"የጤና ሚኒስቴር ትምህርት ለመጀመር የሚስችል ሁኔታ መኖሩን ሲያረጋግጥልን ትምህርት እንጀምራለን" - ዶ/ር ኢንጂ. ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስትር
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሞ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን የጤና ሚኒስቴር ማረጋግጫ ሲሰጥና መንግስት ውሳኔ ሲያሳልፍ ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ከትምህርት ገበታ ውጪ ያሉ ህፃናት በከፍትኛ ሁኔታ እየተጎዱ በመሆኑ ለእነሱ ቅድሚያ እንደሚሰጥም ነው ያብራሩት፡፡
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ለ6 ወር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናት ከዚያ በፊት ለሁለት አመታት ያክል ይዘውት የነበረውን እውቀት ሊያሳጣቸው ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት ለህፃናት ቅድሚያ ለመስጠት እቅድ ተይዟል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው ህፃናት በኮሮና ቫይረስ የመያዝና የማስተላለፍ ባህሪያቸው ከሌሎቹ የቀነሰ በመሆኑ ድርጅቱ የሚያስቀምጣቸውን የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ሙሉ ለሙ በመተግበር ትምህርት ለመጀመር ጥረት ይደረጋል፡፡
በትምህርት አከፋፈት ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታበተስፋፋባቸው እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ትምህርት በ3 ፈረቃ ለመጀመር እቅድ ተይዟል፡፡
ከትላልቅ ከተሞች እርቀው የሚገኙና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት በሌለባቸው አካባቢዎችም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንግዶችን በመተግብር ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Irreecha2013
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት ሲከበር የነበረው የኢሬቻ በዓል ዘንድሮ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከግምት ባስገባ መልኩ እንደሚከበር አባገዳዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚከበር መሆኑንና የሆረ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ደግሞ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚከበር አባገዳዎቹ ገልጸዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥር በሽታውን (ኮሮና ቫይረስ) ለመከላከል በሚያመች መልኩና የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክር መሰረት የሚወሰን መሆኑ ተገልጿል፡፡
የገዳ ስርዓት ባለቤት የሆነው የኦሮሞ ህዝብ የአባ ገዳዎችን ጥሪና የጤና ባለሙያዎቸን ምክር ተከትሎ በዓሉን እንዲያከብር አባገዳዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ፦ የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ፣ ኢቲቪ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#TikvahFamilyBulen በቡለን ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እንዲሁም በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የቤኒሻነጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ወረዳ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሳውቀል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የጤና ባለሞያዎች እንደተናገሩት በሚሰሩበት የጤና ተቋም ጉዳት ደርሶባቸው የመጡ የፀጥታ ኃይል አባላት ስምንት (8) የሚደርሱ እና በርካታ ነዋሪዎች አሉ። ከነዋሪዎች መካከል…
"ከአንድ ሳምንት በኋላ እስካሁን ድረስ የአባቴን አስከሬን አግኝቼ ለመቅበር አልቻልኩም" - አቶ ኃይሉ አዲሱ
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአንድ ሳምንት በፊት በቤኒሻንጉል ክልል ቡለን ወረዳ እየተፈፀመ ስላለ ጥቃት ከቡለን ቲክቫህ አባላት የተላከውን መረጃ ማካፈሉ የሚዘነጋ አይደለም።
በወቅቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ አባላቶቻችን አልገለፁም ነገር ግን በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈ ነዋሪዎች መኖራቸው ፣ የፀጥታ ኃይል አባላት መገደላቸውን፣ እንዲሁም ብዙ ሰዎች መቁሰላቸውን አሳውቀው ነበር።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት BBC በአካባቢው ጥቃት ሰለባ ከሆኑና ቤተሰቦቻቸውን ያጡ የአካባቢው ነዋሪዎችን አነጋግሮ በድረ ገፁ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዞ ወጥቷል ፤ በማስፈንጠሪያው ገብታችሁ አንብቡ : https://telegra.ph/Bulen-09-16
PHOTO : የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

600,000 ብር በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ ተያዘ! በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድንበር አካባቢ 600 ሺህ ብር በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የተገኘ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ለኢዜአ አስታውቋል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ እንደገለፁት ፦ - ግለሰቡ ገንዘቡን ሲያዘዋወር የተገኘው ትናንት በአሶሳ ዞን ሱዳን ጠረፍ…
ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ህገ-ወጥ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ዋለ!
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ተጨማሪ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ለኢዜአ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ፓሊስ ባደረገው ክትትል ትላንት ምሽት ደንጎሮ ኬላ በተሽከርካሪ ውስጥ በማዳበሪያ ተጠቅጥቆ ሊያልፍ የነበረ 770 ሺህ ብር በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል፡፡
እንዲሁም ዛሬ ማለዳ ደግሞ ማንኩሽ ኬላ ላይ ሌላ 300 ሺህ ብር እንዲሁ በሻንጣ ለማሳለፍ ሲሞከር በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር እንደዋለ አስታውቀዋል፡፡
ገንዘቡን ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት (2) ግለሰቦችም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

#MoH
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 1 ሺህ 311 የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።
በነገው ዕለት የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሕሙማን ደህንነት ቀንን አስመልክቶ ዛሬ ጤና ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ ሰማን ተከታዩን ብለዋል ፦
- ኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሥራ ግንባር ቀደም የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ላይ መጠነ ሰፊ ችግር አስከትሏል።
- 1 ሺህ 311 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 700 የሚሆኑት ደግሞ አገግመው ወጥተዋል፤ ቀሪዎቹ በህክምና ተቋማት ይገኛሉ።
- ሁለት የሕክምና ባለሙያዎችም ለሞት ተዳርገዋል።
- ነገ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቱ የሚከበረው የሕሙማን ቀን ቫይረሱ የተገኘባቸው ወገኖቻቸውን ሌት ተቀን እያገለገሉ ላሉ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ክብርና ምስጋናን በመስጠት ይከበራል።

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በብድር እና በስጦታ ውሎች ላይ የሚከተለውን ማሳሳቢያ እና ቅድመ ሁኔታ አውጥቷል!
1. የስጦታ ውልን በሚመለከት ፦
• የአሰራር ማሻሻያዎች እስኪደረጉ ድረስ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ከነገ መስከረም 7 ጀምሮ አይሰጥም።
2. የሽያጭ እና የብድር ውልን በሚመለከት ፦
• የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ለማግኘት የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ በባንክ በኩል ብቻ ማለትም ከሻጭ ወይም ከአበዳሪ የባንክ ሒሳብ ብቻ ተቀናሽ ተደረጎ ወደ ገዥ ወይም ተበዳሪ የባንክ ሒሳብ መተላለፍ (transfer) የተደረገ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
Via abyassinaialw /Elias Meseret/

መስከረም 6/2013 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦
#Somali
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 119 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 18 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 31 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Harari
በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 503 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#DireDawa
ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 85 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 18 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Tigray
በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 398 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 49 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,141 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከወልዲያ ሆስፒታል በአስክሬን ምርመራ)
#Sidama
በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 90 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 23 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,402 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 228 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
#SNNPRS
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 488 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 40 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
@tikvahethiopiaBOT

የመስከረም 6 ሀገር አቀፍ የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 8,355
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ - 738
ከበሽታው ያገገሙ - 677
ህይወታቸው ያለፈ - 10
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 8,355
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ - 738
ከበሽታው ያገገሙ - 677
ህይወታቸው ያለፈ - 10
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"... እኔ የታሰርኩት ለምን ወንጀል ፈፀምክ ተብዬ ሳይሆን ለምን አሰብክ ተብዬ ነው" - አቶ ልደቱ አያሌው
የኢዴፓ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት የወከሏቸውን ጠበቆች ዛሬ አሰናብተዋል።
አቶ ልደቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት 'ህግ የፖለቲካ መሳሪያ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ በህግ ክርክር መብትን ማስከባር ስለማይቻል' እንደሆነ ገልፀዋል።
አቶ ልደቱ አያሌው ከአሁን በኋላ ግዴታዬን ለመወጣት ቀጠሮ ሲሰጠኝ በችሎት ፊት ከመገኘት ባለፈ የህግ ክርክር የማድረግ ፍላጎት የለኝም ብለዋል።
ምንጭ ፦ ኢዴፓ

የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በፍጥነት እንዲሰጥ እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ተናግረዋል።
ዶክተር ቶላ በሪሶ ትላንት ከቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ተከታዩን ብለዋል ፦
- ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናው ተዘጋጅቷል የፈተናው ወረቀት ታትሞ በማተሚያ ቤት ውስጥ ይገኛል ትምህርት ሲጀመር ፈተናው የሚሰጥ ይሆናል። ፈተናው ከተሰጠ በኃላ ከ3 ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ታርሞ ውጤቱ እንዲታወቅ ይድረጋል።
- የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በተመለከተ በድረ ገፅ አማካኝነት ፈተናውን ስለሚወስዱ የፈተና ማዕከላት ተመርጠው ተማሪዎቹ ፈተናውን የሚወስዱበት ሁኔታ እየተመቻቸ ይገኛል።
- ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጭ የሆኑ ተማሪዎች ባለፈው ዓመት ወደ ሚቀጥለው ክፍል ገብተው እንዲማሩ በተወሰነው መሰረት ባለፈው ዓመት ያለፋቸውን የትምህርት ጊዜ ለተወሰነ ጊዜ ከተማሩ በኃላ የዚህን ዓመት ትምህርት የሚቀጥሉ ይሆናል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የተሻለ ዝግጅት እንዲኖራቸው መሥራት እንደሚገባ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳስቧል።
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ጌታቸው ቢያዝን ለክልሉ ቴሌቪዥን (አማራ ቲቪ) ከተናገሩት የተወሰደ፦
- የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሀገር ዓቀፍ ፈተና በተሟላ መልኩ አስፈላጊውን ቅጽ (ፎርም) አልሞሉም ሆኖም የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ90 ሺህ በላይ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- ትምህርት ቤቶች በተለይ 8ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል።
- አብዛኛው በሚባል መልኩ የአማራ ክልል ተማሪ ገጠር አካባቢ እንደመኖሩ በሚፈለገው ልክ ጥረቱ ውጤት አስመዝግቧል ማለት አይቻልም።
- ተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍቶቻቸው በእጃቸው ስላሉ እንዲያነብቡ፣ የ11ኛ ክፍል ትምህርቶችን መልሰው እንዲከልሱና ወላጆች ለልጆቻቸው አጋዥ መጻሕፍትን እንዲገዙላቸው መልእክት ተላልፏል።
- ሀገር አቀፍ ፈተናው በኢንተርኔት በመታገዝ በቀጥታ (ኦንላይን) እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተገልጿል ፤ ተማሪዎች “ታብሌት” ተሰጥቷቸው እንዴት ጥያቄዎችን መሥራት እንዳለባቸው ከቴክኖሎጂ ውጤቱ ጋር የመለማመጃ ጊዜ ይኖራቸዋል።
- ሀገር አቀፍ ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴርም ይሁን በሀገር ዓቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ ይፋ አልተደረገም።
- ትምህርት ከተጀመረ የመጀመሪያዎቹ 45 ቀናት ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የክለሳ ጊዜያቸው ይሆናል።

ውሃ የያዘው የሀረማያ ሃይቅ!
ሀረማያ በውሃ እንደተሞላ አንዲቆይ ምን ይደረግ?
የሀረማያ አካባቢ አርሶ አደሮች በሚሰሩት የመስኖ ስራ ብዙ የውሃ ብክነት እንዳለ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ስለዚህም የአካባቢው አርሶ አደሮች ውሃ ቆጣቢ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ ኀብረተሰቡን ማስተማር እና ግንዛቤ ማስጨበጥ የመፍትሄው አካል መሆን እንዳለበት ያሳስባሉ።
"ይህ ሀይቅ ባለቤት የሌለው ከሆነ ተመልሶ ይደርቃል ፤ ይህ መታወቅ አለበት" ብለዋል የሀረማያ ዩኒቨርስቲ ሀይድሮሊክና የውሃ ሃብት መሀንዲስ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ኢንጂነር ተሾመ ስዩም።
ከዚህ ሌላ ሀረማያ ሀይቅ ድንበር የሌለው እንደመሆኑ መጠን ሀይቁ እንዲቆይ በማካለል ህብረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀምበት ማድረግ ያሻል።
የሀረማያ ሀይቅ በሕይወት እንዲቆይ ለማድረግ የተፋሰስ ልማትን ማካሄድ ያስፈልጋል ፣ እየታጠበ ወደ ሀይቁ የሚገባውን አፈርን ለመቆጣጠርና ውሃ በስርዓቱ ወደ ሀይቁ እንዲፈስ ለማድረግ አስራ አምስት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የተፋሰስ ልማት መሰራት እንደሚያስፍልግ ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ይኹን አንጂ እስከዛሬ የተሰራው የተፋሰስ ልማት በቂ እንዳልሆነ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገልፀዋል።
ችግኞች መትከልና መንከባከብን አከታትሎ መስራትን እንደሚጠይቅ የሚናገሩት እኚህ ምሁር "ሀይቁ አዋሳኝ አካባቢዎች አፈር ታጥቦ እንዳይገባ ሳር መትከል ላይ መስራት በጣም ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ።
ፅሁፉ ከBBC የአማርኛው አገልግሎት የተወሰደ ነው።
📸 Amanuel Ethicha