TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#StopHateSpeech #ኢትዮጵያን_እናድን!

በማህበራዊ ሚዲያ በየቀኑ የሚታየው #የጥላቻ_ንግግር ሀገራችንን ወደለየለት ቀውስ ውስጥ እና ወደማንወጣው #አስከፊ ችግር ውስጥ ይከታታልና ሁላችንም የጥላቻ ንግግሮችን በመቃወም፤ ተሳዳቢዎችን ከተቻለ ለማረም ካልሆነም #Block በማድረግ ይህች ሀገራ እየሄደችበት ካለው የቁልቁለት ጉዞ በፍጥነት ልናስቆማት ይገባል።

#የፀረ_ጥላቻ_ህጉ_ይፍጠንልን!!
#የፌደራል_ጠቅላይ_አቃቤ_ህግ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ

ኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ፅኑ ታማሚዎች 752 ደርሰዋል።

የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ አንስቶ ይህን ያህል የፅኑ ታማሚ ቁጥር አልተመዘገበም።

ባለፉት 24 ሰዓታት የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉን ከጤና ሚኒስቴር የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ ያዕቆብ ሰማን (MoH) ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተጨማሪ ከተደረገው 7,659 የላብራቶሪ ምርመራ 1,981 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ትላንት 1,052 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ሁኔታው #አስከፊ ወደሆነ ደረጃ እየተሸጋጋረ ስለሆነ በምትችሉት አቅም ሁሉ እራሳችሁንና ቤተሰቦቻችን ከወረርሽኙ ጠብቁ እንላለን።

@tikvahethiopia
#Ethiopia : አጫጭር መረጃዎች ፦

- የዳሸን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ከታህሳስ 12 ጀምሮ አቶ ዱላ መኮንንን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ ሰይሟል። አቶ ዱላ የሊቀመንበርነቱን ቦታ የተረከቡት በግል ምክንያት ከኃላፊነታቸው በለቀቁት አቶ ነዋይ በየነ ምትክ መሆኑን ዳሸን ባንክ አሳውቆናል።

- በ2 ወር ውስጥ በ 'አይዞን ኢትዮጵያ' በጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሰብስቧል። በውጭ አገራት ከሚኖሩ ከ23 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ነው ገንዘቡ የተሰበሰበው።

- የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከዛሬ ታህሳስ 21 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ጥር ወር ጀምሮ ወደ በርበራ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል።

- ገቢዎች ሚኒስቴር በ5 ወር በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በመቐለ ገቢዎች ሚኒስቴርና ጉምሩክ ኮምሽን ቅርንጫፎች 1.8 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቢያቅድም ምንም ገቢ እንዳልሰበሰብ፤ በኮምቦልቻ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮምሽን ቅርንጫፎች 2.3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 1.9 ቢሊየን ብር ብቻ ለመሰብሰብ እንደተቻለ አሳውቋል። በዚህም ከመቐለ እና ኮምቦልቻ 4 ቅርንጫፎች ይሰበሰባል ተብሎ ከታቀደው 3.3 ቢሊየን ብር ውስጥ 1.9 ቢሊየን ብቻ ሲሰበሰብ ቀሪው 2.3 ቢሊየን ብር ሳይሰበሰብ ቀርቷል።

- በሶማሊ ክልል በጨረቲ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ አርብቶ አደር ወገኖቻችን በአካባቢያቸው በተከሰተ #አስከፊ ድርቅ እና በበሽታ ምክንያት ግመሎቻቸው እና ከብቶቻቸው እየሞቱ መሆኑን በመግለፅ መንግስት ይደርስላቸው ዘንድ ተማፅነዋል። በርካቶች አካባቢያቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል። ውሃና የምግብ ሬሽን በአስቸኳይ ካልደረሰላቸው ከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚወድቁ ለSRTV ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ስለ ወቅታዊ የሰሜን ኢትዮጵያ ምን አዲስ ነገር አለ ?

1. ህወሓት ከሰሞኑን የአማራ ክልል ፤ ሰሜን ወሎን በመልቀቅ መውጣቱን እና የወጣውም የቦታ ማሻሻያ ለማድረግ መሆኑን በመግለፅ አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ተመልሶ ሊገባ እንደሚችል ባወጣው በመግለጫ አሳውቋል።

ህወሓት በራሴ ስለመውጣቴ በላጎ፣  ቃሊም፣ ወርቄ፣ ተኩለሽ ጎብየ ፣ ቆቦ ያለው ህዝብ በደንብ ያውቀዋልም ብሏል።

ምንም እንኳን ህወሓት የሰሜን ወሎ አካባቢያዎችን በራሴ ለቅቄ ወጣሁኝ ቢልም የቆቦ አስተዳደር የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል ፣ ፋኖ ፣ የሚሊሻ / በጥምር ጦሩ ህወሓትን " አይቀጡ ቅጣት በመቀጣት " አካባቢውን ነፃ እንዳደረጉ በይፋ አሳውቋል። በፌዴራል መንግስት ሆነ በአማራ ክልል መንግስት በኩል #እስካሁን የተሰጠ አስተያየት ሆነ የተባለ ነገር የለም።

2. የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ህወሓት በቆቦ በጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶችንና የህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ውድመት ማድረሱን ከከተማው ነዋሪ ቤትም ገንዘብ ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶችን መዝረፉን ገልጿል። በተጨማሪ በተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች ሴቶች መደፈራቸውን የገለፀው ዞኑ ህወሓት በህብረተሰቡ ላይ ያደረሰውን ሰብዓዊ፣ ቁሳዊና አካላዊ እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ጉዳት በዝርዝር እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

3. ህወሓት ዛሬ በትግራይ ክልል ፤ አዲዳይሮ ከተማ ላይ የድሮን ድብደባ ተፈጽሞ በርካታ ህፃናት እና አረጋውያን ንፁሃን ሰለባ መሆናቸውን ገልጿል። የድሮን ጥቃቱ ሰለባ ያደረጋቸው ተፈናቃዮች መሆናቸውንና እነዚህ ተፈናቃዮች አዲስ ባገረሸው ጦርነት ሳቢያ በቅርቡ ከአዲያቦ የተፈናቃዮች መጠለያ ተፈናቅለው የነበሩ መሆኑን ገልጿል።

NB. ከቀናት በፊት ህወሓት ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ባለችው " አዲ ዳዕሮ "  ላይ የኤርትራ ኃይል የአየር ጥቃት ሰንዝሮ ንፁሃን ሰለባ እንደሆኑ ገልጾ ነበር። ለዚህ የህወሓት ክስ በኤርትራ በኩል የተሰጠ ምላሽ አልነበረም።

ነገር ግን ይኸው ክስ ከ " ህወሓት " በተሰማ ሰሞን በኢትዮጵያ መንግስት ስር ያለው የ " ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ " በትግራይ ክልል ' ዓዲ ዳዕሮ ' የኢትዮጵያ አየር ኃይል በተመረጡ ዒላማዎች ወታደራዊ ቁሳቁስና ተተኳሾች ያሉበትን ቦታ ዒላማ አድርጎ እርምጃ መውሰዱን አሳውቆ ነበር።

መረጃ ማጣሪያው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በንጹሃን ላይ ጉዳት ሳያደርስ በከፍተኛ ጥንቃቄና የዒላማ ጥራት የህወሓትን ወታደራዊ አቅሞች ነጥሎ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ነበር በወቅቱ አሳውቆ የነበረው።

4. ዳግም ባገረሸው ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ እና በተለያዩ ከተሞች የነበሩ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው መመለስ ጀምረዋል ሲል ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። ወደ ቆቦ ከተመለሱ መካከል ኔትዎርክ ወደ ሚሰራበት ቦታው ወጥተው የደወሉ ከተፈናቀሉበት ወደ ቀያቸው ሲመለሱ አንድም ንብረታቸው እንደሌለ ገልፀዋል። በቤት ውስጥ የነበሩ ንብረቶች አንድም ሳይቀር እንደተወሰደባቸው ፤ ከብቶች ፣ ፍየሎች እና በጎችም ሁሉ ታርደው ተበልተው እንደጠበቋቸው አንድ ግለሰብ ተናግረዋል።

5. የመርሳ ከተማ አስተዳደር ፤ በከተማው ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች አካባቢያቸው ነፃ መውጣቱን ተከትሎ ወደቄያቸው እየተመለሱ መሆኑን ዛሬ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል  አሳውቋል። ወንዶች ከትላንት ማታ ጀምረው መውጣታቸውን ፣ ህፃናት ፣ እናቶች ፣ ሴቶች ደግሞ ከጥዋት ጀምሮ ወደ ቄያቸው እየተመለሱ መሆኑን አመልክቷል። በመርሳ ከተማ እስከ 40 ሺህ የሚደርሱ የራያና ቆቦ ወረዳ ተፈናቃዮች በመጠለያዎችና ከህብረተሰቡ ጋር ተጠግተው ይኖሩ እንደነበር ከተማው አመልክቷል።

6. የአውሮፓ ፓርላማ ነገ ረቡዕ ስብሰባ እንደሚያደርግ የተነገረ ሲሆን በዚህ ስብሰባው በአፍሪካ ቀንድና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይወያያል ተብሏል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመወያየት የያዘው አጀንዳ ፤ " በትግራይ ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ እና የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በተለይ የህጻናት ሁኔታ "  እንደሆነ ተሰምቷል።

7. የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በዝርዝር ሳያብራሩ የድርጅታቸው የሰብአዊ እርዳታ ባልደረቦች ከበርካታ ሳምንታት እገዳ በኋላ ዛሬ ከትግራይ ክልል በሰላም መውጣት መቻላቸውን ገልፀው በዚህ "በጣም እፎይታ" እንዳገኙ ገልፀዋል።

" ይህ አበረታች ዜና ነው " ያሉት ግሪፊትስ " ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች ያለችግር እንደሚሄዱ አምናለሁ " ብለዋል። ይህ #አስከፊ_ግጭት ማብቂያ እንዲኖረው ውይይት ብቸኛው መንገድ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ግሪፊትስ ለሁሉም ወገኖች ፦ ድርድሩን እንዲቀጥሉ ፤ ሁሉንም ሰላማዊ ሰዎች እንዲጠብቁ ፤ የሰብአዊ ሰራተኞችን ደህንነት እና ለተቸገሩ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መዳረሻ እንዲያረጋግጡ ፤ ፈጣን እና ያልተቋረጠ የሰብአዊ አቅርቦቶች ወደ ክልሉ (ትግራይ ክልል) እንዲገቡ እንዲፈቅዱ እጠይቃለሁ ብለዋል።

@tikvahethiopia
#IOM

" በቅርብ ከደርሱት #አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው " - የተመድ የስደተኞች ድርጅት

ስደተኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ተገልብጦ፣ ሕፃናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ60 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የተመድ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።

ቅዳሜ የደረሰው አደጋ፣ ወደ #አውሮፓ ለመሻገር በሚሹ ስደተኞች ላይ በሜዲትሬንያን ባሕር ላይ በቅርቡ ከደርሱት አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው ተብሏል።

የተመድ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እንዳለው፣ 86 ሰዎችን ይዛ ስትጓዝ የነበረው ጀልባ፣ ከፍተኛ ማዕበል ገጥሟት በሊቢያ ምዕራባዊ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው " ዙዋካ " ከተሰኘች ከተማ አቅራቢያ ስትገለበጥ 61 ሰዎች #ሰምጠዋል

ድርርቱ ማዕከላዊው የሜዲትሬንያን ባሕር፣ ለፍልሰተኞች አደገኛ የጉዞ መሥመር መሆኑ ቀጥሏል ብሏል።

#ሊቢያ በጦርነት በመታመስ ላይ ያለች አገር ብትሆንም፣ ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ #ሁከትን እና #ድህነት በመሸሽ ወደ አውሮፓ መሻገር ለሚፈልጉ ስደተኞች ተመራጭ መተላለፊያ ሆናለች፡፡

የስደተኞች ድርጅቱ እንደሚለው፣ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈርንጆች 2023 ብቻ ከ2 ሺሕ 500 በላይ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በባሕር ላይ #ሕይወታቸውን_አጥተዋል

መረጃው የቪኦኤ ነው።

@tikvahethiopia