TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሙስሊም ሊቃውንት/ #ዓሊሞች ጉባዔ ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ  እየተካሄደ ይገኛል።

ለሶስት ቀን ይቆያል የተባለው ይኸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት ሁለተኛው ዓመታዊ የዓሊሞች (የሙስለም ሊቃውንት) ጉባዔ ላይ ፦
- #የትግራይ
- የሶማሊ
- የአፋር
- የአማራ
- የኦሮሚያ
- የጋምቤላ
- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ
- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ
- የደቡብ ኢትዮጵያ
- የሐረሪ
- የሲዳማ
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ የዑላማ ምክር ቤቶች እተካፈሉ ይገኛሉ።
                          
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ትላንት ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ፤ " ጦርነት በፈጠረው የሰላም እጦት ችግር ሳቢያ ተለያይተን ከነበርነው የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር ግንኙነታችን ቀጥሎ ዛሬ በአንድ ጉባዔ ላይ መታደማችን የሚያስደስትና የሠላምን ዋጋ ከፍ የሚያደርግ ነው " ብለዋል።

ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፤ " የሀገራችን ሙስሊም ሊቃውንት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆነው ዲኑን ለትውልዶች ለማሻገር እና ማኀበራዊ ትስስር እንዲፈጠር ትልቅ ልፋት የሚያደርጉ ታላቅ የሕዝብ ባለውለታና የዲን መሪ ናቸው " ብለዋል።

የሀገር አቀፉ የዑለማ ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ጀይላን ኸድር በበኩላቸው፣ " የዑለማው በዚህ ዓይነት ትስስር መፍጠር ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ አንድነት ትልቅ ፋይዳ አለው " ብለዋል።

የዑለማው ጉባዔ የሙስሊሙ ችግሮች እና የሚገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ የሚገለጹበት በመኾኑ፣ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ቃዲዎቾ፣ የየክልሉ የዑለማ ም/ ቤት እና የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ኃላፊዎች በዚህ መድረክ ላይ ተገናኝተው መምከራቸው መድረኩን ታሪካዊ ያደርገዋል ተብሏን።

የጉባዔው ተሳታፊ የሆኑት ክልሎች የየክልላቸውን ተጨባጭ ሁኔታ አስመልክተው ለጉባዔው ሪፖርት ማቅረባቸውን ለማቀው ተችሏል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ሊቃውንት ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ እልምና ጉዳዮች ጠቅላት ምክር ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

​NB. የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር የነበረውን አለመግባባት በይቅርታ ፈቶ ወደ ቀደመው ግኝኑነት መመለሱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia