TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኮማንድ ፖስት‼️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ አጎራባች አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ችግር #የተጠረጠሩ 171 ሰዎች #በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ገንዘብም በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉ ተመልክቷል፡፡

የአካባቢውን ሠላም ለመመለስ የተቋቋመው ኮማን ፖስት አባል እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ ኢንዶክትሪኔሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል #ጌትነት_አዳነ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ኮማንድ ፖስቱ ታህሳስ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ከተቋቋመበት ጊዜ አንሰቶ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እየሰራ ነው።  

በእዚህም በክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች በታጠቀ ኃይል ተፈጥሮ በነበረ የጸጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ በጠፋው የሰው ህይወትና በወደመው ንብረት የተጠረጠሩ 171 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስረድተዋል፡፡

ተጠርጣሪዎች የተያዙት ግጭት ከተከሰተባቸው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሽ ዞን እና ቶንጎ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ደግሞ ምዕራብ ፣ ምስራቅና ቄለም ወለጋ፣ ሆሩ ጉድሩ፣ ኢሉአባቦራ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል በየደረጃው የሚገኙ #አመራሮች እንደሚገኙበት ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

የታጠቀው ኃይል ለግድያ እና ሌሎች #ጥፋቶች ሲጠቀምባቸው የነበሩ 49 ክላሽንኮብ ጠመንጃዎችና 1 ሺህ 31 የተለያዩ ጥይቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮሎኔል ጌትነት ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቦቹ በህገ-ወጥ መንገድ ሲያንቀሳቀሱት የነበረ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር እና 12 ሺህ ዶላር ኮማንድ ፖስቱ መያዙን ነው ያስረዱት።

እንደ ኮሎኔል ጌትነት ገለጻ የጥፋት ኃይሎቹ ተጨማሪ ጥቃት ለመፈጸም ያዘጋጁት ሰባት ጸረ-ተሸከርካሪ ፈንጂዎች፣ 215 ቀስቶች እና የተለያዩ ኮምፒዩተሮችም ተይዘዋል፡፡

ታጣቂ ኃይሉ ከመንግስት መዋቅሮች እና ከግለሰቦች አስገድዶ በመውሰድ ለጥፋት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ዘጠኝ አምቡላንሶች፣ አራት አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪዎች፣ ሦስት ቶዮታ ፒክአፕ መኪኖችም ኮማንድ ፖስቱ ማስመለሱን ነው የገለጹት፡፡

ቡድኑ ለጥፋት ሲጠቀምባቸው የነበረውን ንብረት ከማስመለስ ጎን ለጎን በጉዳዩ ላይ ሕብረተሰቡን የማወያየት ሥራ በስፋት እየተካሄደ መሆኑን ኮሎኔል ጌትነት አስረድተዋል፡፡

የጸጥታ ችግር ሲከሰትባቸው በነበረባቸው ዞኖች በአሁኑ ወቅት ግጭት ሙሉ ለሙሉ ቆሞ ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ጠቅሰዋል፡፡

ህብረተሰቡ ያደረገው እገዛ ከፍተኛ መሆኑን ኮሎኔል ጌትነት ጠቁመው ኮማንድ ፖስቱ በቀጣይ ችግሩ እንዳይደገም አደረጃጀቱን ከህብረተሰቡ ጋር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

በሁለቱ ክልሎች አጎራባች አካባቢ የደፈረሰውን ሠላም ለመመለስ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ከፌደራልና ከሁለቱ ክልሎች መንግስታት እንዲሁም ከሀገር መከላከያ እና ከፌደራል ፖሊስ ሠራዊት የተውጣጡ አባላትን ያቀፈ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvqhethiopia