TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቦይንግ

ዛሬ የተከሰከሰው #ቦይንግ_737_Max ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየው አይነት አውሮፕላን ሲሆን አየር መንገዱ ካሉት በጣም #አዲስ አውሮፕላኖች አንዱ ነው። የዚህ አውሮፕላን አይነት ስሪት ጥቅምት ወር ላይ #ኢንዶኔዥያ ላይ ተከስክሶ 189 ሰዎች ሞተው ነበር።

Via Elias Mesert
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake Video‼️

በማህበራዊ ሚዲያ(በተለይም በfacebook) #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ ንብረት የሆነው #ቦይንግ_737 "ከመከስከሱ በፊት" ተብሎ እየተሰራጨ የሚገኘው #ቪድዮ_ሀሰተኛ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ትናንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ቦይንግ 737 #ET302 አውሮፕላን የተከሰከሰበት ቦታ በቁፋሮ የወጡ ነገሮችን ከላይ ባለው ፎቶ መመልከት ይቻላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አብራሪዎቹን ለማሰልጠን የሚያስችሉ የተሟሉ ሰባት ምስለ በረራዎች ወይም የበረራ ማሰልጠኛዎች አሉት።

•በአሁን ወቅት ብቁና የተሟሉ ኪው 400፣ ቢ737 ኤን ጂ፣ ቢ 737 ማክስ፣ ቢ 767 ፣ ቢ 787 ፣ ቢ 777 እና ኤ 350 የተሰኙ ሰባት ምስለ በረራዎች አሉት።

•በዋሽንግተን ፓስት የወጣው መረጃ በመረጃ ላይ ያልተደገፈና #የተሳሳተ ነው።

•ማነነታቸው ካልታወቁ አካላት ተገኙ ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ ከበረራ ስለታገደው #ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ትኩረት ለማስቀየር ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር በነበረው #ቦይንግ_737_ማክስ አውሮፕን የደረሰው አደጋ ከመከሰቱ በፊት የአሜሪካ አውሮፕላን አብራሪዎች ቡድን በዚህ መሰል አውሮፕላኖች የደህንነት ስጋት እንዳለ ለኩባንያው አሳውቀው አንደነበር ተገለፀ፡፡ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በኢንዶኔዥያ ከደረሰው አደጋ በኋላ ሙከስ ተብሎ በሚጠራው መቆጣጠሪያ ስርዓት ላይ ችግር እንደነበረበትና በአፋጣኝ እንዲፈታ አሳስበው እንደነበር ተገልጿል፡፡ የአሜሪካው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ፣ ቦይንግ ግን አብራሪዎች ያነሱትን ጥያቄ ወደጎን በመተው ወደ ፊት የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌሩን ለማስተካከል ቃል መግባቱን ዘገባው አክሏል፡፡ ኩባንያው ባለሙያዎቹ ያቀረቡትን ስጋት ባለመቀበሉ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡ ከችግሩ ጋር በተያያዘም በዓለም ላይ የነበሩ ሁሉም የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች እንዳይበሩ መታገዳቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia