TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መግለጫ‼️

(15.04.2011ዓ.ም የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ)

ወቅታዊ የሀዋሳ ከተማን #ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በከተማው አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የተሰጣዊ ዜጣዊ መግለጫ፦

ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈጣን ፖለቲካዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ መሆኗ በግልፅ የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡ ለውጡን ተከትሎ በከተማችን ሀዋሳም አልፎአልፎ አሉታዊ ክስተቶች ይስተዋላሉ፡፡

ከእነዚህ አሉታዊ ክስተቶች መካከል ከሰኔ 10/2010 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ እየተስተዋሉ ያሉት ግጭቶችና የፀጥታ መናጋት በቀዳሚነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ይህን አልፎ አልፎ የሚከሰተው ግጭት ሀዋሳ ከተማ የምትታወቅበትን ነዋሪዎቿ ለዘመናት ያዳበሩት የመከአበክሮ የመፈቃቀድ እና አብሮ የመኖር እሴት እንዳይሸረሽር መንግስት አበክሮ በመስራት ላይ ነው፡፡

በከተማዋ ለዘመናት የቆየውን አብሮ የመኖር እሴት ለማጠልሽት፣ ቅሬታ ለመፍጠርና የጥላቻ ጥቁር ነጥብ ጥለው ለማለፍ የሚዳክሩ አካላትን ጥረት ለማክሸፍና የህግ የበላይነትን ለማስፈን ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ ግጭቶች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ የጥፋት ሀይሎችን ለህግ በማቅረብ ባጠፉት ልክ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ቀጥላል፡፡

ይሁንና ፀረ-ሰላም ሀይሉ ከድርጊቱ ባለመቆጠብ የተሳሳተ የትግል ስልቱን በመቀያየር የእውቀት መገበያያ የሆነውን ትምህርት ቤት የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለትም በሀዋሳ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ በሚገኘው አዲስ ከተማ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት
ቤት ሁከትና እረብሻ በመፍጠር 12 ወጣቶች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ ተማሪ ያልሆኑ መሆናቸው ተለይቷል፡፡

በግጭቱም እርስበእርስ ድንጋይ በመወራወር በአስሩ ላይ ቀላል ጉዳት እንዲሁም ለፀጥታ ሀይሉ ባለመታዘዝ በሁለቱ ላይ ደግሞ ከባድ አደጋ ደርሷል፡፡

ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ ወጣቶች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል እና በአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

የረብሻው መንስኤ ገና በፀጥታ ሀይሉ #በመጣራት ላይ ያለ ቢሆንም በርካታ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አካላት ያልሆኑ ነገር ግን እራሳችውን ከተማሪ ጋር ያመሳሰሉ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት ተማሪዎችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ከተዋል፡፡

ክስተቱን #የብሔር_ግጭት ቅርፅ ለማስያዝ ጥረት ለማድረግ የሞከሩ ቢሆንም አብሮ መኖርን ባህሉ ያደረገው የከተማው ነዋሪ ግን አልተባበራቸውምና ልፋታቸው ሳይሳካ #መና ሆኖ ቀርቷል፡፡

በዚህ ድርጊት #ጠንሳሽነትና ተሳታፊነት የተጠረጠሩ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር የማዋል ስራ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም
ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በፀጥታ ሀይሉና በህብረተሰቡ የጋራ ጥረት የከተማው #ፀጥታ_ሁኔታ ወደነበረበት የተመለሰ ሲሆን ለከተማው ሰላም ወዳድ ህዝብ የከተማው አስተዳደር ያለውን ክብርና አድናቆት እየገለፀ በቀጣይም ነዋሪው ከመንግስት ጎን በመቆም የከተማውን ሰላም ለማደፍረስና አብሮ የመኖር እሴትን ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ አካላትን አጋልጦ በመስጠት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪውን እያቀረበ የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ሰላም እና ፀጥታ የማስጠበቅ ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታውቃል፡፡

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia