TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አምቦ🔝

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና ኦነግ ዛሬ እንደገና አምቦ ላይ #ዕርቅ ፈጽመዋል፡፡ የኦሮሞ አባ ገዳዎች በመሩት ባህላዊ የዕርቅ ስነ ሥርዓት ላይ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት #ሚልኪያስ_ሚደቅሳ (ዶ/ር)፣ ከኦነግ ደሞ ሊቀመንበሩ #ዳውድ_ኢብሳ ተገኝተዋል፡፡

እንደ ባህሉ ኮርማ ታርዶ በተከናወነው ስነ ሥርዓት ሁለቱ ወገኖች ያለፈውን ሁሉ ከኋላቸው ትተው ድጋሚ ደም በመካከላቸው እንዳይፈስ በዕርቅ መንፈስ በጋራ ለመሰራት ተስማምተዋል፡፡ ዝርዝር የስምምነት ነጥቦችም ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

ዛሬ ረፋዱ ላይ ግን የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ አለሙ ስሜ ኦነግ የሠራዊቱንና ትጥቁን ጉዳይ ለአባ ገዳዎች ትቻለሁ ማለቱ ለሰላም ቁርጠኛ አለመሆኑን ያሳያል ሲሉ ለሸገር ተናግረው ነበር፡፡

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 16/2011 ዓ.ም.

የሶማሌ ክልል መንግሥት ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ አንድ የካቢኔ አባልን ጨምሮ ስድስት ከፍተኛ አመራሮችን #ከኃላፊነታቸው አንስቷል።


በድሬዳዋ የጥምቀትን በዓል ተከትሎ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 84 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።


ድሬዳዋ ዛሬ በተቃውሞ ስትናጥ ውላለች። በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የጥይት ተኩስ ድምጽ ሲሰማ ውሏል። እስካሁን ድረስ በሰዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት በግልፅ የታወቀ ነገር ባይኖርም የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸው ተሰምቷል።


አባይ ኢንዱስትሪያል የልማት ማህበር በአማራ ክልል ደጀን ከተማ በ8.8 ቢሊዮን ብር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት ከቻይናው HY እና ከዴንማርኩ FLS ኩባንያዎች ጋር ሥምምነት ተፈራርሟል፡፡


የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና ኦነግ ዛሬ እንደገና አምቦ ላይ #ዕርቅ ፈጽመዋል፡፡


ሰሞኑን በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን #ግጭት ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች #ተስማምተዋል


የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ #ተገልብጦ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል። ሁለት ሰዎች ሞተዋል ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።


ዛሬ ዱራሜ ላይ በከፋ ዞን ለሞቱ የከንባታ ተወላጆች የሃዘን መግለጫ እና ሻማ የማብራት ፕሮግራም ተካሂዷል።


የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ጀምሯል፡፡


የጉምርክ አሰራርን #ሳያሟላ ወደ መቀለ ሊገባ የነበረ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።


ኮሎኔል #አለበል_አማረ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ የህዝብ ደህንነት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ምንጭ፦ አብመድ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ ኢ.ዜ.አ.፣ fbc፣ የጀርመን ራድዮ፣ ዋዜማ ራድዮ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት


አመሰግናለሁ! ሰላም እደሩ!!
ሀገራችንም ቸር ትደርልን!!
ጥር 16/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኬንያ(ናይሮቢ)🛫

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር #ለመወያየት በአሁኑ ወቅት ወደ #ናይሮቢ ኬንያ አቅንተዋል።

ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ በሶማሊያና ኬንያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ ምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ሊቀ መንበርነታቸው በቅርበት በመከታተል ወደ #ዕርቅ የሚመጡበትን መላ እያፈላለጉ ነው።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኬንያታና የሶማሊያው አብዱላሂ መሐመድ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት በዘለቁ ወቅት ከሁለቱም ጋር ባደረጉት ምክክር፤ ይህንን የኬንያና የሶማሊያ መሪዎች የፊት ለፊት ውይይት ለማመቻቸት ወስነው ነበር። ይህ የውይይት መድረክም በሁለቱ መካከል ያለውን የተካረረ ውጥረት ያረግባል ተብሎ ይታመናል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia