TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ🔝

#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ ትላንት ቅዳሜ የካቲት 02-2011 ዓ/ም ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይነስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ድሌቦ፣ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት አባላት፣ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስራ ሃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረስብ እና ውድ የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ የመጀማሪያ የሆኑትን የህክምና ዶክተሬት ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ በሁለቱም ጾታ አመረቂ ውት ያመጡ ተማሪዎች የተሸለሙ ሲሆን ከሴቶች ዶ/ር #ጋዲሴ_አስፋ ከወንዶች ዶ/ር #ዋክሹም_ፈጠነ የሰርትፍኬት እና የብር ሽልማት ተሸለመዋል፡፡ ዶ/ር ዋክሹም ፈጠነ በአጠቀላይ የሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።

Photo credit Biruk Butishá
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech
#ከጥላቻ_ንግግር_እንቆጠብ!!
የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መድረክ ከልዩ ልዩ ጥበባዊ ዝግጅቶች ጋር በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ነገ #ቅዳሜ እና #እሁድ በቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አማካኝነት በግቢያችን ይካሄዳል።

#ፕሮግራሞች

#ቅዳሜ

☞ ብዙ ኪ.ሜ አቆራርጠው ለፍቅር እና ለሰላም ለሚመጡት የTIKVAH-ETH
ቤተሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል ይደረጋል፣ ጥበባዊ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።

#እሁድ

√የደም ልገሳ ፕሮግራም
√በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት ስለጥላቻ ንግግር ፅሁፎችን ይቀርባሉ ፤ ልዩ ልዩ
ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ይቀርባሉ፡፡
√በግቢያችን የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል

#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁሉም #የTIKVAH_ETH ቤተሰብ አባላት #በሰላም ገብተዋል!! #ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ #StopHateSpeech
እናመግናለን!! #ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ላደረጋችሁት አቀባበል፤ ከልብ #እናመሰግናለን!!

ፍቅርን፤ ሰው ማክበርን አስተምራቹናልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🎂TIKVAH ETHIOPIA~2 ዓመት🎂

#ደብረ_ብርሃን #ወሎ #ጅማ #ሀረማያ #ሀዋሳ #ወልቂጤ #መቐለ #ወልዲያ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #ሆሳዕና/#ዋቸሞ/

📎የሰውልጅ በሰውነቱ የሚከበርበት፤ የግለሰቦች አመለካከት፣ እምነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ የኔ ነው የሚሉት ሁሉ የሚከበርበት፤ ፍቅር፣አንድነትና መተባበር የነገሰበት፣ የሰው ልጅ ሁሉ መሰብሰቢያ የሆነች ከጥላቻ የራቀች ሀገር እንገነባለን!! ተባብረን እንሰራለን፤ ለመጭው ትውልድ ኢትዮጵያን እናወርሳለን!!

እኛ ስንኖር ኢትዮጵያ ትኖራለች፤ ኢትዮጵያ ስትኖር እኛም እንኖራለን!

#ድፍን_ሁለት_ዓመት_በፍቅር_በመተባበር!

ነገ 6:00 አበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት እንገናኝ፤ ከእናታችንም ምርቃት እንቀበል!! ሁላችሁም የዚህ ገፅ ባለቤቶች ናችሁ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

የአዲስ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ማስተካከያ⬆️

"በምትመለከቱት ማስታወቂያ ላይ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥቅምት 28 እና 29 የሚለው የፅሁፍ #ስህተት ስለሆነ መስከረም 28 እና 29 ተብሎ ይስተካከል። በተጨማሪም አዲስ በዱራሜ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀን ጥቅምት 5 እና 6 መሆኑን እንገልፃለን።" ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

#share #ሼር

የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮችን በስፋት በTIKVAH-MAGAZINE ታገኛላችሁ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የነበረንን ጥያቄ ለማቅረብ በወጣንበት " የኃይል እርምጃ ተወስዶብናል " ሲሉ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታ አቀረቡ።

ተማሪዎቹ ጥያቄ የነበረው ከመውጫ ፈተና በኃላ ለሚካሄደው ምርቃት " ምርቃቱ ላይ ለመገኘት የወደቀ ያለፈ መባል የለበትም ፤ አንድ ላይ መመረቅ አለብን ፤ ለ16 አመት ያክል የለፋንበት ፣ ቤተሰብም ብዙ የደከመበት ነው ይሄ ጉዳይ መልስ ያሻዋል " በሚል መሆኑን ገልጸዋል።

" ይህን ጥያቄያችንን ድንጋይ፣ ዱላ ሳንይዝ ምላሻ እንዲሰጠን ለመጠየቅ ሰልፍ ብናደርም የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም፣ ከፍተኛ ድብደባ በመፈፀም፣ የወንድ እና የሴቶች ዶርም ድረስ በመዝለቅ ጉዳዩን የማያውቁ ተማሪዎችን ጭምር በመደብደባ እና በማዋከብ ጥያቄያችንን ለማፈን ሞክረዋል " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኳቸው የቪድዮ ማስረጃዎች የፀጥታ ኃይሎች ተማሪዎችን በደቦ ሰደበድቡ ፣ ወደ ሴቶች ዶርም ዘልቀው ገብተው ተማሪዎችን በኃይል ሲያስወጡ ያሳያል።

ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋሙ ሰራተኞች በኩል ሃስብ ለመቀበል ጥረት አድርጓል። አንድ በሳምንት መጨረሻ ቀናት ለማስተማር በተቋሙ የተገኙ መምህር ጉዳዩን ውስጥ ሆነው ሲከታተሉ እንደነበር ገልጸዋል።

የፀጥታ ኃይሎች ወደ እርምጃ የገቡት ተማሪዎቹ የግቢ ውስጥ እየጮሁ የመማር ማስተማር ስራውን ሲያውኩ፣ መንገድ በድንጋይ ሲዘጉ፣ ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም በፀጥታ ኃይሎች ላይ ትንኮሳ ለመፈፀም በሞከሩበት ወቅት መሆኑን አመልክተዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩ ቪድዮዎች የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳይ አይደለም የሚሉት መምህሩ ግቢውን ለመረበሽ የሞከሩ ተማሪዎች እንዲሁም በተማሪዎች ላይ ከልክ ያለፈ እርምጃ የወሰዱ የፀጥታ ኃይሎችን እኩል ማውገዝ ይገባል ብለዋል።

" ተማሪዎቹን ንጹሕ፤ የጸጥታ ሀይሉን በመወንጀል የሚሰራ ዜና ሚዛናዊነት የሚጎድለው ሁኔታውን የማያስረዳ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላ አንድ የግቢው ሰራተኛ የፀጥታ ኃይሎች ወደ እርምጃ የገቡት የግቢው የመማር ማስተማር ስራ ሲታወክ እና ግቢው ሲረበሽ ነው ብለው የተወሰደው እርምጃ ግን ልክ ያለፈ መሆኑን ገልጸዋል።

መልዕክታቸውን የላኩ ተማሪዎቹ ግን በግቢው ሰራተኞች በኩል የተሰጠው ሃሳብ የማይቀበሉት ሲሆን አጠቃላይ የነበረው ሁኔታ ሰላማዊ እንደነበር፤ ተማሪዎች ግቢ ለመረበሽ ያደረጉት ሙከራ እንደሌለ፣ የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰድ በጀመሩበት ወቅት ግን መንገድ ለመዝጋት መሞከሩን አመልክተዋል።

አንድ የግቢው ተማሪ፤ " በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ከማቅረብ በዘለለ ድንጋይ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ለመወርወር የሞከረ  ፤ ዓመታትን በተማረበት ተቋም ጥፋት ለማድረስ የሞከር ተማሪ አልነበረም ብሏል።

" በእርግጥ መንገድ ዘግተዋል መንገድ የዘጉበት ምክንያት ፖሊስ ተማሪን መምታት ሲጀመር ነው " ሲል ገልጿል።

በርካታ ተማሪዎች የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰዳቸው፤ ተቋሙ ለሰለማዊ ጥያቄ ከውይይት ይልቅ ኃያልን አማራጭ ማድረጉን የሚገልፅ መሆኑን እና በተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች መጎዳታቸውን፣ ንብረትም መዘረፉን አመልክተዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠንን ምላሽ ተከታትለን እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት እንደሚሰጥ የተማሪዎችን ምረቃ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት እንደሚካሄድ በመርሃግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ መሆናቸውን ማሳወቁ ይታወሳል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-11

@tikvahethiopia