TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update⬆️ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንደ #እናት ሆነው ለማሳደግ በዛሬው ዕለት አንድ ህፃን ልጅ ተረክበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-AID 2🔝በዚህ መልኩ ነው የየቀኑን የገንዘብ እንቅስቃሴ ለህዝብ ይፋ የሚደረገው። ይህ በ @tikvahaid2 በሚል እና በተከፈተው የግል አካውንት እየተሰራ ያለ ስራ ነው። አባላት በጠየቁት መልኩ እና ከፍተኛ ሀላፊነት እና እምነት ጥለውበት የሚሰራ ስራ ነው።

🔹የመጀመሪያው ድጋፍ #በአፋር ሎጊያ ለሚገኘ አንድ የ17 አመት ትዳጊ #እናት የሚውል ነው። ቻናሉን ተቀላቅላችሁ ያለውን እያንዳድዷን እንቅስቃሴ መከታተል ትችላላችሁ። ድጋፉ 15,000 ብር ለማድረግ ሲሆን አሁን ላይ 5,547 ብር ተገኝቷል።

ነገ ይጠናቀቃል ይህ ዘመቻ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እየተፈጠረ_ያለ_ችግር_ጋዜጣዊ_መግለጫ_18_09_13.pdf
964 KB
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ፓርቲው በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ስር በሚገኙ ምርጫ ክልሎች በምርጫ ሂደት ፣ በዕጩዎች እና አባሎቹ ላይ እየደረሱ ነው ያላቸውን ችግሮች በዝርዝር አስረድቷል።

ደርሰዋል የተባሉት ችግሮች ፦
- ማስፈራርት፣
- በሽጉጥ የመግደል ሙከራ ማድረግ፣
- እስር ፣
- ዕጩዎች ላይ ክትትል የማድረግ ትእዛዝ መስጠት፣
- ባነር እና ማስታወቂያዎች መገንጠል፣
- በገጠር ቀበሌ ህዝብን እየሰበሰቡ የፓርቲው ስም እንዲጠፋ የማድረግ፣
- ስድብ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ናቸው።

ከእናት ፓርቲ የተላከልን መግለጫ እንደሚያስረዳው ፓርቲው አጋጠመኝ ያላቸው ችግሮች በአማራ ፣ በደቡብ ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ ሐረር ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ነው።

* ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ በPDF ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ

" ንጹሓን የትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችን ወደሥራ ገበታቸው መመለስ ችሮታ ሳይሆን ግዴታ መሆኑ ይታወቅ " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው ኢትዮጵያ ከገባችበት የህልውና ጦርነት ጋር በተያያዘ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የትግራይ ተወላጅ ወገኖች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር እና ሂደቱ ህግ እና ህግን ብቻ መከተል እንዳለበት በተደጋጋሚ አበክሮ ሲያሳስብ መቆየቱን አስታውሷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንዶች እየተለቀቁ መሆኑን ገልጿል።

በሕግ ጥላ ሥር የነበሩ እና በቁጥጥር ሥር ሳይውሉ ከሥራ ገበታ ታግደው በቤት እንዲቆዩ የተደረጉ ንጹሓን ወደየሚሠሩባቸው መሥሪያ ቤቶች ሲመለሱ በአግባቡ እንዳልተስተናገዱ፣ ደመወዛቸው እንደተቋረጠ እና አንዳንድ ቦታዎች ይባስ ብሎ “በእናንተ ቦታ ሌላ ሰው ተተክቶበታል” በሚል ማን አለብኝነት ለተጨማሪ እንግልት እንደተዳረጉ መረጃዎች እንደደረሱት ፓርቲው ገልጿል።

እንዲህ ያለውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ዘመድ አዝማድ እና ተወላጅ ለመሰብሰብ፣ ለማሸማቀቅ፣ ኪስ ለማደለብ የሚሯሯጡ አካላት ተግባር ርካሽና ትሕነግ (TPLF) ካደረሰው በደል ያልተናነሰ ነገር እንደፈጸሙ ሊያውቁት ይገባልም ብሏል።

ፓርቲው ምንም አይነት ወንጀል ሳይፈጽሙ በትውልድ ሥፍራቸው ምክንያት ብቻ ከሥራ እንዲሁም ከሥራና ደመወዝ ታግደው ያሉ የትግራይ ተወላጅ ወገኖች ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ አጥብቆ ጠይቋል።

ይህንን በዜጎች ላይ በሰበብ አስባብ የሚደርስ እንግልት ማስወገድ ችሮታ ሳይሆን የዜጎች መብት የመንግስት ደግሞ ግዴታ መሆኑን እናት ፓርቲ በጽኑ እንደሚያምን ገልጿል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል።

በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ያወጡት እናት ፓርቲ ፣ መኢአድ እና ኢሕአፓ ሲሆኑ ፓርቲዎቹ " ሀገር በህግ እና በስርዓት እንጂ በአፈና አትመራም " ሲሉ ነው ወግለጫ ያወጡት።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው የኑሮ ውድነት፣ በአዲስ አበባ እየተሰራ ነው ስላሉት ደባ ፣ የመሬት ማዳበሪያ ጉዳይ፣ የሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል ጉዳይ፣ የፋኖን ጉዳይ፣ መንግስት እየወሰድኩ ነው ስላለው የህግ ማስከበር እርምጃ እና ሌሎች ጉዳዮችን በስፋት አንስተዋል።

ፓርቲዎቹ በሕግ ማስከበር ላይ የማያወላዳ አቋም እንዳላቸው የገለፁ ሲሆን በአፈናና በግድያ ሕግ ማስከበር እንደማይቻል አጠንክረን እናሳስባለን ብለዋል።

" ማፈን መግደልና የማኅበረሰብን ቅስም የመስበር አካሄድ በአፋጣኝ እንዲቆም " ሲሉ ጠይቀዋል።

አክለውም ፤ በሕግ ማስከበር ሰበብ የታፈኑ ንጹሓን፣ ጋዜጠኞች፣ ማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የፋኖ አባላትና ቤተሰቦቻቸው፣ ምሑራን፣ የጸጥታ ተቋማት ተመላሾችና አባላት፣ የፓርቲ አመራርና አባላት እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

መንግስት ጠረጥሬያቸዋለሁ ብሎ ካሰበም ተገቢውን የሕግ ሂደት በመከተል ለፍርድ ቤት ከማቅረብ ጀምሮ መሰል ሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ሶስቱ ፓርቲዎች " ፋኖ " በጭንቅ ጊዜ ሀገር " ድረስልኝ " ብላ የጠራችው ባለውለታ እንጂ ለሹመትና ለሽልማት የመጣ ባለመሆኑ መንግስት አጉል ሥጋቱን አስወግዶ የያዘውን አካሄድ ይፈትሽ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል መንግስት ያለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ሚሊዮኖችን ለጎዳና እና ለከፋ ረሃብ ከመዳረጉ በፊት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ያለውን የገበያ ምስቅልቅል እንዲያርምና እንዲያረጋጋ ጠይቀዋል።

(ሙሉ መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ #ድርድር

እናት ፓርቲ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ ለማድረግ የታሰበውን ድርድር እንደሚገፍ ገልጾ ነገር ግን በሁለቱ ፓርቲዎች (ብልፅግና እና ህወሓት) መካከል የሚደረግ እንዳይሆን ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብሏል።

ፓርቲው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በላከልን መግለጫው ነው ይህን ያለው።

እናት ፓርቲ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውና ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀረው ጦርነት ምን አልባት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከጋጠሟት ጥፋቶችና ውድመቶች ሁሉ ከቀዳሚዎቹ ሊቆጠር የሚችል ነው ብሏል።

ጦርነቱ ሰዋዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ ልቡናዊና ድፕሎማሲያዊ ጉዞን ለብዙ አሥርት ዓመታት ወደኋላ መልሷል ያለ ሲሆን ይህ ጦርነት ሊያመጣ የሚችለው ምስቅልቅልና ዳፋ አሳስቦት በእርቅና ሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሽምግሌዎችን ከማፈላለግ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷሳ።

አሁንም ያ ውድመትና ውረድ እንውረድ ዳግም እንዳይከሰት ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት የታየው መነሳሳት በደስታ የሚመለከተው ኩነት መሆኑን ገልጿል።

በመጀመሪያ ችግሩ እንዳይከሰት ብንከላከለው ጥሩ ነበር ከተከሰተ በኋላ የውጭ አካል ገብቶ በድርድር መልክ ከሚፈታ ይልቅ በሀገሬው ባህል በእርቅና ይቅርታ ቢፈታ መልካም ነበር ሲል ገልጿል።

ይህ ድርድር ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን ተሸክሞ የሚደረግ ነው ያለው ፓርቲድ ስለሆነም ሂደቱ ከቅድመ ድርድር ጀምሮ ዘለቄታዊ መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ ታቅዶ ካልተፈጸመ እና የውጭ ኃይሎችን "አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት መከላከል ካልተቻለ ጅብ ፈርቶ ዛፍ ብወጣ፣ ነብር ቆየኝ” ዓይነት መሆኑ አይቀሬ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ፓርቲው ለድርድሩ ውጤታማነት ወሣኝ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችን አንድ በአንድ ዘርዝሮ በመግለጫው አስቀምጧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

" መንግስት በቅጡ ሐዘናችንን እንድንወጣ ባያውጅልንም በራስ ተነሳሽነት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በመጪው ሰኞ፣ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ጥቁር ልብስ በመልበስ በቅርቡ በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን የተሰማችሁን ሐዘን እንድትገልጹ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዕለቱ ከቀኑ 6:30 ላይ ዅላችሁም በያላችሁበት የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት እንድታደርጉ፣ መገናኛ ብዙኃንም ዕለቱን በሙሉ ሐዘናችሁን ከመላው የኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚገባው እንድትገልጹ እንጠይቃለን። " - ኢሕአፓ፣ መኢአድ እና እናት

ኢሕአፓ ፣ መኢአድ እና እናት ፓርቲዎች ትላንት ያወጡት መግለጫ ሙሉ ቃል ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

ባለፈው ሳምንት ህዳር 27 ቀን 2015 እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አቢዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ሰነድ ፈረመዋል።

ስምምነቱ ዋነኛው ተግባር ምንድነው ? ፋይዳውስ ? ስለ ስምምነቱስ በጋራ ምን አሉ ?

" የትብብር ስምምነቱ ፓርቲዎቻችን በሚከተሉት አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራና በትብብር እንዲሠሩ ማዕቀፋዊና ሞራላዊ ግዴታ ይጥልባቸዋል፡፡

በሀገራዊ መግባባት፣ በምርጫ፣ በሰላም ማስፈን እና መሰል ጉዳዮች  ላይ የጋራ አቋሞችን በማራመድ #በሰላማዊ_መንገድ በትብብር #እንታገላለን፡፡

በተለይ በየዕለቱ ለሚሞተው እና በድርሱልኝ ሲቃ ለሚቃትተው ወገናችን ድምጽ በመሆን ከገባበት ችግር እንዲላቀቅ መሥራት ከግንባር ቀደም ተግባሮቻችን ዋናው ነው፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" እናቴን አላገኘኋትም " - አሠልጣኝ ኃይለ ኢያሱ

ዛሬ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ወደ #መቐለ ከተጓዘው የትግራይ ተወላጆችን ያቀፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት መካከል የአትሌት ለተሰንበት ግደይ አሰልጣኝ ኃይለ ኢያሱ አንዱ ነው።

አሰልጣኙ ከ2 ዓመት መለያየት በኋላ ዛሬ ከቤተሰቦቹ ጋራ መተያየቱን የገለፀ ሲሆን እናቱን ግን በህይወት እንዳላገኛቸው ገልጿል።

" #ሰላም_ያመጡ ሰዎችን አመሰግናቸዋለሁ " ያለው አሰልጣኝ ኃይለ ኢያሱ " ወደ ሀገሬ በመምጣቴም በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ። ሆኖም #እናት እና ሀገር አንድ ናቸው። ባጋጠመው ሊሆን በማይገባው ሁኔታ #በመድኃኒት_እጦት ምክንያት ሕይወቷ ማለፉን ነግረውኛል " ሲል ለቪኦኤ ሬድዮ ተናግሯል።

Credit : ቪኦኤ

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ ትላንት እሁድ በአዲስ አበባ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያደርግ መከልከሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

ፓርቲድ " ክልከላ በእሳት ፈትኖ እንደ ብረት ቢያጠነክረን እንጂ ሸብረክ እንድንል አያደርገንም " ብሏል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" በቅድሚያ 6 ኪሎ የሚገኘው በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሥር የሚተዳደረው የስብሰባ ማዕከል አዳራሽ ይሁንታ አግኝተን በመንግሥት ክልከላ ተደርጎብናል፡፡

ቀጥሎም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትልቁ አዳራሽ በአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በኩል አስይዘን ስለነበር ወደዚያ ቀይረን እንዲሁ ለጉባኤው ከ48 ሰዓት በታች ሲቀር በድጋሚ ክልከላ ተደርጎብናል፡፡

#የግድ መደረግ ያለበት በመሆኑ ሦስተኛ አማራጭ ከብዙ ድካም በኋላ የቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሰርግ አዳራሽ ሕጋዊ ሂደቶችን አሟልተን፣ ክፍያ ፈጽመን፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን አስገብተንና ትላንት ጠዋት ከሀገራችን 4ቱም ማዕዘናት ከመጡ ከ700 በላይ አባላት ተገኝተው፣ የተጋበዙ የሌሎች ፓርቲዎች አመራሮች፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች፣ ተጋባዥ እንግዶች ጋር በመሆን ወደአዳራሽ ስናመራ “ከመንግሥት የመጣ ትዕዛዝ” በሚል ወደውስጥ እንዳንገባ ታግደናል፡፡     
   
በዚህ መሐል የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሓላፊ ለወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጉዳዩን አስረድተን ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም፣ በተዋረድ ካሉ የጸጥታ ተቋማት ሓላፊዎች ጋር ቢደወልም መፍትሔው ሊቀርብ አልቻለም፡፡

ፓርቲያችንም ከ3 (ሦስት) ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገበት ጉባኤ ሳይከናወን አባላትን ለከፍተኛ እንግልት ዳርጎብናል፤ እንደፓርቲም ከፍተኛ የገንዘብ ኪሣራና የሥነልቡና ጉዳት አድርሶብናል፡፡ "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " እናት እና ልጅን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል " በአዲስ አበባ ትናንት ምሽት በጣለው ዝናብ እናት እና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳውቋል። ትናንት ምሽት የጣለውን ዝናብ ተከትሎ ከምሽቱ 12:05 ሰዓት በንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ማንጎ ሰፈር ወንዝ ዳርቻ ላይ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጎርፍ…
" የአራቱም ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል " - የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ " ማንጎ ሰፈር " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በደረሰዉ የጎርፍ አደጋ #እናት እና #ልጅን ጨምሮ 4 ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸዉን ተከትሎ የአስክሬን ፍለጋ ሲደረግ ውሏል።

በዚህም የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የዋናተኛ ቡድን የአራቱንም ሰዎች አስከሬን ማግኘት እንደቻለ ኮሚሽኑ አሳውቋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሟቾቹን አስከሬን ለማግኘት በተደረገዉ ጥረት ለአካባቢዉ ማህበረሰብና ለጸጥታ ሀይሎች ምስጋናዉን አቅርቧል።

#ሰሞኑን_እየጣለ_ባለዉ_ዝናብ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም ህብረተሰቡ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

ምንጭ፦ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው በዚህ መግለጫው፤ መንግሥት " ኦነግ ሸኔ '' እያለ ከሚጠራው የታጠቀ ቡድን ጋር በታንዛኒያ እያደረገው ያለው ድርድር ከሴራ ፖለቲካ በፀዳ መልኩ ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ ምኞቱን ገልጿል።

እናት ፓርቲ ፤ " ካለ ፍትሕ ሰላምን ማስፈን አስቸጋሪ መሆኑን ብናምንም ድርድሩ ከተለመደው የሴራ ፖለቲካ በጸዳ መልኩ ተከናውኖ በስቃይ ውስጥ የሚገኘውን ሕዝባችንን ሊታደግ በሚችል መልኩ እንዲቋጭ እንመኛለን፡፡ " ብሏል።

መንግስት ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ሀሳብ ካላቸው ፓርቲዎች ጋርም የጋራ መግባባትን ለማስፈን የሚያስችል ውይይት እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ አስተላልፏል።

ከዚህ ባለፈ የአማራ ክልል ብልጽግና ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ግድያን ተከትሎ መንግስት አሁንም " ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች" ን ትጥቅ በማስፈታት " ሰላም አስከብራለሁ " በሚል በአማራ ክልል የጀመረው እንቅስቃሴ ከሕወሓትና " ኦነግ ሸኔ " ጋር የታለፈበትንና አገርን ውድ ዋጋ ያስከፈለ አካሄድ የሚደግም ነው ብሎታል።

" መንግስት ካለፈ ስህተቱ መማር ሲገባው  ወደ ሌላ የግጭት አዙሪት አገርንና ሕዝብን የሚከት፤ የክልሉን ወጣት ለአመጽ የሚጋብዝ " ነው ያለው ፓርቲው " በዚህም ከቀደሙት መደበኛ ጦርነትና የሽምቅ ውጊያ ሂደቶች ትምህርት ያልወሰደ፣ የሚያስከትለውንም መጠነ ሰፊ ጉዳት እና መዘዝ በአግባቡ ያላገናዘበ አደገኛ የማንአለብኝነት አካሄድ እየተከተለ ነው " ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

ስለዚህ መንግሥት ከጀመረው የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ፣ የድርጅቶችን የንግድና የገንዘብ እንቅስቃሴ የማገድ ሂደት ወዘተ. በእሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ አካሄዶች ራሱን አቅቦ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ በሚችሉበት ሁኔታዎች ላይ ብቻ እንዲያተኩር አጽንዖት ሰጥቷል።

ከዚህ ውጭ የድርድርና የውይይት ፍኖትን ባለመሻት መንግሥት በማንአለብኝነት አካሄዱ ቀጥሎ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ውድመት ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ እናት ፓርቲ በጽኑ እንደሚያምን ገልጿል።

እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ፥ በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦች መፅናናት ተመኝቶ ፤ ምርመራ ባልተካሄደበትና ጥፋተኞች በአግባቡ ባልተለዩበት ሁኔታ የሚደረጉ ፍረጃዎች የፍትህ አሰጣጡን እንደሚያዛባው ገልጿል።

(ፓርቲው የላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia