TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምስራቅ ዕዝ~መከላከያ‼️

ሰራዊቱ ከህዝቡ ጋር የጀመረውን ሰላምና ልማትን የማስቀጠል ስራዎችን #በተጠናከረ መንገድ እንደሚያስቀጥል የምስራቅ ዕዝ አመለከተ። 7ኛውን ዙር የመከላከያ ሰራዊት ቀንን በማስመልከት በህዝባዊ ውይይቶች፣ በጽዳት ዘመቻና በሌሎች በጎ እድራጎት ስራዎች በመከበር ላይ ነው።

የምስራቅ ዕዝ የኢንዶክትሬሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮረኔል ፍስሐ ተክለሐይማኖት ዛሬ እንደገለጹት በዓሉ ሰራዊቱንና ህዝቡን የሚያገናኝ በዓል ነው። 7ኛው ዙር የመከላከያ ሰራዊት ቀን ባዓልም እስከ የካቲት 6 ቀን 2011 በምስራቁ አገሪቱ ክፍል በሚገኙ ዞኖች፣ክልሎችና አስተዳደር ከተሞች በፓናል ውይይት፣በጽዳት ዘመቻና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች እየተከበረ ይገኛል፤ ሰራዊቱም የሰላምና የልማት ሐይል እንደመሆኑ ችግሮች ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይደርስ እንደከዚህ ቀደሙ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያከናውነውን የሰላምና የልማት ስራዎችን የሚያጠናክርበት እና የሚያጎለብትበት በዓል ነው።

በተለይ በተለያዩ አካባቢዎች በአዋሳኝ ስፍራዎች፣ በመልካም አስተዳደርና በሌሎች የተነሱት አለመግባባቶች በእርቅና እንዲፈቱ የሰላም አምባሳደር ወጣቶችን ከክልልና ዞንና አመራር አካላት ጋር በመመልመልና ስልጠና በስጠት እንዲፈቱ የሚደረግበት መሆኑን ተገልጿል። እንዲሁም በየቦታው የሚታዩ አለመግባባቶች፣ ስርዓት አልበኝነት፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ገንዘብ ዝውውርና ሌሎች በህዝቡ ላይ ጉዳት በሚያደርሱ ተግባራትን ከአመራሩና ከህዝቡ ጋር ሰፊ የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሮ ችግሩ የሚወገድበት መንገድ የሚመቻችበት እንደሆነ አመልክተዋል።

ሰራዊቱም #ህዝባዊነቱን የተቸገሩ ወገኖችን #የሚረዳበት፣ በሆስፒታል የሚገኙ #ህሙማንን የሚጎበኙበት በደም እጦት እናቶች ህይወታቸውን እንዳያጡ ደም የሚለግሱበትና ሌሎች የበጎ አድራጎስ ስራዎች የሚከናወኑበትና አለኝታነቱን የሚያስመሰክርበት ነው ሲሉ አብራርተዋል፤ ህዝቡም ከሰራዊቱ ጋር እየተወያየ በየአካባቢው እየታየ የሚገኘውን ሰላምን የማጠናከር ስራ ማጠናከር ይጠበቅበታል ብለዋል። “ህገ መንግስታዊ ታማኝነታችንንና ህዝባዊ ባህርያችንን ጠብቀን የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን” በሚለው መሪ ቃል በሚከበረው 7ኛው ዙር የመከላከያ ሰራዊት ቀን በዓል የካቲት 7 ቀን 2011 በአየር ሐይል እና በኦሮምያ ክልል አዘጋጅነት በአገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት #በአዳማ ከተማ ይከበራል።

ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia