TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቅኝት
" ኢትዮጵያውያን ከሶሚሊያ ይውጡልን " እስከ " ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማት ይነጠቅ " ዘመቻ !
ከሰሞኑን #የሶማሊያ እና #የግብፅ አክቲቪስቶች እንዲሁም " ሶማሊያን ነው የምንደግፈው " የሚሉ የኢትዮጵያ አክቲቪስቶችና ታዋቂ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ዘመቻ ከፍተዋል።
ጉዳዩ ኢትዮጵያ የባህር በር ለመጠቀም እድል ይሰጣታል ከተባለውና ከሶማሌላንድ ጋር ካደረገችው የመግባቢያ ስምምነት በኃላ የመጣ ነው።
ከስምምነቱ ማግስት ጀምሮ የሶማሊያ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ መግለጫ የማውጣት፣ አጉል ዛቻ የማድረግ ፣ ኢትዮጵያውያን እንደ * ወራሪ * እንዲታዩ የማድረግ ስራ ሲሰራ ነበር።
የሀገሪቱ ብሄራዊ የመንግሥት የዜና አውታሮች እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ አክቲቪስቶች እንዲሁም የግብፅ ሰዎች #የተናበበ በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያን ጫና ውስጥ ይከትልናል ያሉትን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ።
ቀላል የማይባል የተከታይ ቁጥር ያላቸው ገፆች #ነጭ_ውሸት ከማሰራጨት ባለፈ ኢትዮጵያውን እንዲጠቁ የማድረግ ዘመቻ እያደረጉ ነው።
ለአብነት ፤ " አዲስ አበባ ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት እየተደረገ ነው ፣ መዲናዋ በተኩስ እየተናጠች ነው ፣ የሀገሪቱ መንግሥት ለሁለት ተከፋፍሏል ፣ እርስ በእርሱ እየተዋጋ ነው፣ ኢትዮጵያ በሁሉም መልኩ ተዳክማለች " የሚሉ ነጭ ውሸቶችና እና ሀሰተኛ የፕሮፖጋንዳ ስራዎች እየሰሩ ይገኛሉ።
እንዲሁም " ኢትዮጵያውያን ሶማሊያ ውስጥ ምን ይሰራሉ ? ፣ ጠራርገን እናስወጣቸው፣ ወደ ሀገራቸው እንሸኛቸው ፣ ወራሪ ናቸው " የሚሉ ለጥቃት የማመቻቸትና የጥላቻ ቅስቀሳዎችን ከዚህ አለፍ ሲልም የግድያ ዛቻዎችን እስከማስተላለፍ ደርሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንድትፈጥር ላደረጉት ስራ የተሰጣቸው ዓለም አቀፉ " የኖቤል የሰላም ሽልማት " እንዲነጠቁ የሶማሊያ ሰዎች ዘመቻ ማድረግ ጀምረዋል።
ዘመቻው በብሄራዊ የሶማሊያ ቴሌቪዥን ጣቢያ እና ብሄራዊ ዜና አገልግሎት ጭምር ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት ሰዎች እንዲፈርሙት እየተደረገ ይገኛል።
ይህንን ዘመቻም የግብፅ አክቲቪስቶችም አብረው እያሟሟቁት ይገኛሉ።
NB. የኖቤል የሰላም ሽልማት አንዴ ከተሰጠ እንደማይሻር / እንደማይነጠቅ ይታወቃል፤ በስቶክሆልምና በኦስሎ ያሉት የሽልማት ሰጪ ኮሚቴዎች አንድም ጊዜ ሽልማትን ለመሻር/ ለመንጠቅ አስበው አያውቁም።
በአጠቃላይ የሶማሊያ ሰዎች " የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኖቤል ሽልማት ይነጠቅ " ከማለት አንስቶ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት እንዲከፈት ፣ በአዲስ አበባ እና ክልል ያለው ህዝብ እንዲሸበር በማህበራዊ ሚዲያ እየሰሩ ያሉትን ዘመቻ የግብፅ ሰዎችም ሲደግፏቸው ታይቷል።
በዚህ የሶማሊያ እና የግብፅ ሰዎች የጋራ የሚመስል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ #የሀገራችን_ዜጎችም ሲሳተፉ መመልከት ተችሏል።
በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ፤ ኢትዮጵያ ማንንም ባልወረረችበት ፣ የሰው ሀገር ባላጠቃችበትና ፍትሃዊ ጥያቄ በመጠየቋ ብቻ የሀገራችን ዜጎች ሆነው ከሶማሊያ እና ግብፅ ጋር በማበር የሚያደርጉት ድርጊት እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።
" የኖቤል ሽልማት ማሻር፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣን ማስወረድ ፣ የሀገሪቱን መንግሥት መቀየር ይህ ሁሉ #ኢትዮጵያውያንን ብቻ የሚመለክት ነው " ያሉ ሲሆን " በሀገር ውስጥ የቱንም ያህል ተቃውሞ፣ ቅሬታ ቢኖረን እንዴት ከሌላ ሀገር ሰዎች ጋር ለዛውም ለኢትዮጵያ መልካም ከማያስቡ ሰዎች ጋር እናብራለን ? ይህ ተገቢ አይደለም መታረም አለበት ፤ ማንኛውም የውስጥ ጉዳዮች በውሥጥ ማለቅ አለባቸው " ብለዋል።
#ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia