TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቤጂንግ እና የዋሽንግቶን ውጥረት ?

አሜሪካ እና ቻይናን ውጥረት ውስጥ የከተታቸው የታይዋን ጉዳይ ነው።

ቻይና ታይዋን #ወደ_እናት_አገሯ መመለስ ያለባት አፈንጋጭ ግዛቷ እንደሆነች ነው የምታስበው

ይህንንም ለማሳካት ወደፊት ቤይጂንግ ኃይል መጠቀምን እንደ አንድ አማራጭ ታየዋለች። 

አሜሪካ ደግሞ ከቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ሲሆን፣ ከታይዋን ጋር ግን “ይፋዊ ያልሆ ጠንካራ” ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት አላት ይባላል።

ረጅም ጊዜ ይሄ ጉዳይ ሲንከባለል እና በቻይና እና አሜሪካ መካከል ምልልስን ሲፈጥር ቆይቷል።

አሁን ግን የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን እንደሚጎበኙ ማሳወቃቸው የለየት ውጥረትን ፈጥሯል።

ፔሎሲ በአገሪቱ የሥልጣን አርከን ውስጥ ከፕሬዝዳንቱ እና ከምክትላቸው ቀጥሎ ሦስተኛ ሰው ናቸው።

ቻይና ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ እስከ ወታደራዊ እርምጃ ድረስ ልትወስድ እንደምትችል ሲነገር ነበር።

ምንም እንኳን ቻይና የአሜሪካዋ 3ኛ ሰው ታይዋንን እንዳትጎበኝ ብታስጠነቅቅም ከጥቂት ሰዓት በፊት ታይዋን ደርሰዋል።

አቀባበልም ተደርጎላቸዋል።

የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉብኝቱን ለቻይና ክብር አለመስጠታቸው ማሳያ ነው ፤ ለቻይና ተገንጣይ ቡድኖች እውቅና መስጠት ነው ብሏል።

ሚኒስቴሩ በፔሎሲ ውሳኔ ማዘኑን አስታውቋል፡፡

ለሉአላዊነትና ደህንነትን ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ለሚመጣው መዘዝ አሜሪካ እና ታይዋን ሃላፊነቱን ይወስዳሉ ብሏል።

#RT #CGTN #BBC

@tikvahethiopia