ የፈፀሙት #ከፖሊስ_ጣቢያ ፊት ለፊት መሆኑ ነው። ፖሊስ በመሃል ገብቶ ከመገላገል ውጭ፤ ወጣቶቹ ለምን ድብደባ እንደፈፁሙ እንኳን ይዞ #አልጠየቃቸውም። የተደራጁት ወጣቶች ከአካባቢው ከሄዱ በኃላ ጋዜጠኛ #ፋሲል በግለሰብ መኪና ወደጤና ተቋም እንዲሄድ ይደረጋል በወቅቱ ምንም አይነት የፀጥታ ሀይል አብሮት አልሄደም።

በጋዜጠኛ ፋሲል ላይ በደረሰው ድብደባ በጭንቅላቱ ላይ 2 ቦታ የመሰንጠቅ አደጋ ደርሷል እዲሁም ከፍተኛ ደም ፈሷል፤ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታልም ሪፈር ተብሎ የሄደ ሲሆን የደረሰበት አደጋ ከፍተኛ ቢሆንም በቤቱ ተኝቶ ህክምናውን መከታተል እንደሚችል ተነግሮ ወደቤቱ ተመልሷል።

ምንጭ፦ ወ/ሮ ፍሬዘር ነጋሽ(የmerej.com ስራ አስኪያጅ) - ለTIKVAH-ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia