TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢትዮ ቴሌኮም⬇️

‹‹ከሁለት የስልክ ቀፎዎች በላይ ወደ ሀገር #ማስገባት አይቻልም የሚለው ገደብ ተነስቷል፡፡››
.
.
ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡም ሆነ ከሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ የስልክ ቀፎዎችን ለማስከፈት ወደ ጉምሩክ እና ኢትዮ ቴሌኮም መስሪያ ቤቶች መሄድ እንደማያስፈልግ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

የስልክ ቀፎዎች አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት በኢትዮ ቴሌኮም እና በጉምሩክ በኩል ህጋዊነታቸው እንዲረጋገጥ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ዓላማውም ህገ ወጥነትን ለመከላከል ተብሎ እንደ ነበር ይታወቃል፡፡ አሰራሩም ወጥነት የሌለው፣ክፍተቶች ያሉበት እና ደንበኞችን ከማጉላላት ባለፈ የጎላ ፋይዳ ያልታየበት መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ ለአብመድ ተናግረዋል።

ከሁለት የስልክ ቀፎዎች በላይ ወደ ሀገር ማስገባት እንደማይቻል የሚከለክለው እገዳም ተነስቷል ነው ያሉት አቶ አብዱራሂም፡፡ በመሆኑም IMI ቁጥር ያላቸውን ማለትም ደረጃውን የሚያሟሉ የስልክ ቀፎዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ መገልገል እንደሚቻል አረጋግጠዋል፡፡

በመሆኑም ወደየተቋማቱ መሄድ ሳያስፈልግ አዳዲስ የስልክ ቀፎዎችን #መገልገል ይቻላል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በዘርፉ የሚስተዋሉ የኮንትሮባንድ እና የቴሌኮም ማጭበርበርን ለመግታትም ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎች ተግባራዊ ያደርጋል
ነው ያሉት፡፡ እንደ አቶ አብዱራሂም መረጃ የታሪፍ ቅናሽ አና የስልክ ቀፎዎችን አለማስመዝገብ ከትናንት ነሀሴ 17/12/10 ዓ.ም ጀምሮ #ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ~የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ🔝

ከነገ በስቲያ/ሀሙስ የካቲት 14/2011 ዓ.ም. የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሀዋሳ ከተማ የጠራው #ሰላማዊ_ሰልፍ በመንግስት ፍቃድ አግኝቷል።

ሰልፉ ህዝበ ውሳኔ #ተግባራዊ እንዲሆን የሚጠይቅ ሲሆን በሰልፉ ላይ ከሲዳማ የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ #ተሳታፊዎች ይካፈሉበታል ተብሏል። የሰልፉ ተሳታፊዎችም ህገ መንግስታዊ መብታቸው እንዲከበር ድምፃቸውን ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበት ሰዓት፦
ከጥዋት 1 ሰዓት እስከ ቀን 6 ሰዓት

ሰላማዊ ሰልፉ የሚያካልላቸው የከተማይቱ ቦታዎች፦

•መነሻው፦ ሀዋሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
•ሲዳማ ዞን አስተዳደር
•አሮጌው መናኸሪያ
•ተስፋዬ ግዛው ህንፃ
•መሳይ ሆቴል
•ማሳረጊያ፦ ሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም

ጥንቃቄ እና ማሳሰቢያ‼️

ሰላማዊ ሰልፉ ቤተክርስቲያናት፣ መስጊዶች፣ የፀሎት ቦታዎች፣ ሆስፒታሎች፣ መካነ መቃብሮች፣ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎች የመሳሰሉት በሚገኙባቸው ቦታዎች 100 ሜትር ርቀት ውስጥ ሊደረግ የማይችል መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሰልፉ አስተባባሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እና ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 #በኢትዮጵያ_መንግስት እና #በህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ይዘት የሚገልፅ 12 ነጥብ ያለው #የጋራ_መግለጫ ከላይ ተያይዟል። ነገ ሁለት ዓመት የሚደፍነውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅለትና ህዝቡም እረፍት እንዲያገኝ ፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ፣ አርሶ አደሮችም ወደ እርሻቸው ፣ ሰራተኞችም ወደ ስራቸው፣ ነጋዴዎችም ወደንግዳቸው እንዲመለሱ አጠቃላይ…
ስለ " ሰላም ስምምነቱ " ምን ተባለ ?

🕊 የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኢትዮጵያ ለሰላም ያላት ቁርጠኝነት አሁንም የፀና መሆኑን ገልፀው " ስምምነቱ #ወደተግባር እንዲለወጥ አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ ጠንካራ አቋም / ቁርጠኝነት አለን " ብለዋል።

🕊 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (አንቶኒዮ ጉተሬዝ) ፦

በደቡብ አፍሪካ የተደረሰው የ " ሰላም ስምምነት " የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ህይወት የቀጠፈውና ሁለት ዓመት ያስቆጠረውን አስከፊ ጦርነት ለማስቆም ወሳኝ የሆነ የመጀመሪያ እርምጃ ነው ብለዋል።

#ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል አመራሮች ለሰላም የወሰዱትን እርምጃ እንዲደግፉ አሳስበዋል።

የጦርነት ማቆም የሚሰጠውን እድል በመጠቀም ለተቸገሩ ሰላማዊ ዜጎች ሁሉ ሰብአዊ እርዳታን ከፍ ለማድረግ እና በጣም አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

🕊 አሜሪካ ፦

ከአፍሪካ ኅብረት፣ ተመድ፣ ኢጋድ እና ከሌሎችም ጋር በመሆን የተደረሰው ስምምነት #ተግባራዊ እንዲሆን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ድጋፏን እንደታደርግ ገልጻለች። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነቱ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት እና ለልማት ያላቸውን ፍላጎት እንደምትደረግፍም አሳውቃለች።

🕊 የአውሮፓ ህብረት (ጆሴፕ ቦሬል) ፦

የሰላም ስምምነቱ ባስቸኳይ ሊተገበር ይገባል ያሉ ሲሆን በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ማቅረብ ፤ በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንደገና መጀመር #ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-11-03

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኡጋንዳ

" ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ #አይፈርሙ " - ተመድ

" ህጉ ኤችአይቪ/ኤድስን በመዋጋት ረገድ የተገኘውን ውጤት ሊቀለበስ ይችላል " - አንቶኒ ብሊንከን (የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ከቀናት በፊት ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት / አፍቃሪዎች ጋር በተያያዘ የኡጋንዳ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔ ተቃወመ።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በሕግ አውጭዎች ማክሰኞ የፀደቀውን ህግ እንዳይፈርሙ በይፋ ጥያቄ አቅርበዋል።

ኮሚሽነሩ ህጉን " ጨካኝ ህግ " ሲሉ ጠርተው በአጠቃላይ በህብረተሰቡ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር እና የሀገሪቱን ህገ መንግስት እንደሚጥስ ገልጸዋል።

እኚሁ የተመድ ባለስልጣን ፤ ፓርላማው ያሳለፈው ይኸው ህግ አድሎአዊ ነው ብለው " ምናልባትም በዓለም ላይ ካሉት እጅግ በጣም አስከፊው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳት ሙሴቬኒ በህጉ ላይ እንዳይፈርሙም ጠይቀዋል።

የኡጋንዳ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔ የተለያዩ ምዕራባውያን ሀገራት እየተቃወሙ መሆናቸው ይታወቃል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ውሳኔውን ተቃውመው ያሰራጩት መልዕክት በብዙሃን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።

ብሊንከን ህጉን " የኡጋንዳውያንን መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች የሚገታ እና ኤችአይቪ/ኤድስን በመዋጋት ረገድ የተገኘውን ውጤት ሊቀለበስ ይችላል። " ሲሉ ነው የገለፁት።

" የኡጋንዳ መንግስት የዚህን ህግ ተግባራዊነት እንደገና እንዲያጤነው #እናሳስባለን" ም ብለዋል።

የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሞሴቬኒ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሀገሪቱ ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ምንም አይነት ቦታ እንደሌላት ገልፀዋል።

ከቀናት በፊትም በፓርላማ ባሰሙት ንግግር #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉም ነው የገለፁት።

ፕሬዜዳንቱ ፓርላማው ባፀደቀው አዲሱ ህግ ላይ ፊርማቸውን ይኖራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው ፤ ልክ ፊርማቸው እንዳረፈ በቅፅበት #ተግባራዊ ይሆናል።

በአዲሱ የኡጋንዳ ህግ ፦

- በኡጋንዳ ምድር ማንም ሰው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ነኝ በሚል ማንነቱን ቢገልፅ ህይወቱን ሙሉ / ለበርካታ አመታ እስር ቤት ውስጥ እንዲያሳልፍ ይሆናል።

- በአንዳንድ ሁኔታዎች #ሞት ያስፈርዳል።

- የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ ፣ በቤተሰብ ደረጃ #ያስጠለለ ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን ይጥላል።

- ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ #የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይፀናበታል።

- " በተመሳሳይ ጸታ መብት " ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት ማተም አልያም በሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ማሠራጨት አይችሉም። ይህን ካደረጉ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

@tikvahethiopia
" መንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እስር እና እንግልት ያቁም " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር

የኢትዮጵየ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ባወጣው መግለጫ ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ባለሙያዎች የሚሰሩበት አውድ እየጠበበ ጋዜጠኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ በመንግስት የፀጥታ አካላት #እየተሸማቀቁ እና #እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ መታዘቡን ገልጿል።

ከሰሞኑን ፤ የማህበሩ መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ ፦
👉 ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ ፣
👉 ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ፣
👉 ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ ፣
👉 ጋዜጠኛ በየነ ወልዴ፣
👉 ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በመንግስት ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።

አንዳንዶቹ ያሉበት ቦታ እና ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኳን ቤተሰቦቻቸውም በቂ መረጃ ሳይኖራቸው በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ማህበሩ ፤ ጋዜጠኞች ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ እየታሰሩ፣ እየታፈኑና ቤታቸውና ቢሯቸው እየተበረበረ መሆኑ ባለሞያዎች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ፤ የፕረስ ምህዳሩ የበለጠ እንዲጠብ እያደረገ ነው ሲል ገልጿል።

ማህበሩ የተቋቋመው እንደዚህ አይነት ሙያውን የሚያቀጭጩ ጫናዎችን ለመታገል መሆኑን በመግለፅ የመንግሥት እርምጃዎችን በፅኑ አውግዟል።

ጋዜጠኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ጉዳያቸውን እስር ቤት ሳይቆዩ መከታተል እንደሚችሉ ከሁለት ዓመት በፊት በወጣው በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቢደነገግም ይህ ግን #ተግባራዊ_አለመደረጉ ማህበሩ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር መንግስት፦
- የፕረስ ነፃነት እንዲረጋገጥ
- ያጸደቃቸውን ህገ-መንግስታዊና ዓለም አቀፋዊ ህጎች እንዲያከብርና ውስጡን እንዲፈትሽ
- ያለምንም የህግ አግባብ ያሰራቸውን የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ
- ባለሙያዎች ላይ የሚያደርሰውን ማሸማቀቅ እንዲያቆም ጠይቋል።

@tikvahethiopia
#Update

" የተሟላ ሀገራዊ ሰላም ለማስፈን ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል " - ገዢው ብልፅግና ፓርቲ

ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ከጥር 13 እስከ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ የሥራ አስፈፃሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

ይህንን ስብሰባ ተከትሎ ፓርቲው መግለጫ አውጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሙሉ መግለጫውን ከላይ ያያዘ ሲሆን አንኳር ያላቸውን ጉዳዮች ከታች አቅርቧል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በ2017 የበጀት ዓመት #ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ፓርቲው ገልጿል።

የተሟላ ሀገራዊ ሰላም ለማስፈን እንዲቻል ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ መቀመጡን አሳውቋል።

" በሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን ለሚያቀርቡ አካላት ሰላማዊ መንገዶች እስከሚቻለው ድረስ እንዲመቻቹ፤ ዓላማቸው በነፍጥ ፍላጎታቸውን ማስፈጸም በሆኑ አካላት ላይ ደግሞ፣ ተገቢው ሕግን የማስከበር ሥራ በተጠናከረ መንገድ እንዲካሄድ " ሲል ፓርቲው ውሳኔ አሳልፏል።

ከሶማሌላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ የኢኮኖሚና የባህል ትሥሥር ያላትን አቋም የሚያሳይ መሆኑ መታየቱና በቀጣይም የተጀመረውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ #ተግባራዊ_ስምምነት ለማድረስ፣ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትም ጋር ተጨማሪ የባሕር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ፓርቲው ውሳኔ አሳልፏል።

ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ፣ የሽግግር ፍትሕና የቀድሞ ታጣቂዎች የተሐድሶ ፕሮግራሞች በተገቢው መንገድ ተከናውነው ለውጤት እንዲበቁ፣ ፓርቲው መንግሥትን እንደሚመራ ፓርቲ የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ገልጿል።

በፕሪቶርያው ስምምነት የተገኙ የሰላም ፍሬዎችን በመንከባከብ፣ የጎደሉ ክፍተቶችን በመሙላት፣ ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲሸጋገር ፓርቲው የተጀመሩ ጥረቶችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

(የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia