TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኮማንደር ዋለልኝ⬆️"እስካሁንም በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ምንም አይነት የመገናኛ ሬዲዮም ሆነ ቦምብ የለም።”

#BahirDar #ባህር_ዳር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BAHIRDAR

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት በየአጥቢያዎቹ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ጸሎተ ምህላ አወጀ፡፡ ሀገረ ስብከቱ ለመስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ከፊታችን ሰኞ መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ጸሎተ ምህላ አውጇል፤ ለመስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመላከተው የፀሎተ ምህላው ዓላማ በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ የሚደርሰውን መከራ፣ ግፍ እና መሰደድ አስመልክታ ለፈጣሪዋ መልዕክት ለማቅረብ ነው፡፡

ከጸሎተ ምህላው እና ከሰልፉ በኋላ በእለቱ 10፡00 ሰዓት ላይ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ስለወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ውይይት ይደረጋል ተብሏል በመግለጫው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BAHIRDAR_INDUSTRIAL_PARK

የባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያው የግንባታ ምእራፍ ተጠናቆ በመስከረም ወር መጨረሻ ሥራ እንደሚጀምር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አማረ አስገዶም እንደገለፁት፣ የፓርኩ የመጀመሪያው ምእራፍ ግንባታ በ75 ሄክታር መሬት ላይ በውሉ መሰረት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። በዚሁ ምእራፍ የተገነቡት የፋብሪካ ሼዶችም ስምንት ሲሆኑ፣ በመጀመሪያው ዙር ለአራት ሺ በሁለተኛው ዙር ደግሞ ለስምንት ሺ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገለፃ፤ በመጀመሪያው ምእራፍ የፓርኩ ግንባታ የሚያስፈልገው የኃይል መጠን ስምንት ሜጋ ዋት በመሆኑ በኃይል አቅርቦቱ ዙሪያ ጥናት ተሰርቶ ተጠናቋል። የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰጪ አካሉም የኤሌክትሪክ ምሰሶ ተከላዎችን ጀምሯል። በዚህ ወር መጨረሻም ለፓርኩ የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ይቀርባል ተብሎ ይታሰባል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BAHIRDAR

"የባህር ዳር ነዋሪ ነኝ ፍርድ ቤት አካባቢ ዛሬ የእነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ቀጠሮ ነበር። ትንሽ ቆይቶ የተቃውሞ ድምፅ ሰማን፤ እስረኞች ይፈቱ የሚል። እናም ልንወጣ ስንል አስለቃሽ ጭስ ተተኮሰ እናም መውጣት አልቻልንም። እስከ ቤታችን ድረስ አይናችን እየተቃጠለ፤ አፋችንም ታፍኖ ነበር የደረስነው።" DAGI/TIKVAH-ETH/

POHTO: ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopua
#BAHIRDAR

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በባህር ዳር ከተማ የተጣለው የ14 ቀን እንቅስቃሴ እገዳ ዛሬ 23/07/2012 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን እገዳውን በማይተገብሩት ላይ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አሳውቋል።

ምንጭ፦ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BahirDar

በባሕር ዳር ከተማ ውሃ ተበክሏል እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ #ሀሰት መሆኑን የባህር ዳር ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ለአብመድ ገልጿል፡፡

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የውሃ እና ፍሳሽ ባለሙያዎች በየዕለቱ በሁሉም ቦታዎች ማለትም (ታንከር ላይ ፣ መሥመር ላይና ቤት ለቤት በመዞር) የፊዚካል ፣ ባዮሎጂካል እንዲሁም የኬሚካል ናሙና ምርመራ ይደርጋሉ።

ዛሬ እና ትናንት በተደረገው የናሙና ምርመራ ምንም ችግር እንደሌለ መረጋገጡን የከተማው ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት አሳውቋል።

ዛሬ ህዳር 25/2013 ውሃ ተበክሏል በሚል ሥጋት ጥቆማ በተደረገባቸው የከተማዋ አካባቢዎች ናሙና ተወስዶ ምንም አይነት ችግር አለመኖሩ ተረጋግጧል።

የከተማው ውሃ በቀላሉ የሚበከል አለመሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይም አጠራጣሪ በሆኑ አካባቢዎች የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገ ነው።

ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ/ም በኋላም የጥበቃ ሥራው መጠናከሩ ተገልጿል።

ሕዝቡ እውነቱን ተገንዝቦ 'ያለምንም መረበሽ' የእለት ተዕለት ተግባሩን እንዲከውን የከተማው ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት መልዕክት ተላልፏል። (AMMA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የ125ኛው ዓድዋ የድል በዓል እየተከበረ ይገኛል :

#Menelik_II_Square

125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በሚኒሊክ አደባባይ በተለያዩ ትዕይንቶች ታጅቦ እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ ጀግኖች አርበኞች፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም የጉዞ አደዋ የዘንድሮ ተሳታፊዎች እና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

#MeskelSquare

የአድዋ የድል በዓል በመስቀል አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፥ የፌዴራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች፥ የጥንት አርበኞች፥ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ፥ ከተለያዩ የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች የታደሙ 20 ሺህ የሚሆኑ ፈረሰኞች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

#Debremarkos

በአሁኑ ሰዓት የጎጃም ደብረማርቆስና አካባቢው ማህበረሰብ የአደዋን በዓል በንጉስ ተክለሃይማኖት አደባባይ በመገኘት በማክበር ላይ ይገኛል።

#Bahirdar

በባህርዳር ከተማ 6ቱ ክፍለ ከተሞች በአንድነት 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት እያከበሩ ነው።

በዓሉ የአማራ ክልል ርዕሰመስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

#Gondar

የአድዋ ድል በዓል በጎንደር ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በበዓሉ አባት አርበኞች፣ ወጣቶች፣ ልዩ ልዩ የጸጥታ አባላትና ከተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተወጣጡ ነዋሪዎች ታድመውበታል።

More : @tikvahethmagazine
#Bahirdar

ባህር ዳር ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

የከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ፥ "ከተማችን ሰላም ናት ወደመደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች" ነው ያለው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Bahirdar

በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ማታ ማታ የሚኒቀሳቀሱ ባጃጆች ቁጥር እንዲወሰን ተደረግ።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ወንጀል እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ እንደሆነ ተነግሯል።

እንደሀገር ሆነ እንደ ክልል የተከሰተውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢ መንገድ ለመምራት በባህር ዳር በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የባጃጅ ማህበራት ከከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ጽ/ቤት፣ ከፖሊስና መሰል የህግና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በሌሊት አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጆች ተጠያቂነት ባለው አሰራር ታቅፈውና ለቁጥጥር እንዲያመች በቁጥር ተወስነው እንዲሰሩ መደረጉን የየማህበራቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረት ከስምንት የባጃጃ ማህበራት ውስጥ በስነ-ምግባር እና ለማህበረሰቡ ቅንና ታማኝ አገልግሎት ከሚሰጡ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መካከል 120ዎችን በመመልመልና ከምሽቱ 3፡00 እስከ ንጋት 11፡00 ድረስ በሁሉም ቀበሌዎች እየተንቀሳቀሱ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።

ይህ ለከተማው ሰላምና፣ ለማህበረሰቡ ደህንነት ሲባል የሚደረግ በመሆኑ የተመደቡ ባጃጆች ተጠያቂነት እንዲኖራቸው የማህበራቸውን ስምና አንፀባራቂ የደንብ ልብስ እንዲጠቀሙ፣ በዚያው ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር በኩል ለሚደረገው ተግባር ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉንም ገልፀዋል፡፡

ለዚህ ከተመደቡ ውጭ ማነኛውም ባጃጅ ከ3 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ እንደሌለበትና ይህን ውሳኔ ተላልፎ የተገኘ የባጃጅ አሽከርካሪ ካለ በህግ ይጠየቃል ተብሏል።

የተመደቡት 120 ባጃጆች ያለምንም ዋጋ ጭማሪና ያለ አድሎ በሌለበት ሁኔታ እንዲሰሩ በሚሰጡት አገልግሎትም እጥረት ካለ እየተገመገመ እንደሚስተካከል ከ #ባህርዳር_ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#BahirDar

ዛሬ በባህርዳር ከተማ በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለከተማ በህገወጥ መልኩ የተከዘነ በርበሬ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

በርበሬው ተከማችቶ የተገኘው በአፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በአዲስ አለም ቀበሌ መስኪዱ አካባቢ ነው::

በቁጥጥር ስር የዋለው በርበሬ በኩንታል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሲሆን በህብረተሰቡ ጥቆማ ነው ሊያዝ የተቻለው::

ባለሃብቱም ከንብረቱ ጋር በቁጥጥር የዋለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።

በባህር ዳር ከተማ ህገወጥ ነጋዴዎች እና ስግብግብ ነጋዴዎች የኑሮ ውድነቱን እንዲባባስ መንስኤ በመሆናቸው ህብረተሰቡ የዚህ አይነት ተግባራትን ሲያገኝ ለፖሊስና ለሚመለከተው አካል በመጠቆም ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል::

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara : " 4 ሚሊዮን ሕዝብ ለከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ተዳርጓል" የአማራ ክልል መንግስት 750 ኪሎ ሜትር በሚያካልል አካባቢ 5 ዞኖች በህወሓት ወረራ እንደተፈፀመበት ሪፖርት አደረገ። ክልሉ ይህን ያሳወቀው ዛሬ በባህር ዳር ከፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት ተወካዮች ጋር በመከረበት ወቅት ነው። የዛሬው ውይይት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አፋጣኝ የሰብዓዊ…
#BahirDar

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር ሕወሓት በተቆጣጠራቸው በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰሜን ወሎና በተወሰኑ የሰሜን ጎንደር አካባቢዎች ሰዎች በመድሀኒት እጥረትና በርሀብ እየሞቱ ነው ሲሉ ተናገሩ።

የክልሉ ፕሬዜዳንት ይህንን ያሉት ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ከዓለም አቀፍ የእርዳታ ለጋሽ ድርጅት ተወካዮች ጋር በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

አቶ አገኘሁ ተሻገር ፤ በደቡብ ጎንደር እና በደቡብ ወሎ ህወሓት ወረራ ፈፅሞ በወጣባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የህዝብ መጎሳቆል መፈጠሩን የተናገሩ ሲሆን ዓለም አቀፉ ረጂ ድርጅቶች በፍጥነት ሕወሓት ተቆጣጥሮ ባለባቸው አካባቢዎች "በርሀብና በህመም ላሉ 4 ሚሊዮን ዜጎች እንዲደርስላቸው" ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የUNHCR የኢትዮጵያ ኃላፊ ዶክተር ካትሪን ሶዚ ችግሩን መረዳታቸውን ገልጸው የመገናኛ ዘዴዎችና የደህንነት ሁኔታው ከተመቻቸ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

የWFP) ተወካይ የእርዳታ ማድረሻ ተሸከርካሪዎች 19 ብቻ መሆናቸውን ጠቁመው "በነዚህ ተሸከርካሪዎች 4 ሚሊዮን ህዝብ እደርሳለሁ ማለት አይታሰብም" ብለዋል፤ ያለውን ክፍተት ከሞላልን እርዳታ እናደርሳለን ሲሉ መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Bahirdar : በባህርዳር ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህገ-ወጥ ሽጉጥ እንዲሁም የብሬን፣ የክላሸና የሽጉጥ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋለ።

በባህር ዳር ከተማ ልዩ ቦታው ዳግማዊ ምንሊክ ክፍለ ከተማ ማርዘነብ ቀበሌ በተባለው ስፍራ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ፦
- 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ህገ-ወጥ ሽጉጥ፣
- 2ሺ 1መቶ የብሬን ጥይት፣
- 69 የክላሽ ጥይት እንዲሁም 222 የሽጉጥ ጥይቶች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።

የባህር ዳር ፖሊስ ፥ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው የአማራ ክልል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር መሆኑን ገልጿል።

የባህር ዳር ፖሊስ 9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ንብረቱ ሞት ፥ ህብረተሰቡ ከዚህ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊት እንዲቆጠብ ያሳሰቡ ሲሆን "ህገ-ወጥ ድርጊት ፈፃሚ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በምናውልበት ጊዜ ህዝቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል" ሲሉ ጥሪ አስተላፈዋል።

@tikvahethiopia
#Bahirdar : የባህርዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ መመሪያን ተከትለው ያልሰሩ የግል ትምህርት ቤቶችን አስጠነቀቀ።

መምሪያው በከተማው ላሉ ትምህርት ቤቶች በፃፈው ደብዳቤ ከዚህ ቀደም በትምህርት ቤት ክፍያ ጉዳይ ተከታታይ ውይይት መደረጉን አስታውሷል።

መስከረም 7/2014 ዓ/ም ትምህርት ቤቶቹ የተማሪ ወላጆችን ሰብስበው በክፍያ ዙሪያ ከወላጅ ጋር ተግባብተው በመመሪያው መሰረት ወላጅ ያመነበትን ክፍያ እንዲያስከፍሉና ወላጆችን ያወያዩበት ቃለጉባኤ የተሳታፊዎችን ፊርማ እና በቪድዮ የተደገፈ ማስረጃ ለትምህርት መምሪያው መረጃ አደራጅተው እንዲያሳውቁ በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት ተቋማቱ ዕድሉን እንዳልተጠቀሙበት ትምህርት መምሪያው በደብዳቤው ላይ ገልጿል።

አሁን ላይ ወላጆች የት/ቤት ክፍያ እንደተጨመረባቸው ይህ የተጨመረው ጭማሪም ወላጆች ያላመኑበት መሆን ለመምሪያው ቅሬታ እያቀረቡ እንደሚኙ ገልጿል።

ትምህርት መምሪያው ፥ ትምህርት ቤቶች የጨመሩት ክፍያ ከተማሪ ወላጆች ስምምነት ውጭና ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ከመስከረም 2014 ጀምሮ የተከፈለ ክፍያ ለቀጣይ ወራት ታሳቢ ተደርጎ በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ሲያስከፍሉ የነበረውን ክፍያ እንዲያስከፍሉ አሳስቧል።

ት/ቤቶቹ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ የማያደርጉ ከሆነ በቀጣይ የማስተማር ፍቃዳቸው እንደሚነሳ ፤ ከ2ኛ ሴሚኒስተር በኃላ ምንም አይነት ተማሪ በተቋማቸው የማይማርና ተቋማቱም እንደሚዘጋ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#Bahirdar : የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በባህር ዳር ከተማ በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ እየመከረ ይገኛል።

መድረኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የሚመራ ሲሆን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሁሉም ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የበላይ አመራሮች ተገኝተዋል።

የግንኙነት መድረኩ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል።

የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኘነት መድረክ የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ስርአትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት የተቋቋመ ነው።

መረጃው የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#BahirDar : በባሕር ዳር በአንድ ግለሰብ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ፥ በግሸ አባይ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ3 ሺህ በላይ ጥይትና ሌሎች የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ፖሊስ ጥቆማው የደረሰው ከማኅበረሰቡ መሆኑን
አመልክቷል።

በጥቆማው መሰረት ተጠርጣሪው ቤት ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ፍተሻ በማካሄድ በግለሰቡ መኖሪያ ውስጥ 2 ክላሽ ፣ ከ3 ሺህ በላይ የክላሽ እና የብሬን ጥይት፣ አንድ ኤፍዋን ቦንብ እና አንድ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿጻ።

የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነት በአግባቡ በማጣራት አድራሻቸውን ለፖሊስ እንዲያሳውቁም ጥሪ ቀርቧል።

Credit : AMC

@tikvahethiopia