TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሲአን #ሲዳማ_ዞን #ሞረቾ #ወተረሬሳ #ሀገረሰላም

በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ኔሳ ዛሬ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በሲዳማ ዞን ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በነበረ ግጭት 21 ሰዎች መሞታቸው ተናግረዋል። በሲዳማ ዞን ስር ባለው ወተረሬሳ 12 ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት አቶ ደሳለኝ በሞሮቾ ሶስት እና በሀገረሰላም ደግሞ ሁለት ሰዎች በግጭቱ ህይወታቸው እንዳለፈ አስረድተዋል።

በሐዋሳ በነበረው ግጭት አራት ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች ሰባት ሰዎች በፅኑ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሾዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በግጭቱ የተጠረጠሩ 150 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከንቲባው ጠቁመዋል። ግጭቱን ተከትሎ የክልል እና የፌደራል አካላት ባደረጉት የማረጋጋት ስራ በሐዋሳ ከተማ እና በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን አቶ ስኳሬ ገልፀዋል። በሐዋሳ በዛሬው ዕለት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደታየና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎች ተከፍተው ስራ መጀመራቸው ተሰምቷል። የኢንተርኔት አገልግሎት እና የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ግን አሁንም ዝግ ናቸው።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲዳማ_ዞን

በሲዳማ ዞን ስለጠፋው ክቡር የሰው ህይወት የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ነዋሪዎችን ዋቢ አድርገው ከሚገልፁት ቁጥር ውጪ በመንግስት በኩል ይፋ የተደረገ መረጃ የለም። እኛም በተለያየ መልኩ ስለጠፋው የሰው ህይወት የተረጋገጠ መረጃ ለማግኘት እየጣርን ነው። የወደመ የተቋማት እና የግለሰቦች ንብረትን በተመለከተም አስተማማኝ መረጃ ወድናተ ለማድረስ ጥረት እያደረግን ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia