TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የአዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ የምረቃ ስነ ስርዓት እየተካሄ ይገኛል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ #ለማ_መገርሳና የአማራ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው፣ ዶ/ር #አርከበ_ኤቁባይ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵየ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ዶ/ር #አርከበ_እቁባይ የጃፓንን ከፍተኛ ሽልማት ከንጉሳቸው ትናንት ተቀብለዋል። ይህ The Order of the Rising Sun, Gold and Silver የተባለው ሽልማት ኢትዮጵያ ውስጥ ላከናወኑት በጎ ተግባር የተበረከተ ነው ተብሏል።

©ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

ዶክተር #አርከበ_እቁባይ "ከህወሀት ጋር #ተለያይተዋል" ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አረጋገጠ። ጋዜጠኛው በማዕበራዊ ሚዲያ በተሰራጨው መረጃ ዙሪያ ከዶ/ር #አርከበ ጋር በኢሜይል በተለዋወጠው መልዕክት "ዶ/ር አርከበ ከህወሀት ጋር ተለያይተዋል!" የሚለው መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል። ዶ/ር አርከበ በጉዳዩ ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ በፅሁፍ የሰጡት አጭር ምላሽ፦ "አመሰግናለሁ! ይህ #ስህተት ነው"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አርከበ ሆስፒታል ናቸው...

"በሚንስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚንስትሩ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር #አርከበ_እቁባይ ታመው ቤልጅዬም በሚገኝ ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ።" ይህ መረጃ #PetrosAshenafi እና ethiopiaobserver.com ናቸው ያወጡት።

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia