TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.6K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲያበቃ እና ችግሩ በድርድር እንዲፈታ በርካቶች ሲጠይቁ ቆይተዋል።

ህወሓትም ጦርነቱ ቆሞ ችግሩ በውይይት ይፈታ ዘንድ ለAU እና ለሌሎችም ጥሪ ሲያቀርብ ነበር።

ድርድርን በሚመለከት የፌዴራል መንግስቱ በፍፁም ህወሓት ውስጥ ካሉት 'ወንጀለኛ' ቡድን ጋር ቁጭ ብዬ #አልደራደርም ብሎ አሳውቋል።

ይህ 'ህወሓት' ውስጥ ያለው ቡድን ታሪክ ይቅር የማይለውን ጥፋት አጥፍቷል፣ የሀገር መከታ የሆነውን መከላከያ ሰራዊት አጥቅቷል ፣ ይህን ጉዳይ አምኗል ፤ አሁን እየተካሄደ ያለው የህግ ማስከበር እና የሀገርን ህልውና እና ክብር የማስጠበቅ ዘመቻ የሚጠናቀቀው ወንጀለኞቹ ህግ ፊት ሲቀርቡ ብቻ ነው ሲል ከዚህ ቀደም አቋሙን ገልጿል።

ትላንት ምሽት ድርድርን በሚመለከት በተለያዩ መገናኛ ብዙን አንድ መረጃ ሲሰራጭ ነበር። ይህ የተሰራጨው መረጃው ግን ሀሰተኛ ነው ተብሏል።

ጉዳዩን በሚመለከት ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተሰጠው አጭር ምላሽ ይኸው ነው ፦

"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኀብረት ሊቀ መንበር የሆኑትን የሲሪል ራማፎሳን ልዑካን ተቀብለው በግል ይወያያሉ።

ሆኖም ግን ፣ የፌደራል መንግሥትን እና በህወሓት የሚገኙ ወንጀለኞችን ለማሸማገል ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ በመሰራጨት ላይ የሚገኘው ዜና #ሀሰት መሆኑን እናረጋግጣለን።

#ድርድርን አስመልክቶ የፌደራል መንግሥት ያለው አቋም ፈጽሞ ያልተለወጠ ነው።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia