TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UkraineCrisis የሩስያ እና የዩክሬን ቁርሾ ምንድነው ? ዩክሬን ወደ አውሮፓ ተቋማት NATO እንዲሁም አውሮፓ ህብረት የምታደርገውን እርምጃ ሩሲያ ስትቃወም ቆይታለች። አሁን ደግሞ ዩክሬን #የምዕራቡ_ዓለም_አሻንጉሊት እንደሆነች እና በማንኛውም ሁኔታ ትክክለኛ ሃገር እንዳልነበረች ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይገልፃሉ። ዋና ፍላጎታቸው ደግሞ ዩክሬን የ30 ሃገሮች የመከላከያ ሃይል ጥምረት…
#Ukraine

አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው ?

- ዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ለመውረር እንቅስቃሴው ተጀምሯል ብላለች።

- ዛሬ ማለዳ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ በአገራቸው ላጥ ጥቃት መክፈቷን አሳውቀዋል። የሚሳአኤል ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። ሩሲያ ዛሬ ማለዳ ላይ የከፈተችው ጥቃት ኢላማ ያደረጉት የዩክሬን መሰረተ ልማቶችና የድንበር ጥበቃዎች ላይ ነው ብለዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሰራዊቱ ጥቃት መሰንዘሩን አረጋግጦ ኢላማዎቹ ከተሞች ላይ ሳይሆኑ የዩክሬን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች፣ የአየር መከላከያ እና የአየር ኃይል ተቋማት መሆናቸውን ገልጿል።

- ሩሲያ በማንኛውም ቀን "አውሮፓ ውስጥ ትልቅ ጦርነት" ልትጀምር እንደምትችል የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ አስጠንቅቀው ሩሲያውያን እርምጃውን እንዲቃወሙት ጠይቀዋል። ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን አስታውቀዋል። "ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር የስልክ ንግግር ለማድረግ ሞከርኩ። ውጤቱ ዝምታ ሆነ" ብለዋል ዜለንስኪ። ሩሲያ ወደ 200 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮች እና በሺዎች የሚቆጠሩ የውጊያ መኪናዎች በዩክሬን ድንበር እንዳሏት ተናግረዋል። ሩሲያውያን በዩክሬን ጉዳይ እየተዋሹ መሆኑን ጠቅሰው ጥቃትን እንዲቃወሙ ተማፅነዋል።

- የቭላድሚር ፑቲን በምስራቃዊ ዩክሬን #ዶንባስ ክልል ወታደሮቻቸው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲያካሂዱ አዘዋል። በሩሲያ የሚደገፉ አማጺያኖች ጋር እየተዋጉ የሚገኙ የየክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደቤታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አስተላልፈዋል። ዩክሬንን የመቆጣጠር እቅድ እንደሌላቸው የገለጹ ሲሆን ነገር ግን ማንኛውም አካል ሩሲያ ላይ አደጋ የሚጭር ነገር ካደረገ ምላሻችን ፈጣን ነው ብለዋል።

#BBC

@tikvahethiopia
#Ukraine

በዩክሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጎ እንደ ፖላንድ ወዳሉ ጎረቤት ሀገራት እንዲሄዱ እንዲያመቻችላቸው ተማፅነዋል።

ሌሎች ሀገራት ከዩክሬን ዜጎቻቸውን በማስውጣት ላይ ይገኛሉ።

ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ዩክሬን ሀገር የሄዱ 49 የሀገራችን ዜጎች የሆኑ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ግን ከ400 እስከ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ እንደሚገኙ ይገመታል።

ኬንያ ከ270 በላይ የሆኑ ዜጎቿን ከዩክሬን ለማስውጣት እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑ ታውቋል።

#EliasMesert

@tikvahethiopia
#Ukraine

በዩክሬን ዩኒቨርሲቲዎች ከሚማሩ የውጭ ሀገር ተማሪዎች በግምት 20% የሚሆኑት ከአፍሪካ የሄዱ ናቸው። ከእነዚህ መከከል በግምት 4000 የናይጄሪያ ተማሪዎች ይገኙበታል።

አሁን ላይ ዩክሬን ውስጥ ባለው ጦርነት የንግድ በረራዎች በመቋረጣቸው ምክንያት በዩክሬን ያሉ ተማሪዎች እጣፋንታ በእጅጉ እያሳሰባቸው መሆኑን የናይጄሪያ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እየገለፁ ይገኛሉ።

የሀገሪቱ መንግስትም ለተማሪዎቹ አንዳች መፍትሄ ይፈልግ ዘንድ ተማፅኖ እየቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ብቻችንን አጋፍጠውናል " - ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ " ብቻችንን አጋፍጠውናል " ሲሉ ምዕራባውያንን ወቅሰዋል። ዜሌኒስኪ " ሃገራችንን ለመጠበቅ በብቸኝነት እየተዋጋን ያለነው እኛው ነን " ሲሉ ተናግረዋል፡፡ " ማን አግዞን ከጎናችን ሆኖ ተዋጋ? " ሲሉ የሚጠይቁት ፕሬዝዳንቱ " ማንም "ሲሉ መልሰዋል። " ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደተወን ነው የተሰማኝ፤…
#Ukraine #USA

" ከሀገር እናስወጣህ " - አሜሪካ

" ውጊያው ያለው እዚህ ነው። የምፈልገው የጦር መሳሪያ እንጂ የማምለጫ መንገድ አይደለም " - የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ


እንደ ዋሽንግተን ፖስት መረጃ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ከሀገራቸው እንዲወጡ ለመርዳት ተዘጋጅታ ነበር ነገር ግን እሳቸው ከሀገራቸው ንቅንቅ እንደማይሉ ገልፀዋል።

ፕሬዜዳንቱ ትላንት በሰጡት መግለጫ ላይ #ምዕራባውያንን ክፉኛ መተቸታቸውና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደተዋቸው እንደሚሰማቸው መግለፃቸው ይታወሳል።

ፕሬዜዳንቱ ፥ " እንደሚደግፉን ነበር ቃል ሲገቡልን የነበሩት፤ ሆኖም ሞትን እንድንጋፈጥ ብቻችንን ትተውናል " ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Ukraine #Russia

በሩስያ እና ዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ሰላማዊ መፍትሄ ካላገኘ በበርካታ ታዳጊ ሀገራት እንዲሁም ባደጉት ሀገራት ጭምር የሚያሳድረው ተፅእኖ የበረታ እንደሚሆን እየተገለፀ ነው።

በተለይ በጦርነቱ ከ2ቱ ሀገራት ውጭ NATO የመሰሉ ኃይሎች የሚቀላቀሉ ከሆነ ዓለማችን እጅግ የከፋ ቀውስ ውስጥ ትገባለች ተብሎ ተፈርቷል።

እስካሁን ምዕራባውያን ከሩስያ ጋር ጦር ባይማዘዙም የማዕቀብ ናዳ ሩስያ ላይ እያወረዱ ዩክሬንን በመሳሪያ እያስታጠቁ የሚያስፈልግሽን ሁሉ ድጋፍ እናደርግልሻለን እያሉ ይገኛሉ።

ጦርነቱ እንዲሁ በቀላሉ የማታይ አይደለም፤ በተዋጊዎቹ ሀገራት መካከል የሚረግፈው የሰው ህይወት እንደተጠበቀ ሆኖ ኢኮኖሚያቸው ይዳከማል። በርካታ ሀገራትን ችግር ላይ ሊጥል ይችላል። እስካሁን በነዳጅ፣ በስንዴ፣ በተፈጥሮ ጋዝ...ዋጋ ንረት ላይ ያሳደረው ተፅእኖ የሚታይ ነው።

ተጎጂዎቹ ግን ታዳጊ ሀገራት ብቻ ሳይሆኑ ያደጉትንም ያካትታል።

ለምሳሌ፦ ዩናይትድ ኪንግደምን ብንመለከት ተንታኞች በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ባለፉት አሥርተ ዓመታት ባልታየ ፍጥነት የዋጋ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል ይጠቁማሉ።

ካረን ዋርድ የተባሉ አንድ ተንታኝ በግጭቱ ምክንያት የሚከሰቱ ኢኮኖሚያዊ ውድቀቶች የዋጋ ግሽበት 8 በመቶ ሊያደርስ ይችላል ብለዋል።

የዓለም የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ጨምሯል ያሉት ተንታኙ ይህም የዩናይትድ ኪንግደም የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አድርጓል ብለዋል።

ሩሲያ ትልቅ #የማዳበሪያ ላኪ በመሆኗ የምግብ ምርት ዋጋ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋትም አለ።

ጦርነቱ ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ይገኝ እንደሆነ አንዳችም ፍንጭ ማየት አልተቻለም። በየዕለቱ እየተባባሰ ዓለምን ህዝብ ስጋት ከፍ እንዳደረገ ቀጥሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WW3 " ምዕራባውያን ሩስያን ወደ 3ኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ ነው " - የቤላሩስ ፕሬዜዳንት የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የምዕራባውያን ማዕቀቦችን " ሩሲያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ " ነው ሲሉ ተጠያቂ አድርገዋል። የ #NATO ሀገራት ሩስያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንት ሉካሼንኮ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። ፕሬዝዳንቱ…
#Belarus #Russia #Ukraine #USA

ቤላሩስ የሩሲያን የኒዩክለር ጦር መሳሪያ በቋሚነት በግዛቷ ውስጥ እንዲተከል መስማማቷን ዛሬ በሰጠችው ህዝብ ውሳኔ በሙሉ ድምጽ ማጽደቋን አስታውቃለች፡፡

በዛሬ እለት ተቀልብሷል የተባለው ነባር ህግ የቤላሩስን ገለልተኝነት የሚሽር ሲሆን ከሩሲያ ጋር ለምታደርገው ጠንካራ ወታደራዊ ልምምድ በር ይከፍታል ተብሏል፡፡

ባለፈው ሀሙስ በወታደራዊ ልምምድ ወደ ዩክሬን የሄዱት የሩሲያ ወታደሮችም ከዚሁ ከቤላሩስ የተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተነግሯል።

ለውጡ ቤላሩስ ከሶቭዬት ህብረት ነጻ ከወጣች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዛቷ የኒውክለር መሳሪያ እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተያያዘ መረጃ አሜሪካ በቤላሩስ ያላትን የኤምባሲ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ መዝጋቷን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ማስታወቋን ቪኦኤ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ሩስያ እና ዩክሬን መካከል ዛሬ የመጀመሪያው የሰላም ንግግር በቤላሩስ ተደርጓል፤ ውይይቱ ረጅም ሰዓታት የወሰደ ሲሆን የተገኘ ፍሬ ነገር ስለመኖር አለመኖሩ እስካሁን አልታወቀም። የሁለቱም ሀገራት ልዑካን ወደ የሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #UKRAINE #RUSSIA

ሩስያ ዩክሬን ላይ የጀመረችው ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጠር ጫና እንደሚኖር የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ተናግረዋል።

ዶ/ር እዮብ ለፋና ብሮድካስት በሰጡት ቃል ፤ " ሩስያ እና ዩክሬን የንግድ አጋሮቻችን እንደመሆናቸው የሚፈጠር ጫና ይኖራል " ብለዋል።

" ያም ሆኖ ግን ከሀገራቱ በብዛት ኢትዮጵያ ምታስገባው ስንዴ ለዚህ ዓመት የሚበቃው ቀድሞ በመገዛቱ ተፅእኖው ፈጥኖ ላይደርስብን ይችላል " ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
#UKRAINE #NATO

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ ዛሬ በመዲናቸው ኬዬቭ ሆነው በቴሌቪዥን ለህዝባቸው ባሰሙት ንግግር ላይ የተናገሩት ፦

" ...ምዕራባውያን መሪዎች ሩሲያ አገራችንን ልትወር መሆኗን ያውቁ ነበር፤ ፑቲን ከተሞቻችንን በቦምብ እንዲደበድቡ ፈቅደዋል።

በዩክሬን ላይ ጥቃት እንደሚፈጸም እና ጉዳትም የማይቀር መሆኑን እያወቀ NATO ሆን ብሎ የዩክሬን ሰማይ ለበረራ ዝግ እንዳይሆን አድርጓል።

የNATO መሪዎች ዛሬም ከበረራ ነጻ የሆነ ቀጠና ውሳኔን ባለማሳለፋቸው ምክንያት ተጨማሪ የዩክሬን ከተሞች እና መንደሮች በቦምብ እንዲደበደቡ ፈቅደዋል።

NATO ዩክሬንን ለመከላከል እርምጃ ባለመውሰዱ በጦርነቱ ምክንያት ለሚሞቱ የአገራችን ዜጎች ሕይወት ተጠያቂ ነው። "

ለምንድነው NATO የዩክሬንን አየር ማይዘጋው ?

NATO በምድርም ሆነ በአየር ወደ ዩክሬን የመግባት ፍላጎት የለውም።

ለNATO ውሳኔ ምዕራባውያን ባለሥልጣናት እንደምክንያት የሚያስቀምጡት በዩክሬን ከበረራ ነጻ የሆነ ቀጠና ከተከለለ የNATO አውሮፕላኖች ጥሰት በሚፈጽሙ የሩሲያ ተዋጊ አውሮፕላኖች ላይ ጥቃት መሰንዘር ይችላሉ።

ይህ ደግሞ 3ኛው የዓለም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።

@tikvahethiopia
#Ukraine

ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ወዳጅ የሆኑ ሀገራት (አሜሪካ እና አጋሮቿ) ፕሬዜዳንቱ በሩሲያ ሃይሎች ቢያዙ ወይም ቢገደሉ በእሳቸው ቦታ ላይ ስለሚኖረው ‘የመተካካት ሂደት' እየተወያዩ መሆናቸውን ኒውዮርክ ታይምስ ዛሬ አስነብቧል።

አሜሪካ እና አጋሮቿ ሩስያ የሚታዘዝላትን መንግስት በኬዬቭ እንዳታስቀምጥ ስጋት አላቸው ተብሏል። ለሚቀመጠው መንግስትም እውቅና እንደማይሰጡ እና ይህም እንዳይሆን እንደሚከላከሉ ነው አቋማቸው።

ከዚህ ቀደም የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፕሬዜዳንት ቮልድሚር ዜሌስንኪ የምትመራውን ዩክሬን " የምዕራቡ ዓለም አሻንጉሊት " ሲሉ የጠሯት ሲሆን የዩክሬን ጦር ከአስተዳደራቸው ስልጣን እንዲነጥቅና እንዲቆጣጠር ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል።

አሁንም በዩክሬን እና በሩስያ መካከል ጦርነቱ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የዩክሬኑ ፕሬዜዳንት ህዝባቸው እንዲፋለም ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

በተጨማሪ " ዓለም ለሩስያ ሮኬቶች እና አውሮፕላኖች የአየር ቀጠናችንን የመዝጋት ኃይል አለውና ይዝጋልን ፤ የዩክሬንን ሰማይ አስተማማኝ ለማድረግም የጦር አውሮፕላኖች ያስፈልጉናል " የሚል ጥሪ እያቀረቡ ነው።

ትላንት ቭላድሚር ፒቲን በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላ ለማድረግ የሚሞክር የትኛውም ኃይል በጦርነቱ ውስጥ ተሳትፎ እንዳደረገ እንደሚታይ እና እንዲህ ያለው እርምጃ ለአውሮፓ እና ለዓለም አስከፊ መዘዝ የሚያስከትል እንደሆነ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Ukraine

የዩክሬን መንግሥት ስንዴ፣ አጃ እና መሰል የእህል ምርቶች ከሀገር ውጭ ለገበያ እንዳይቀርቡ ማገዱ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

የግብር እና ምርቶችን የሚመለከተው አዲሱ ሕግ ዩክሬን ውስጥ የተደነገገው በዚህ ሳምንት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

በአሁን ሰዓት ከሩስያ ጋር በጦርነት ላይ የምትገኘው ዩክሬን የምድራችን ከፍተኛ የስንዴ አምራች ሀገር ናት።

በተጨማሪ ዓለማችን ግማሹን የሱፍ አበባ እና ከዚህ ሰብል የሚገኙት ዘይትና ሌሎች ምርቶችን የምታገኘው በአሁን ሰዓት ጦርነት ላይ ካሉት 2ቱ ሀገራት ነው።

ዩክሬን በበቆሎ ምርቷም በዓለማችን የምትታወቅ ሀገር ናት።

@tikvahethiopia