TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Russia #Africa #Ethiopia

ኢትዮጵያ የነበረባት 163.6 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ ተሰረዘላት!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኢትዮጵያ የነበረባትን 163.6 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ መሰረዛቸውን ሞስኮ ታይምስ ዘግቧል። እንደዘገባው ሞዛምቢክ 40 ሚሊዮን ዶላር፣ ማዳጋስካር 89 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ታንዛኒያ መጠኑ ያልታወቀ የብድር መጠን ተሰርዞላቸዋል።

ምንጭ፦ እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AFRICA

በአፍሪካ 46 ሀገራት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠቂዎች ቁጥር 3,778 ደርሷል። 109 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። በተጠቂዎች ቁጥር ደቡብ አፍሪካ የቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች በሀገሯ 1,170 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ በቀጣዮቹ 12 ወራት 190 ሺ ሰዎችን በአፍሪካ ሊገድል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ አስጠንቅቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ የ47 ሃገራት ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት አስጠናሁ ባለው ጥናት ለወረርሽኙ አፋጣኝ ምላሽ እና ተገቢው ትኩረት ካልተሰጠ ስርጭቱ ሙሉ በሙሉ ሳይጠፋ ረጅም አመታትን ሊቆይ እንደሚችልም አስታውቋል፡፡

ከአሁን ቀደምም እንደ መንግስታት የዝግጁነት እና የምላሽ ሁኔታ ቢለያይም እስከ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ አስጠንቅቆ ነበር፡፡

በያዝነው ሳምንት ይፋ የሆነው የድርጅቱ ጥናት የቁጥጥር ስራዎች በታሰበው ልክ ውጤት የማያመጡ ከሆነ ወረርሽኙ በተከሰተበት በዚህ ዓመት ብቻ ከ29 እስከ 44 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ - #AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

አፍሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 105,100 ደረሱ። ከነዚህ መካከል 3,185 ሰዎች ሲሞቱ 42,643 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦

- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 20,185፣ ሞት 397 ፣ ያገገሙ 10,104

- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 15,786 ፣ ሞት 707 ፣ ያገገሙ 4,374

- አልጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 7,918 ፣ ሞት 582 ፣ ያገገሙ 4,256

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

አፍሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 131,760 ደርሰዋል። ከነዚህ መካከል 3,814 ሰዎች ሲሞቱ 55,145 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦

- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 27,403 ፣ ሞት 577 ፣ ያገገሙ 14,370

- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 20,793 ፣ ሞት 845 ፣ ያገገሙ 5,359

- አልጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 8,997 ፣ ሞት 630 ፣ ያገገሙ 5,277

#worldometers
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

አፍሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 137,677 ደርሰዋል። ከነዚህ መካከል 3,945 ሰዎች ሲሞቱ 58,225 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦

- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 29,240 ፣ ሞት 611 ፣ ያገገሙ 15,093

- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 22,082 ፣ ሞት 879 ፣ ያገገሙ 5,511

- ናይጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 9,302 ፣ ሞት 261 ፣ ያገገሙ 2,697

#worldometers
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

አፍሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 160,100 ደርሰዋል። ከነዚህ መካከል 4,522 ሰዎች ሲሞቱ 69,327 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦

- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 35,812 ፣ ሞት 755 ፣ ያገገሙ 18,313

- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 27,536 ፣ ሞት 1,052 ፣ ያገገሙ 6,827

- ናይጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 10,819 ፣ ሞት 314፣ ያገገሙ 3,240

#worldometers
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

አፍሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 172,183 ደርሰዋል። ከነዚህ መካከል 4,784 ሰዎች ሲሞቱ 75,830 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦

- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 40,792 ፣ ሞት 848 ፣ ያገገሙ 21,311

- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 29,767፣ ሞት 1,126 ፣ ያገገሙ 7,756

- ናይጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 11,516፣ ሞት 323 ፣ ያገገሙ 3,535

#worldometers
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

በመላው አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 216,479 ደርሷል፤ ከነዚህ መካከል 5,744 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 99,828 ሰዎች አገግመዋል።

ከፍተኛ የሰው ቁጥር በቫይረሱ የተያዘባቸው 5 ሀገራት ደቡብ አፍሪካ 58,568 ሰዎች ፣ ግብፅ 38,284 ሰዎች፣ ናይጄሪያ 13,873 ሰዎች ፣ አልጄሪያ 10,589 ሰዎች እና ጋና 10,358 ሰዎች ናቸው።

ኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት ...

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 21,023 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በ6ቱ ሀገራት የ674 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 6,651 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

በመላው አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከ270,000 አለፈ። ከነዚህ መካከል 7,251 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 125,625 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦

- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 80,412 ፣ ሞት 1,674፣ ያገገሙ 44,331

- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 49,219 ፣ ሞት 1,850 ፣ ያገገሙ 13,141

- ናይጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 17,335 ፣ ሞት 468 ፣ ያገገሙ 5,967

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA🏆

ከጥር 1 - ጥር 29 ቀን 2014 ድረስ በካሜሩን በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ላይ ሀገራቸው 🇪🇹 ኢትዮጵያን ወክለው የሚፋለሙ ተጨዋቾች ይፋ ሆነዋል።

(ዝርዝሩ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል)

More : @tikvahethsport
#AFRICA

#AFCON_2021 ውድድር ከወዲሁ ምድባቸው ማለፍ የቻሉ አራት ሀገራት ፦

🇨🇲 ካሜሩን
🇲🇦 ሞሮኮ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇧🇫 ቡርኪናፋሶ

ከምድቧ ማለፍ ሳትችል ቀርታ ከውድድሩ ቀድማ መሰናበቷ የተረጋገጠው ደግሞ ኢትዮጵያ 🇪🇹 ናት።

More : @tikvahethsport
#RUSSIA #AFRICA

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ወደ አፍሪካ ለሚገቡ የስንዴ ምርቶች ሁኔታዎችን እንደሚያመቻቹ አሳውቀዋል።

ፑቲን የስንዴ ምርቶች ወደ አፍሪካ መላካቸውን ለማረጋገጥ ሃገራቸው እንደምትሰራም ገልጸዋል፡፡

ይህን የገለፁት ከወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና ከሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ጋር ከጦርነቱ ጋር በተያያዙ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሶቺ ከተማ በተወያዩበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ወቅት ማኪ ሳል አፍሪካ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ቀጥተኛ ተሳትፎ ባይኖራትም በጦርነቱ ምክንያት ሰለባ መሆኗን ገልፀዋል።

በተለይ ከዩክሬንና ሩሲያ ይገቡ የነበሩ የግብርና ምርቶች እና ግብዓቶች ጉዳይ አፍሪካን ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር እንደዳረጋት አስረድተዋል።

ሩሲያን ጨምሮ የአፍሪካ አጋር የሆኑ ሁሉም ሃገራት የጣሏቸውንና በስንዴ እና በማዳበሪያ ላይ ያነጣጠሩ ማዕቀቦቻቸውን እንዲያነሱም ጠይቀዋል፡፡

የሩሲያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ሩድያ የምግዜም የአፍሪካ አጋር መሆኗን ገልፀው ከዩክሬን ወደ አፍሪካ ለሚገቡ የስንዴ ምርቶች በወደብ ላይ ለቀሩትም ጭምር ሁኔታዎችን እንደሚያመቻቹ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዜዳንት ፑቲን ሰው ሰራሽ #የአፈር_ማዳበሪያ ምርቶች አፍሪካ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ዝግጁ ስለመሆናቸውም አሳውቀዋል።

ከ40 በመቶ የሚልቀው የአፍሪካ የስንዴ ፍጆታ በዩክሬን እና በሩሲያ የስንዴ ምርቶች የሚሸፈን ነው፡፡

መረጃው የአል አይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በአሜሪካን ዋሽንግቶን ዲሲ የሚገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። - ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ከአሜሪካ የንግድ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይን ተገናኝተው ተውያይተዋል። የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥሩ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል። - ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ IMF…
#USA #AFRICA

ለ3 ቀናት የተካሄደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ሐሙስ ተጠናቋል።

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በጉባኤው ምን አሉ ?

- ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች በቅርቡ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች የሚያደርግት ጉብኝት እንደ ፕሬዝደንት የመጀመሪያው ነው። ቀኑን እና የትኞቹ ሀገራትን እንደሚጎበኙ ግን አላሳውቁም።

- አፍሪካ እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልፀው አሜሪካ ትኩረቷን እንደምትጨምርም ጠቁመዋል።

- ከፍተኛ አማካሪዎቻቸውን ወደ አፍሪካ እንደሚልኩ ገልፀዋል። ወደ አፍሪካ ከሚላኩት ውስጥ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን፣ የገንዘብ ሚኒስትሯ ጃነት የሊን እና የንግድ ሚኒስትሯ ጂና ሬይሞንዶ ይገኙበታል።

- በሚቀጥለው ዓመት ለሚደረጉ ምርጫዎች 165 ሚሊዮን ዶላር እንደሚመደብ ቃል ገብተዋል።

ፕሬዚደንት ባይደንና ባለቤታቸው ጂል ባይደን የአፍሪካ አገራት መሪዎችንና ቀዳማዊ እመቤቶቻቸውን በዋይት ሃውስ የእራት ግብዣ አድርገውላቸዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአሜሪካ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ሊሳተፍ ወደ አሜሪካ አቅንቶ የነበረው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ሀገር መመለሱን የጠ/ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ አመሻሹን አሳውቀዋል።

#ቪኦኤ #አምባሳደር_ሬድዋን_ሁሴን

@tikvahethiopia
#Russia #Africa

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ፤ በሁለተኛው የአፍሪካ ራሺያ የጋር ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሩስያ፤ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ይገኛል።

ልዑካን ቡድኑ ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በመገናኘት፣ በሁለቱ አገራት ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይም መክሯል።

ነገ ከሚጀመረው የሩስያ - አፍሪካ የጋራ ጉባኤ ጎን ለጎን ኢትዮጵያና ሩስያ 15 የሚደርሱ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶችን እንደሚፈራረሙ ፕሬዝዳንት ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ ገልጸውላቸዋል።

የትብብር ስምምነት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ፣ ኢትዮጵያ ከአቶሚክ ኃይል ኤሌክትሪክ ለማመንጨትና ለመጠቀም የሚያስችላት የትብብር ፍኖተ ካርታ እንደሆነ ፕሬዝዳንት ፑቲን ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ አገራት በሳይበር ደህንነትና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክ ለመተባበር ስምምነት እንደሚፈራረሙ ታውቋል።

" በሩስያ ቆይታዎ ወቅት የትብብር ስምምነት የምናደርግባቸውን የሰነዶች ፓኬጅ አዘጋጅተናል፤ ከነዚህም መካከል የመረጃ ደህንነት ስምምነት ፣ በአየር ትራፊክ ፣ በኢንፎርሜሽንና የግንኙነት ቴክኖሎጂዎች መስክ የመግባቢያ ሰነድ ፣ የአቶሚክ ኢነርጂን ለመጠቀም የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ፣ በጉምሩክ አገልግሎቶች ፕሮቶኮልና ሌሎች " ሲሉ ፕሬዚደንት ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ ተናግርዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ በበኩላቸው ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ግልጽ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

" ታሪካዊ ትሥሥራችንን መሠረት አድርገን ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን እና ኢኮኖሚያዊ ትብብራችንን ማሳደግ እንቀጥላለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ ዛሬ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
* የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማኅማትን፤
* የኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን
* የዲፕሎማቲክ ልዑካን ቡድኖች አባላትን በ "ወንጪ ዳንዲ ኤኮ ቱሪዝም መንደር" መቀበላቸውን የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ የAU እና ኢጋድ መሪዎችን እና ዲፕሎማቶችን ከመቀበል ባለፈ ውይይቶችን አድርገው እንደሆነ የተባለ ነገር የለም።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ከተጋሩ በኃላ በቀጠናው ሰፊ መነጋገሪያ ሆነዋል።

#Ethiopia #Africa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Africa-Italy የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ጣልያን፣ ሮም ገብተዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድም ሮም ይገኛሉ። የሀገራት መሪዎች ፣ እና የመንግሥታት ተወካዮች በሮም እየተሳብሰቡ የሚገኙ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ዛሬ እና ነገ ለሚካሄድ የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ነው። የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ…
ፎቶ ፦ የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በጣልያን፣ ሮም ከተማ እየተካሄደ ሲሆን የበርካታ ሀገራት መሪዎችና የመንግስት ተወካዮች ጉባኤውን እየተካፈሉ ይገኛሉ።

በዚህ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙት መሪዎች መካከል፦
* የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣
* የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
* የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
* የኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ይጠቀሳሉ።

የሁለት ቀኑ የአፍሪካ-ጣሊያን የመሪዎች ጉባኤ በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በኢኮኖሚና መሰረተ ልማት፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢነርጂ ደህንነት እና ሽግግር እንዲሁም በሙያ ስልጠናና በባህል ዘሪያ እኩል አጋርነትን መፍጠር ላይ ያተኩራል።

#Africa #Italy

@tikvahethiopia
#Africa

" በኮንፌዴሬሽን ለመዋሃድ ተስማምተናል " - በመንፈንቅለ መንግስት የመጡት የሶስት ሀገራት መሪዎች

ቡርኪናፋሶ ፣ ኒጀር እንዲሁም ማሊ በኮንፌደሬሽ ለመዋሃድ ተስማሙ።

በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት የቡርኪናፋሶ ፣ ኒጀር እና ማሊ ወታደራዊ ሁንታዎች በኮንፌደረሽን ለመዋሃድ ማስማማታቸው ተሰምቷል።

ከምዕራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ ጥምረት (ECOWAS) ፍቺ መፈጸማቸውንም ገልጸዋል።

የ3ቱም ሃገራት ወታደራዊ ሁንታዎች ስልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክቡ ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በተለይ ደግሞ ECOWAS ብርቱ ውትወታ እና ማዕቀብ ሲደረግባቸው ነበረ።

ጥምረቱ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንደሚያደርግ ከገለጸ በኋላም ከሶስቱም ሃገራት ብርቱ ትችት ሲደርስበት ቆይቷል።

ሀገራቱ ECOWASን የቀድሞ ቅኝ ገዢያቸው " የፈረንሳይ ጉዳይ ፈጻሚ " በማለት ክፉኛ ሲወቅሱት ነበረ።

ይህንንም ተከትሎ ከፈረንሳይ ጋር የነበራቸውን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነትን በማቋረጥ ወደ ሩስያ አማትረዋል።

አሁን ደግሞ የስስቱም ሃገራት መሪዎች በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ ባካሄዱት ስብሰባ " የሳሕል ሃገራት ኮንፌደሬሽን መንግስት " በሚል ለመዋሃድ መስማማታቸውን እና መፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሀገራቱ በድምሩ 72 ሚሊዮን ህዝብ ያላቸው ሲሆን 3ቱም በታጣቂ ቡድኖች በሚፈጠር አለመረጋጋት እየተፈተኑ ይገኛሉ።

አሁኑን ስምምነት ተከትሎ በጸጥታ ጉዳዮች አብረው እንደሚሰሩ የኢኮኖሚ ትስስራቸውንም እንደሚያጠናክሩ ይጠበቃል።

ECOWAS በዛሬው ዕለት ስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን ይህ የኮንፌደሬሽን ምስረታ ጉዳይ ዋና የመዋያያ አጀንዳው እንደሚሆን  ተዘግቧል።

መረጃው የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፣ የዶቼቨለ ሬድዮ እና አናዱሉ ነው።

@tikvahethiopia
#Africa

የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ " ደመወዘኔን 40 በመቶ እቀንሳለሁ " ሲሉ አስታወቁ።

ጽ/ቤታቸው፤ " ፕሬዜዳንቱ ይህ እርምጃ የሚወስዱት ተጠያቂ አስተዳደር በመፍጠር አርዓያ ለመሆን እና ከዜጎች ጋር ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ነው " ብሏል።

ፕሬዚዳንት ቦአካይ ፥ ከጥቂት ወራት በፊት ዓመታዊ ደመወዛቸው 13 ሺህ 400 ዶላር (769 ሺህ ብር በላይ) እንደሆነ ገልጸው አሁን ባቀረቡት 40 በመቶ ቅነሳ ወደ 8 ሺህ ዶላር (459 ሺህ ብር በላይ) ያደርሰዋል።

የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት የዚህ ዓመት በጀት ወደ 3 ሚሊዮን ዶላር ይጠጋል።

አንዳንዶች የፕሬዚዳንቱን የደመወዝ ቅነሳ እርምጃ ቢያደንቁም ሌሎች ግን እንደ ዕለታዊ አበል እና የህክምና ሽፋን ጥቅማጥቅሞችን እንደሚያገኙ ጠቅሰው " ይህ በእውነት መስዋዕትነት ነው ወይ ?  ሲሉ ጠይቀዋል።

ከሳቸው በፊት የነበሩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ ደመወዛቸውን 25 በመቶ ቀንሰው ነበር።

በሀገሪቱ ባለው ከፍተኛ ኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ ያሉት ላይቤሪያውያን አንደኛው ቅሬታ የሚያነሱት ጉዳይ የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ነው።

በላይቤሪያ ውስጥ በአማካኝ ከአምስቱ አንዱ ሰው ከ2 ዶላር (114 ብር) ባነሰ ዕለታዊ ገቢ ኑሯቸውን ለመግፋት ተገደዋል። #BBC

@tikvahethiopia