TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ትላንት ማምሻውን ለፕሬዝዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ ፕሬዚዳንቱ በንግግራችው አዲስ አበባ #የኬንያኖችም የሁሉም ከተማ መሆንውን ገልጸዋል። በተያያዥነትም የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት #እንደሚደግፉ ገልጸው የኬንያ ባለሀብቶች በገበታ ለሸገር ከጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና #ኢትዮጵያዊያን ጎን እንደሚቆሙ #ቃል_ገብተዋል

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikbahethiopia
"ኢትዮጵያን #የሚያጠፏት እኔ አውቅላችኃለሁ ባዮች ናቸው" ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ
.
.
የአሁኑ ትውልድ ራሱን ከጥላቻ ንግግሮች በማራቅ በአንድነት፤ በፍቅር ኢትዮጵያን እንዲገነባ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰሩ ጥሪውን ያቀረቡት TIKVAH-ETH በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው #StopHateSpeech/የፀረ ጥላቻ ንግግር/ ዘመቻ መድረክ ላይ ነው።

ወጣትነት ማለት ያልተለኮሰ ሻማ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ደጀኔ -- ሰይጣን ሲለኩሰው የጥፋት እና የውድመት ኃይል ይሆናል፤ በመልካምነት እና በበጎነት ሲለኮስ ደግሞ ሀገር ይገነባል፤ ሀገር ይታደጋል ብለዋል። አክለውም ሁሉም ወጣት የእርስ በእርስ ግጭት ተፈጥሮባቸው ከነበሩት ሀገራት #በመማር ከጥላቻ ንግግሮች በመቆጠብ፤ በሰላም በፍቅር እና በአንድነት ለኢትዮጵያ እንዲሰራ ሀገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ፕሮፌሰር ደጀኔ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላትን ያመሰገኑ ሲሆን ለሰላም እና ለፍቅር የሚደረገውን ጉዞ #እንደሚደግፉ ገልፀዋል፤ በ#StopHateSpeech ጉዞ ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶችንም ያበረታቱ ሲሆን "ነገ ታሪክ ያስታውሳችኃል ጉዟቹን ቀጥሉ ሁሉም ከእናተ ዘንድ ይሰለፋል" ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia