TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ...

#ዓዲግራት_ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ሲያስተምራቸው የነበሩ 5 ሺህ 161 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በስድስተኛ ዙር ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል የኤርትራ፣ ሶማልያ፣ ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎች ይገኙበታል፡፡

Via #DW
ፎቶ: Liknew/TIKVAH-ETH/
🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ #ራያ #አክሱም #ዓዲግራት

ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ምልከታ ሊያደርግ ነው፡፡

በግጭቱ ምክንያት ሥራ ያቋረጡትን አክሱም፣ ራያ፣ አዲግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አገልግሎት ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ዳግም ወደ አገልግሎት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ንግግር መጀመሩን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ተናግረዋል።

በቀጣይም ከመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነት እንደሚጀመር ኃላፊው አመላክተዋል፡፡

በአክሱም ከተማ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተከትሎ፤ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ከሰኞ ጀምሮ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ግቢ ጨምሮ አድዋ እና ሽረ ግቢዎችን በስፍራው በመገኘት ምልከታ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በመሰረተ ልማት፣ በቤተ ሙከራ፣ በኔትወርክ፣ በመኝታና መማሪያ ክፍሎች፣ በማስተማሪያ ሆስፒታል፣ በቤተ መጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎቶች ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ ይመለከታል፡፡ #FBC

@tikvahuniversity
#ዓዲግራት

በደም አፋሳሹ ጦርነት የወደሙ ተፈጥራአዊ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ለማደስ በትኩረት እንደሚሰራ የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።

ዩኒሸርስቲው የህንን ያስታወቀው የዘንድሮው የመስቀል በዓል በማስመልከት ባከናወነው ዓለምአቀፍ ኮንፈረንስ ነው ።

የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ፕረዚደንት ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ በኮንፈረንሱ መክፈቻ እንዳሉት ፤ ባለፉት ሁለት የጦርነት አመታት በቅርሶች ላይ የውድመትና የስርቆት ተግባራት መፈፀማቸው በቱሪዝም ኢንዱስትሪው አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል።

ፕረዚደንቱ አክለው እንዳሉት በአከባቢው በሚገኙ የአርኪኦሎጂ ማእከላት የደረሰው ጉዳት ከባድ መሆኑና በተለይ የአክሱም ቅድመ ስልጣነ ማሳያ መሆናቸው በቁፋሮ የተረጋገጠላቸው መዛብርና መነበይቲ የተባሉ ቦታዎች ለኤርትራ ቅርብ በመሆናቸው ያሉበት ሁኔታና የደረሰባቸው ውድመት ምንያህል እንደሆነ ማጥናት አልተቻለም ብለዋል። 

የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ.ር ኣፅብሃ ገ/እግዚአብሔር በኩላቸው የማንነት ምንጭ የሆኑት የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች የመጠበቅና የመንከባከብ ስራ የሁሉም ዜጋ ርብርብ ይጠብቃል ፤ በተለይ በክልሉ የሚገኙ አራቱ ዩኒቨርስቲዎች ያለውን እምቅ የቱሪዝም ፀጋ በማጥናትና በማስተዋወቅ ወደ ጥቅም እንዲለወጥ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። 

የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የአርኪኢሎጂ ትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃይላይ አፅብሃ ደግሞ ዓለምአቀፍ የቅርሶች ጥበቃ ስምምነት በጦርነት ወቅትና በኃላ መነሻ ማድረግ በቱሪዝምና አርኪኦሎጂ ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ የአገር ውስጥና የውጭ ሙሁራን ያጠኑት መለስተኛ ጥናት መቅረቡንና ዩኒቨርስቲው ጥናቱን መነሻ በማድረግ ጉዳት የደረሰባቸው ቅርሶች በመለየት የመልሶ ማልማት ስራ እንደሚሰራ አስረድተዋል። 

በትግራይ ደረጃ በዓዲግራት ዓጋመ የሚከበረው የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ በዓዲግራት የኒቨርስቲ አዘጋጅነት በተከናወነው የባህልና የቱሪዝም ዓለምአቀፍ ኮንፈረስ በክልሉ ምስራቃዊ ዞን ብቻ ከ120 በላይ በአገር ውስጥና በውጭ ቱሪስቶች ሊጎበኙ የሚችሉ ውቅር አብያተ ክርስትያን እንዳሉ ያመለክታል።

በዓለም የቅርስ ጥበቃ ድርጅት ማለትም ዩኔስኮ የተመዘገበው የውቕሮው አልነጃሺ መስጊድ ፤ የአክሱም ቅድመ ስልጣኔ መገኛ መሆኑ በዓለም አቀፍ የቁፋሮ ባለሙያዎች (አርኪኦሎጂስቶች ) የተረጋገጡ መዛብርና መነበይቲ የቁፋሮ ማእከላትም በአከባቢው ይገኛሉ።

የዘንድሮ የመስቀል በዓል" ለሰላም ለመልሶ ግንባታ ስነ-ልቦናዊ ማገገም " በሚል መሪ ቃል በትግራይ ደረጃ በመቐለና በዓዲግራት ከተሞች በልዩ ድምቀትና ትኩረት እየተከበረ ይገኛል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከዓዲግራት ከተማ ዘግቧል ።
 
ዓዲግራት ከኤርትራ ደንበር በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ነች።

@tikvahethiopia
#ትግራይ #ዓዲግራት

" ብርጌድ ንሓመዱ " የተባለው የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣቶች እንቅስቃሴ በትግራይ ኢትዮጵያ ተቋቋመ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ " ምምስራት ብርጌድ ንሓመዱ ጨንፈር ትግራይ መላእ ኢትዮጵያ " ማለትም ' የብርጌድ ንሓመዱ  መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ምስረታ '  በሚል ርእስ በተለይ ኤርትራውያን በሚጠቀሙባቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወር ያገኘው የጥሪ ደብዳቤ በመያዝ #ሃቀኝነቱን ለማረጋገጥ ጥረት አድርጓል።

በትግርኛ ቋንቋ የተፃፈውና በማህበራዊ ትስስር ገፆች  የተሰራጨው ማህተምና ፊርማ  የሌለው በመላ ኢትዮጵያ ለሚኖሩ ኤርትራውያን የተፃፈው ደብዳቤ ሙሉ ቃል እንዲህ ይላል።

"... ይፋዊ  ምስረታ 'ብርጌድ ንሓመዱ ' መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ።

'ብርጌድ ንሓመዱ ' የተባለ የኤርትራውያን ህዝባዊ ማዕበል እንቅስቃሴ ለማጠናከር በምናካሂደው ህዝባዊ ስብሰባ እንድትሳተፉ በክብር ጥሪ እናቀርባለን።

        የስብሰባ ቦታ ዓዲግራት ትግራይ !!

                ሕጊ ይንገስ
               ምልኪ ይፍረስ !!
                ህግ ይንገስ
                አምባገነንነት ይፍረስ "

የጥሪ ደብዳቤውን በመከተል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል እሁድ ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም ከመቐለ ወደ ዓዲግራት ተጓዘ ።

ስብሰባ ይካሄድበታል ወደ ተባለ ቦታ በመሄድ ከአስተባባሪዎች ተገናኘ። አስተባባሪዎቹ ለድህንነታቸው ሲባል ስማቸው ምስላቸውና በኤርትራ የየት አከባቢ ነዋሪዎች እንደነበሩ  ለመጥቀስ ፍቃደኞች አይደሉም።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከአስተባባሪዎቹ በመሆን ስብሰባ ወደ ተጠራበት ሰፊ አዳራሽ ይደርሳል። በሰፊ አዳራሹ ቁጥራቸው አነስተኛ ተሰብሳቢዎች ተገኙ።

አስተባባሪዎቹ ለጥንቃቄ ሲባል ፎቶ ማንሳትም ሆነ ድምፅ መቅረፅ አይፈቀድም ባሉት መሰረት የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ሪፓርተር የተባለውን በመቀበል ሰብሰባውን ተከታትሏል።

ይኸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል እንደረጋገጠው 'ብርጌድ ንሓመዱ 'የተባለው የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣቶች እንቀስቃሴ ' ብርጌድ ንሓመዱ ጨንፈር ትግራይ መላእ ኢትዮጵያ ' ማለት የ 'ብርጌድ ንሓመዱ ' የመላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በይፋ በዓዲግራት ተቋቁመዋል። እንቅስቃሴው የሚያስተባብሩ አመራሮቹም መርጠዋል።

የእንቅስቃሴው አስተባባሪዎች እንዳሉት ፤ " ከ30 ዓመታት በላይ ያለ ህዝባዊ ምርጫ በአምባገነንነት ተቀምጠዋል " ያሉትን የኤርትራ መንግስት ለመጣል በመላ ዓለም በሚኖሩ ኤርትራውያን ወጣቶች እየተደረገ ያለው ትግል በመደገፍና በመቀላቀል ትግሉ በመላ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ኤርትራውያን ተቀባይነት እንዲያገኝ አበክረው ይሰራሉ።

የ ' ብርጌድ ንሓመዱ  መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ' በሚል የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣት ኤርትራውያን እንቅስቃሴ በይፋ የተመሰረተባት የትግራይዋ ዓዲግራት ከተማ ከኤርትራ ደንበር በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ትገኛለች ሲል ቲክቫህ ኢትጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከዓዲግራት ዘግቧል። 

@tikvahethiopia
#ዓዲግራት

በንዋየ ቅዱሳን ሰርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ግለሰቦቹ የመቐለ ነዋሪ ናቸው።

5 የወርቅ መስቀሎችን ከመቐለ ወደ ዓዲግራት ወስደው ሊሸጡ ሲደራደሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዓዲግራት ፓሊስ ፅ/ቤት አስታውቀዋል።

የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ዋና አዛዥ የማነ ኪዳኑ  ፥ " ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ/ም የግል ተበዳይ ከመቐለ ወደ ሽረ ከተማ የወርቅ መስቀሉን ጭኖ በመውሰድ ላይ ሳለ ነው ተጠርጣሪዎቹ ሰርቆቱን ፈጽመው የተሰወሩት " ብለዋል። 

ግለሰቡም በመቐለ ከተማ ለቀዳማይ ወያነ ፓሊስ ፅህፈት ቤት ያመለከተውን መረጃ መነሻ በማድረግ በተካሄደው ክትትል ተጠርጣሪዎች በዓዲግራት ከተማ ውስጥ ሊያዙ እንደቻሉ ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዎች የሰረቁትን አንዱ ብር 25 ሺህ የሚያወጣ መስቀል ፤ በ15 ሺህ ሊሸጡት ተሰማምተው በዋጋው ማነሰ የተጠራጠረ ገዢ በኩል መረጃው ወደ ፓሊስ በመድረሱ ግለሰቦች ከነእግዚብታቸው በፓሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ የፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል።

ግለሰቦቹ 4 ሲሆኑ ነዋሪነታቸውም መቐለ ነው።

የዓዲግራት ፖሊስ ፤ እንዲገዛ ግብዣ የቀረበለት ግለሰብ ጊዚያዊ ጥቅም እና ትርፍ ሳያሸንፈው ለፓሊስ ያደረገው ትብብር ሌላው እጅግ አርአያ የሚሆነው ሲል አወድሷል።

መረጃው ይህ ሆኖ ሳለ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የዓዲግራት ወጣቶች የሆኑ ከቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ውስጥ ንዋየ ቅዱሳን ዘረፉ "  እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia