TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለነገ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን ሸገር ራድዮ ዘግቧል። ስብሰባው የተጠራው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ቅዳሜ ባጸደቀው የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና አሠራር አዋጅ ላይ ለመነጋገር ነው ተብሏል። በርካታ የጋራ ቃል ኪዳን ስምምነቱን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ የጸደቀው ቀደም ሲል ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ከተስማማንበት መንፈስ ውጭ ነው በማለት እንደሚቃወሙት በጋራ ባወጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

Via #ShegerFM/wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አውቶብሱ የተገለበጠው የሰሌዳ ቁጥሩ ይፋ ያልተደረገ ኮድ 3 አ/አ መኪና ለመሸሽ ሲሞክር ነው!

እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ጀርባ በሚገኝው ድልድይ ውስጥ የመውደቅ አደጋ የገጠመው የከተማ አውቶብሱ ምክንያት ለጊዜው የሰሌዳ ቁጥር ይፋ ያልተደረገ ኮድ 3 አ.አ መኪና ለመሸሽ ሲል እንደሆነ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች የኮምንኬሽን ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለሽገር ራድዮ አስረድተዋል።

አውቶብሱ የተለመደ የመስመር ቁጥር ያልተሰጠው አዲስ ስምሪት እንደሆነም ታውቋል። መነሻውንም ከሽሮሜዳ አድርጎ ወደ ካዛንችስ እየሄደ እንደነበርም ነው ባለሙያው የተናገሩት። አደጋው ያጋጠመው አንበሳ የከተማ አውቶብስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- አ/አ 68377 እንደሆነ ታውቋል። በዚሁ አደጋም 31 ሰዎች ብርቱ ጉዳት እንደገጠማቸው ተሰምቷል።

ካሰቡበት ለመድረስ #በአውቶብሱ ተሳፍረው አደጋው ያገኛቸው ኢትዮጵያውያንም ወደ ጥቁር አንበሳ ዘውዲቱ እና አቤት ሆስፒታል መወሰዳቸውን ባለሙያው ተናግረዋል። በደረሰው አደጋ እስካሁን የ2 ሰው ህይወት አልፏል ተብሏል። የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር ይችላል ያሉት የኮምንኬሽን ባለሙያው ናቸው።

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
912 ሺህ 292 ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዘዋውረዋል!

በ2011 ዓ/ም የ10ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ወደ ቀጣይ ክፍል የተዘዋወሩት 912 ሺህ 292 ተማሪዎች ሲሆኑ ከተዘዋወሩት ተማሪዎች መካከል 750 ሺ 174 ወንዶች ናቸው፤ 162 ሺ 118 ተማሪዎች ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል። በአጠቃላይ ወደ 11ኛ ክፍል ከተዘዋወሩ ተማሪዎች መካከል የሴቶች ድርሻ 17.77 በመቶ መሆኑን ከአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የባለፈው አመት የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 2.71 እና ለሴቶች 2.57 እንደበር ይታወሳል፡፡ በግል ለተፈተኑት ወንዶች 3.43 እና ለሴቶች 3.14 የማለፊያ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የኤጀንሲው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኙ የአዲስ አበባ ቆሬ አካባቢ አደጋ፦

[ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1]

- አደጋው የደረሰው 5:30 አካባቢ ከብስራተ ገብርኤል ወደ ጀሞ ሲሄድ የነበረና አጠና የጫነ IVECO ግልባጭ መኪና ቆሬ ዓለም ሰላም ድልድይ ውስጥ ባሉ ቤቶች ላይ ወድቆ ነው።

- በአደጋው የሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏፋ። በአንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ከሟቾች ውስጥ የ11 ወር ህፃንና ንፍሰጡር ሴትም ይገኛሉ። ነፍሰጡር ሴቷ የ25 ዓመት ወጣት እና የህፃኑ አክስት እንደሆነች ተገልጿል።

- የ28 ዓመት ወጣት የሆነው አሽከርካሪም በአደጋው ህይወቱ አልፏል።

- የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

#ShegerFM #EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#attention አሁንም በአንዳድን የማንቡክ አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ እየተገለፀልን ከቤተሰቦቻችን እየተገለፅልን ነው። በአካባቢው የተፈጠረውንና እየተፈጠረው ያለውን ዝርዝር ጉዳይ ከቤተሰቦቻችን ጠይቀን፤ ተጨማሪ መረጃዎችን አካተን እንድታነቡት እናደርጋለን። ለሁሉም ግን የሚመለከታችሁ አካላት [የፀጥታ ኃይሉ] የአካባቢውን ደህንነት እንድታስጠብቁ የቲክቫህ ማንቡክ ቤተሰቦች አሳስበዋል።…
የማንቡክ ከተማ ሰላም መደፍረስ...

[በሸገር ኤፍ ኤም 102.1]

- ለማንቡክ ከተማ ፀጥታ መደፍረስ መነሻው ከቀናት በፊት የተፈፀመን ግድያ ተከትሎ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ የተፈፀመ የበቀል ግድያ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

- የበቀል ጥቃት የተፈፀመባቸው ወገኖችም አፀፋውን ለመስጠት ትናንት ረፋድ ላይ መሳሪያ ታጥቀው ወደማንቡክ ከተማ መጥተው ነበር። በመከላከያ ኃይል ምክር ወደመጡበት ተመልሰው ነበር።

- እኚሁ ሰዎች አመሻሽ ላይ በከተማው ድርቻ ላይ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል። በጥቃቱም በከተማው ዳርቻ ያሉ ቤቶች በእሳት ጋይተዋል። ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከጥቃት ፈፃሚዎቹ መካከል የተወሰኑ ሰዎች ተገድለዋል።

- የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የፀጥታ መደፍረስ ምክንያቱ እውነት እንደሆነ አረጋግጠዋል። ችግሩ መከሰቱንም አምነዋል። ምክትል አስተዳዳሪው የሰው ህይወት መጥፋትን በተመለከተ ማጣራት እየተደረገ ነው ብለዋል። የተወሰኑ የሳር ቤቶችም ተቃጥለዋል ሲሉ ገልፀዋል። መከላከያ ገብቶ ሁሉንም ነገር አረጋግቷል።

#ShegerFM #ማህሌትታደለ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

"የአሜሪካ መንግስት ለግብፅ እያደላ ነው" - ዴቪድ ሺን

በኢትዮጵያና በቡርኪና ፋሶ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዴቪድ ሺን የሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል ድርድርን አስመልክቶ የአሜሪካ መንግሥት ለግብጽ እያደላ ያለ ይመስላል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ዴቪድ ሺን ከሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ፣ግብጽ እና ሱዳን እያካሄዱ ባሉት ድርድር ዙርያ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በዶናልድ ትራምፕ ተወክሎ በታዛቢነት መግባቱን እንደሚያውቁ ጠቅሰው፣ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ እስከ መስጠት መድረሱ ግራ እንዳጋባቸው በብሎጋቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

የትሬዥሪ መምሪያው ኃላፊ ስቲፈን ምኑቺን ባለፈው አርብ ይፋ ባደረጉት መግለጫ በአሜሪካ አደራዳሪነት ተደረሰበት ያሉትን ስምምነት ግብጽ ለመፈረም ዝግጁ መሆኗን በአድናቆት ማውሳታቸው እንግዳ ነገር ነው ብለዋል ዴቪድ ሺን፡፡

ተደራዳሪዎቹ አካላት ስምምነት ላይ ስለመድረሳቸው አንዳችም በይፋ የሚታወቅ ነገር አለመኖሩን የጠቀሱት አምባሳደር ሺን መግለጫው ድርድሩ በስምምነት ሳይቋጭ የመጨረሻ ሙከራና ግድቡን ውሃ የመሙላት ሥራ መካሄድ የለበትም ሲል ኢትዮጵያን ማስጠንቀቁ አስገራሚ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ስምምነቱን ለመቀበል ዝግጁ ስለመሆኗ ምልክት እንኳ እንዳልሰጠች፣ ሌላው ቀርቶ ሱዳንም ስምምነቱን መቀበል አለመቀበሏን እንዳላሳወቀች አምባሳደር ዴቪድ ሺን አስታውሰዋል፡፡

በእንዲህ ዓይነቱ ድርድር ላይ ሚና ሊኖረውና መግለጫ ሊሰጥም የሚገባው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ሆኖ ሳለ፣ የግምጃ ቤቱ መምሪያ በኢትዮጵያ ላይ ጫና የሚያሳድር መግለጫ ማውጣቱ አሜሪካ ለግብጽ እያደላች ነው የሚል ጥርጣሬ እንደሚያሳድር ዴቪድ ሺን በብሎጋቸው ጽፈዋል፡፡

#ShegerFM #ዘከርያመሐመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠቅላይ ዐቃቢ ህጉ እና የንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል!

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት የሚከተለውን ሹመት ሰጥተዋል፡፡

በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፦

1. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
2. ወ/ሮ የአለም ፀጋዬ
3. ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ
4. አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ
5. አቶ ባጫ ጊኒ
6. አቶ ይበልጣል አዕምሮ
7. አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ
8. አቶ ነብያት ጌታቸው
9. አቶ ተፈሪ መለስ ተሹመዋል፡፡

እንዲሁም፦

1. አቶ አድጐ አምሳያ
2. አቶ ጀማል በከር
3. አቶ አብዱ ያሲን
4. አቶ ለገሠ ገረመው
5. ወ/ሮ እየሩሳሌም አምደማርያም እና
6. አቶ ሽብሩ ማሞ

በአምባሳደርነት ማዕረግ መሾማቸውን የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

#ShegerFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በአንጋፋው የማስታወቂያ ባለሞያ አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ ሕልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል፡፡

ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባል የነበሩት አቶ ውብሸት ቡድኑ ወደተለያዩ ሃገራት በተጓዘበት ጊዜ የቡድኑን መንፈስ በማነቃቃት ጎልህ አስተዋፅኦ ነበራቸው ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ በተለይ በብሮድካስት ሚድያ ማስታወቂያ ፈር ቀዳጅ ለነበሩት ለአቶ ውብሸት ቤተሰቦች፣ ጓደኞች እና ለኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባላት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ ለሁሉም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

#ShegerFM

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየደረሰባት ላለው የኢኮኖሚ ቀውስ ማቅለያ 150 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ኢትዮጵያ ለቡድን 20 አባል ሀገራት ጥሪ አቅርበች። ኢትዮጵያ ላለባት ብድር የወለድ ስረዛ እንዲደረግላትም አባል አገራቱን ጠይቃለች፡፡

#ShegerFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በረራ ያቋረጠባቸው መዳረሻዎች ወደ 72 ከፍ ማለታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል፡፡ በሚቀጥለው ሳምንትም ሁኔታው እየታየ ተጨማሪ መዳረሻዎችም ሊቋረጡ ይችላሉ ተብሏል፡፡

#SHEGERFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተገነቡት መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የወጣላቸው 52,229 የዕጣ ዕድለኞች ዛሬ ቁልፍ እንደሚረከቡ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በተጨማሪ 22,915 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችም እንዲሁ ቁልፍ እንደሚረከቡ ከሬድዮ ጣቢያው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የአ/አ ከተማ አስተዳደር የገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ሲያስረክብ ይህ 13ኛው ዙር ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአዲሰ አበባ ማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ የቁልፍ ፣ የካርታ እንዲሁም የውል ርክክብ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት እይተካሄደ ይገኛል።

#ShegerFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ #አጽድቋል። ረቂቅ አዋጁ የተወሰኑ ማስተካከያዎች እንደተደረጉበት ተመላክቷል። አዋጁ በ1 ድምፀ ተቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ " አዋጅ ቁጥር 1334/2016 " ሆኖ ነው የጸደቀው። የጸደቀው አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት…
#Ethiopia

የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በዛሬው እለት ጸድቋል።

ስለ አዋጁ ...

➡️ በልማድ ሲከበር የቆየውን " ግንቦት 20 " ብሔራዊ በዓልነቱ #አስቀርቷል፡፡ 

➡️ የሰማዕታትን ቀን ( #የካቲት_12 ) እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ( #ህዳር_29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ #ታስበው ይውላሉ።

➡️ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ፣ የሰንደቀ አላማ ቀን ፣ የሴቶች ቀን ፣ የአፍሪካ ቀን ሌሎችም ታስበው ይውላሉ።

➡️ የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ይከበራል።

➡️ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ ያለባቸው ተቋማት ዝርዝር ተቀምጧል።

በዚህም  ፦
° የውሃ
° የመብራት
° የስልክ
° ሚዲያዎች (ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ)
° የጤና ተቋማት እና መድሃኒት ቤቶች
° መከላከያ
° ፖሊስ
° ደህንነት
° የእሳት አደጋ መከላከል
° የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች
° ነዳጅ ማደያዎች
° ሙዝየሞች ፣
° ፓርኮች ክፍት ሆነው ከሚውሉት ውስጥ ናቸው።

ስለ አዋጁ ምን ጥያቄ ተነሳ ?

አንድ የምክር ቤት አባል ፦

" የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ተከብረው ከሚውሉት በዓላት ለምን አልተካተተም ? ለምን ታስቦ ከሚውል ውስጥ ተካተተ ? ምክንያቱም ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ሀገር ነች !! ታስቦ ይውላል እና ተከብሮ ይውላል የሚለው የተለያየ አጀንዳ አለው " የሚል ጥያቄ አንስተው ነበር።

የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ከኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ አንድ በዓል እንዲከበር እና ታስቦ እንዲውል የሚያደርገው የሚያመጣው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ተጠንቶ ነው ብለዋል፡፡

" ኢኮኖሚያችንስ ? " ሲሉ የጠየቁት ወ/ሮ ወርቀሰሙ " ሁል ጊዜ ስራ እየዘጋን ፤ በዓል እያከበርን መዋል በኢኮኖሚው ላይ የሚያመጣው ከፍተኛ ጫና አለ። ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል ታስቦ የሚውል በተለያዩ ነገሮች ደምቆ የሚውል ሊሆን ይችላል በሚል ነው በታሳቢነት እንዲቀጥል የተደረገው " ሲሉ አስረድተዋል።

#ShegerFM #TikvahEthiopia #HoPR

@tikvahethiopia
#Sudan #Ethiopia

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ ሱዳን ከኢትዮጵያ በቀን የምትወስደው የኤሌክትሪክ ኃይል ከ200 ሜጋዋት ወደ 50 ሜጋዋት መውረዱን ገለጸ።

በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትወስደው የኤሌክትሩክ ኃይል በእጅጉ መቀነሱን ተነግሯል፡፡

ሱዳን #ጦርነት_ውስጥ_ከመግባቷ_በፊት ከኢትዮጵያ የምትገዛው የኤሌክትሪክ ኃይል በቀን እስከ 200 ሜጋዋት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን 50 ሜጋዋት እና ከዚያ በታች ሆኗል ሲል አገልግሎቱ አስረድቷል፡፡

ለሱዳን የሚቀርበው ኃይል ከመውረዱም በላይ " ለተጠቀሙት የኤሌክትሪክ ኃይል እየከፈሉ አይደለም " ብሏል።

በታሰረው ውል መሰረት #ለተጠቀሙበት_ካልከፈሉ አገልግሎቱን ማቋረጥ የሚቻል ቢሆንም ግንኙነቱ እንዳይሻክር ኢትዮጵያ ይህንን አላደረገችም ሲል ገልጿል።

ኢትዮጵያ ከሱዳን ከጅቡቲ እና ከኬኒያ የኃይል ትስስር ያላት ሲሆን በቀን እስከ ሁለት ቴራ ዋት ሀወር ለሶስቱ ሀገራት ኃይል እንምድታቀርብ ተነግሯል።

ጅቡቲ የምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል አብዛኛው ከኢትዮጵያ የሚሄድ ሲሆን ኬኒያም ከምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል 10 ከመቶ ከኢትዮጵያ የሚሄድ ነው ተብሏል፡፡

#ShegerFM

#Sudan #Ethiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት ፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት አዋጅ በ4 ተቃውሞ በ6 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

አዋጁ ፤ ከዚህ በፊት በልማት ተነስተው የካሳ ክፍያ ያላገኙትን እና አሁንም ድረስ እየጠበቁ ያሉ የልማት ተነሺ ሰዎችን እንደማያካትት ተሰምቷል።
 
ከምክር ቤት አባላት ምን ተጠየቀ ? ምን ምላሽ ተሰጠ ?

Q. ከዚህ በፊት በርካታ የካሳ ክፍያዎች አዲሱ የካሳ ክፍያ እና ተነሺዎች መልሶ የሚቋቋሙበት አዋጅ እስከ ሚፀድቅ ድረስ እንዲቆዩ ተደርገዋል ይህ አዋጅ እንዴት ሊያስተናግዳቸው አስቧል ?
 
Q. ካሳ የመክፈሉ ኃላፊነት ለክልሎች በአዲሱ አዋጅ መስጠቱ ለሰራተኞቻቸው እንኳን ደሞዝ መክፈል ያልቻሉ ክልሎች ባሉበት ሰዓት እንዴት እንዲህ አይነት ክፍያ ሊከፍሉ ይችላል ?

Q. አንዳንድ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች በተመለከተ ለፌደራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት መስጠቱ አግባብነት የለውም። ይህ እንዴት ሊታይ ታስቦ ነው ለከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ችግሮችን ለማየት ስልጣን የተሰጠው ?


ሌላው ፤ ከዚህ በፊት ከፍተኛ የሆነ ምዝበራ ይፈፀም የነበረው በክልሎችና በወረዳዎች በሚጣሉ የካሳ ተመኖች ነበር አዋጁ ይህ እንዲባባስ ሊያደር ይችላል የሚል ስጋት ተነስቷል።
 
በተ/ም/ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፥ ከዚህ በፊት ከልማት ጋር በተያያዘ ያልተከፈሉ ክፍያዎች የሚዳኙት በቀድሞ አዋጅ መሰረት ነው ብለዋል።

አዲሱ አዋጅ የሚመለከተው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ያሉ የካሳ ክፍያዎች ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
 
በክልሎች ያለው በጀት ጉድለት እንዳለ ሆኖ ለልማት ተነሺዎች የሚከፈለው የካሳ ክፍያ የሚፈፀመው የፌደራል መንግስት ለክልሎች በሚሰጠው የበጀት ድጎማ እንደሆነ ተመላክቷል።

በክልሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሲታቀዱ ለክልሎች የሚመደበው በጀት ላይ የካሳ ክፍያ ታሳቢ ይሆናል።
 
ከዳኙነቱ ጋር በተያያዘም ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሌላኛው የቋሚ ኮሚቴ አባል ፤ " ውሳኔውን ለመስጠት የተፈለገው ልማቶች ሲካሄዱ ፈጣን ፍርድ ለማሰጠትና ሀብትን ከምዝበራ ለመታደግ በማሰብ ነው " ብለዋል።

#ShegerFM
#HoPR
 
@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" የቀበሌና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ  4,000 መኖሪያ ቤቶች ተዘጋጅተዋል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበባ ይካሄዳል በተባለው 2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ለሚነሱ የግል ባይዞታዎች 5 ቢሊዮን ብር ካሳ እና 100 ሄክታር  ምትክ መሬት መዘጋጀቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ከሚነሱት ውስጥ ፦

➡️ 80 በመቶው የቀበሌ ቤት፣

➡️10 በመቶው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቶች ነዋሪዎች

➡️ 10 በመቶው የግል ባለይዞታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የቀበሌ እና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ 4,000 መኖሪያ ቤቶች  መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

ለስራ እድል ፈጠራ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ አካላት የማምረቻ፣ መሸጫ እና ምርት መያዣ ሼዶች በቀበሌ እና በንግድ በቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች ተደራጅተው የንግድ ቦታ እንዲገነቡ  እንዲሁም በአነስተኛ ሱቆች ሲሰሩ ለነበሩ 500  የሱቅ ኮንቴነሮች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት በ8 ኮሪደሮች 132 ኪሎሜትር ርዝመት እና ከ 2,817 ሄክታር  ቦታ ለማልማት ተቅዷል ብለዋል።

የሁለተኛው ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት መስመሮች የትኞቹ ናቸው ?

1. ካዛንቺስ፣ መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ፣ ቸርችል፣ አራት ኪሎ፣ እስጢፋኖስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት 1000 ሄክታር ቦታ ስፋት እና 40.4 ኪሎሜትር ርዝመት ፤

2. ሳውዝጌት፣ መገናኛ ፣ ሃያሁለት፣ መስቀል አደባባይ የኮሪደር ልማት 128.7 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 7.1 ኪሎሜትር ርዝመት፤

3. ሲኤምሲ፣ ሰሚት ጎሮ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ቪአይፒ ተርሚናል፣ አዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚብሽን ማዕከል የኮሪደር ልማት 146 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 10.8 ኪሎሜትር ርዝመት፤

4. ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ፣ ፉሪ አደባባይ ኮሪደር ልማት 565 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 15.9 ኪሎሜትር ርዝመት፤

5. አንበሳ ጋራዥ፣ ጃክሮስ ጎሮ ኮሪደር ልማት 16.58 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 3.1 ኪሎሜትር ርዝመት

6. አራት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማርያም፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል የኮሪደር ልማት 314 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 13.19 ኪሎሜትር ርዝመት

7. የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት 372.5 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 20 ኪሎሜትር ርዝመት፤

8. እንጦጦ፣ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር ልማት 274 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 21.5 ኪሎሜትር ርዝመት፤

በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል።

#AddisAbaba #ShegerFM

@tikvahethiopia