TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETH የተሰሩ ተግባራት!

√2007 ዓም--ከዛሬዎቹ ቤተሰቦች 600 መፅሃፍትን በማሰባሰብ በሃዋሳ ከተማ ለሚገኝ ላይብረሪ ድጋፍ አድርጓል/መፅሃፉ የተሰባሰበው ከተማሪዎች እና ሰራተኞች ነው/

√2007 ዓም -- ሀዋሳ ከተማ በተዘጋጀ ልዩ የበጎ አድራጎት እና የጥበብ ፌስቲቫል የተገኘ 5,000 ብር ለአረጋዊያን ድጋፍ ተደርጓል።/ብሩ የተገኘው በተዘጋጀው ልዩ ዝግጅት ላይ ከተገኙ ሰዎች ነበር በወቅቱ መግቢያው 15 ብር ነበር/ በተጨማሪ ሜሪጆይ ለሚገኙ አረጋዊያን የአልባሳት ድጋፍ ለማድረግ ተሞክሯል።

√2008 ዓም--በተመሳሳይ 400 መፅሃፍትን በማሰባሰብ ድጋፍ ተደርጓል። እንዲሁም የመማር አቅም ለሌላቸው 25 ተማሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል/ድጋፍ የተደረገው በወቅቱ ልዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅት በማዘጋጀት በተገኘ ገቢ ነው/

√2009 ዓም--በተመሳሳይ ከ300 በላይ የመማሪያ መፅሃፍትን በማሰባሰብ ገቢ ማድረግ ተችሏል። በውቅቱ ለአዲስ አመት ዋዜማ በተዘጋጀ ዝግጅት እንዲሁም ከተለያዩ ድርጅቶች እየዞረ በተሰበሰበ የትምህርት ቁሳቁስ የ30 ተማሪዎችን የትምህርት ወጪ መሸፈን ተችሏል።

√2010 ዓም--ከአለን ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመሆን 1000 መፅሃፍትን ለማሰባሰብ ተችሏል።

√2011 ዓም--በሀገሪቱ ያለውን ችግር እንዲፈታ ለማገዝ እና ወጣቶች ለሀገራቸው እንዲቆሙ የStopHateSpeech መድረኮችን እያዘጋጀ ይገኛል።

ከላይ ያሉት ጥቂት ስራዎች ናቸው👆

TIKVAH-ETH በቴሌግራም ከመጣ በኃላስ፦


√ወቅታዊ እና የተመረጡ መረጃዎችን ከየተኛውም ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ እያደረሰ ይገኛል።

√ጥቆማዎችን ያደርሳል

√የተቸገሩ ወገኖችን ህይወት ለማትረፍ ይረባረባል።

√የታመሙትን ይጠይቃል።

√ጠንካራ ሀገር እንዲገነባ በገለልተኝነት የተለያዩ የአስተሳሰብ ማጎልበቻ ስራዎችን ይሰራል።

√ሰላም እና አንድነት ላይ ያተኮሩ ሀገር አቀፍ ስራዎችን ይሰራል።

በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ፦

TIKVAH-ETH ከየትኛውም የመንግስት እና የግል ተቋማት ጋር አብሮ #አይሰራም። መሪዎቹ የቤተሰቡ አባላት ናቸው። እስከዛሬ በማንም ተፅኖ ስር ያልወደቀ ነው። የገንዘብ ምንጩ የቻናሉ ማስታወቂያ ብቻና ብቻ ነው።

እስከዛሬም በተሰሩት ስራዎች፦ የትኛውም የመንግስት አካል #በገንዘብም #በሀሳብም የደገፈን #የለም። ሁሉም ስራ በቻናሉ አባላት የሚሰራ ብቻ ነው።

እኔም፦
√ከፖለቲካ ወግንተኝነት ነፃ ነኝ
√የየትኛውም ድርጅት አባልም ተከታይም አይደለሁም
√ከየትኛውም ድርጅት ጋር ትውውቅ የለኝም

አመሰግናለሁ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia