TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የውጪ ሀገራት ጉዞ⬇️

"ስምምነት ከተደረገባቸው አገራት ውጪ የሚደረግ ሕገወጥ ጉዞ መቆም አለበት" ም/ጠ/ሚ/ ደመቀ መኮንን
*
*
*
ባለድርሻ አካላት ኢትዮጵያ ስምምነት ካደረገችባቸው 3ቱ የአረብ ሀገራት የውጭ ሀገር ጉዞ ውጪ የሚደረገውን ሕገወጥ ጉዞ በማስቆም የድርሻቸውን እንዲወጡ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ፡፡

ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ኃላፊነት ለተሰጣቸው የፌዴራል ፖሊስ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች መምሪያ፣ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣንና ኢትዮጵያ አየር መንገድ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ደመቀ መንግሥት መስራት ለሚችሉ ዜጎች በሀገር ውስጥ ምቹ የሥራ ዕድሎች የሚስፋፊበት ሁኔታ ለመፍጠር የሚያደርገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መብታቸው ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ ባላቸው ችሎታና አቅም ሰርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2ዐዐ8 ማውጣቱን ለተቋማቱ በፃፉት ደብዳቤ አመልክተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት አሁን ላይ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈርሞ ሰራተኞችን ለመላክ ቅድመ ዝግጅት የተደረገባቸው ሀገራት #ሳዑዲ_አረቢያ#ኳታር
እና #ጆርዳን ብቻ መሆናቸውንም በደብዳቤያቸው ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም ግን የሁለትዮሽ ስምምነት ካልተደረገባቸው ሀገራት መካከልም ኩዌት፣ ባህሪን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ቤይሩት እና ኦማን በተለያዩ የቪዛ አይነቶች ማለትም በቱሪስት በዘመድ ጥየቃ፣ በጉብኝት፣ በንግድ በመሳሰሉት ምከንያቶች ከሀገር እየወጡ ሕገወጥ የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ግለሰቦች እንዲሁም በዚህ መልኩ ዜጎችን ወደ ውጭ የሚልኩ ኤጀንሲዎች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑም በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የመብት ጥሰት ለመታደግ የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተደረገባቸው ሀገራት በተለያዩ የቪዛ አይነቶች ለሥራ የሚሄዱ ዜጎች እና በዚህ ሁኔታ ዜጎችን የሚልኩ ኤጀንሲዎች ድርጊታቸው ሕጋዊ መሠረት የሌለው መሆኑ ታውቆ ጉዳዩ የሚመለከታቸው እነዚህ ተቋማት በሙሉ ሀገራዊ የሥራ ስምሪቱ በይፋ ከተከፈተበት ከመስከረም 30/2011 ጀምሮ ሕገወጥ አሠራሩ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሼህ አላሙዲ‼️

"ሼህ አላሙዲ ወደ #አዲስ_አበባ ይምጡ፤ #ሳዑዲ ይቆዩ #አናውቅም"- ጠበቃቸው
.
.
ላለፈው አንድ ዓመት ከሁለት ወር በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የቆዩት ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ከእስር #መፈታታቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቱጃር ከእስር የተፈቱት ዛሬ ከሰዓት መሆኑን ጠበቃቸው አቶ ተካ አስፋው ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ገልጸዋል።

አቶ ተካ ሼህ አላሙዲንን #በስልክ ባይነጋግሯቸውም ከወንድማቸው ጋር አብረው እንዳሉ #አረጋግጩያለሁ ብለዋል። “ዛሬ ተፈትተዋል። አሁን ከሪያድ ወደ ጅዳ እየሄዱ ነው፤ ወደ ቤታቸው ማለት ነው። አጠገባቸው ካለ ሰው ጋር ተገናኝተናል። አዲስ አበባ ይምጡ፣ እዚያው ይቆዩ የምናውቀው ነገር የለም። እኛ አሁን #በመፈታታቸው ብቻ ደስታ ላይ ነው ያለነው።”

ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በከፈተው የጸረ-ሙስና ዘመቻ ከሌሎች ቱጃሮች፣ ልዑላን፣ ሚኒስትሮች እና ባለስልጣናት ጋር በጥቅምት ወር 2010 ዓ. ም. ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት። ከእርሳቸው ጋር ታስረው የነበሩ ቢሊየነሩ ልዑል አልዋሊድ ቢን ታላልን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር ድርድር ካደረጉ በኋላ እንደተፈቱ ሲገለጽ ቆይቷል። ሼህ አላሙዲ ስለተፈቱበት ሂደት የተጠየቁት ጠበቃቸው “ዝርዝሩን አላወቅንም። እኛ የምናውቀው መፈታታቸውን ብቻ ነው” ሲሉ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሳዑዲ አረቢያ በወጣቱ አልጋወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን የሚመራ የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ካቋቋመች በኋላ 11 ልዑላንን ጨምሮ 200 ገደማ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎችን አስራ ነበር። ልዑላኑ እና ቱጃሮቹ ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሳምንታት በሪያድ በሚገኝ ባለአምስት ኮከቡ ቅንጡ ሆቴል እንዲታሰሩ መደረጉ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል። ተጠርጣሪዎቹ ሆቴሉን እንዲለቅቁ ከተደረጉ በኋላ በታሰሩበት ስፍራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጸምባቸዋል የሚል ወቀሳ ሲሰማ ቆይቷል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሳዑዲ_አረቢያ

ኢትዮጵያውያን በስራ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመቀየር ብለው ሀገራቸውን ጥለው በስደት በሚኖሩባት ሀገረ ሳዑዲ አረቢያ እንግልት ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ማሸማቀቅ፣ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሆነ እየገለፁ መሆኑ ይታወቃል።

በእስር ቤት ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ስፍር ቁጥር የላቸውም።

በተለይ ደግሞ ከሰሞኑን የሳዑዲ አረቢያ ፀጥታ ኃይሎች መኖሪያ ፍቃድ ያላቸውም ሆነ የሌላቸውን እያፈሱ መሆኑ መገለፁ ይታወቃል።

የሳዐዲ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ ለምን ይህንን እያደረገ እንደሚገኝ ይፋዊ በሆነ መንገድ ስለመግለፁ ምንም አልተሰማም / መረጃም የለም።

ዛሬ በሳዐዲ አረቢያ ከሚገኙ ዜጎቻችን ጋር በተገናኘ በሰማነው መረጃ የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካን ወደ ሳዑዲ አረብያ ሄደዋል።

የልዑካን ቡድኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ሃላፊዎችን ያካተተ ሲሆን በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ይመክራል ተብሏል።

የስደተኞች መብት አጠባበቅና ስደተኞች ወደ ሃገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ዙርያ ከሚመለከታቸው የሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት ጋር መወያየት የልዑኩ ዋነኛው ተልኮ ነው።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ችግር ለማቃለልና በክብር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የሳዑዲ አረብያ መንግስት ትብብር በጣም አስፈላጊ ነው ብሏል። በሳዑዲ አረቢያ ከሚደረገው ውይይት የሚገኘው ዉጤት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር አንዱ ማሳያ ይሆናል ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
" በ5 ወር 27,800 ሰዎች ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን ተሻግረዋል " - IOM

እንደ ተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ (IOM) ፤ ባለንበት በዚህ ዓመት 2022 (እኤአ) /በ5 ወር/ ቢያንስ 27,800 ሰዎች ከአፍሪካ ቀንድ በጦርነት ወደምትታመሰው ወደ #የመን ተሻግረዋል ፤ ይህ ደግሞ በ2021 ሙሉ ዓመት ከተደረጉት ጉዞዎች ሁሉ የሚበልጥ ነው። (በ2021 ዓመት 27,700 ነበር)

IOM በዚህ ደረጃ ቁጥሩ ከፍ እንዲል ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የCOVID-19 እንቅስቃሴ ገደቦች መቃለላቸው ፣ የበለጠ ምቹ የአየር ሁኔታ መኖር እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ እና ድርቅ ይጠቀሳሉ ብሏል። (አብዛኞቹ ስደተኞች ከኢትዮጵያ መሆናቸው ተጠቅሷል)

IOM በቅርቡ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ በፍቃደኝነት የሚመለሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለመደገፍ የ7.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ጠይቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ በሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች በየመን በኩል ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመድረስ በማሰብ አደገኛውን የኤደን ባህረ ሰላጤ ያቋርጣሉ።

ስደተኞቹ በዋናነት ዓላማቸው ወደ የመን ሰሜናዊ ጎረቤት ወደሆነችው #ሳዑዲ_አረቢያ ለመድረስ ነው።

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

#ሳዑዲ_አረቢያሳዑዲ አረቢያ የሃጅ ተጓዦችን እየተቀበለች ትገኛለች። ከቀናት በፊት የመጀመሪያው የሃጅ ተጓዦች ቡድን ከኢንዶኔዥያ ወደ ሳዑዲ መግባቱ ይታወሳል። ዛሬ ባገኘነው መረጃ እስከ ትላንት እሁድ ድረስ ከተለያዩ ሀገራት ለሃጅ ጉዞ ሳዑዲ የገቡ ተጓዦች 955 ደርሰዋል። ሳዑዲ አረቢያ ዘንድሮ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ 1 ሚሊዮን የሃጅ ተጓዦችን እንደምታስተናግድ ይታወቃል።

#ጀርመን ፦ የጀርመኑ መኪና አምራች ኩባንያ መርሴዲስ-ቤንዝ 1 ሚሊዮን ገደማ አሮጌ መኪናዎችን ለጥገና ጠርቷል። ኩባንያው እኚህ መኪናዎች ፍሬናቸው ችግር አለባቸውና ጠግኜ ልመልስላችሁ ብሏል። ኩባንያው መኪኖቹ ከፍተኛ በሆነ ዝገት ምክንያት የፍሬን ሰርዓታቸው ተገቢውን ሥራ ላይሰራ ይችላል ብሏል። ጀርመን ያሉ 70 ሺህ መኪናዎችን ጨምሮ ከ993 ሺህ በላይ መኪናዎች መጠገን አለባቸው።

#UK ፦ ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመርያ ጊዜ ኤም 270 የተባሉ ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን ልትሰጥ ነው። እነዚህን እጅግ ዘመናዊ ሮኬት ማስወንጨፍያ መሣሪያዎች መቼ እና በምን ያህል መጠን ወደ ዩክሬን እንደምትልክ አልገለጸችም።

#ሩስያ ፦ የሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ልከዋል። ሀገሪቱ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ልገሳ እንድታቆም ያስጠነቀቁ ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርሰው ጥቃት መጠኑ እየሰፋ እንደሚመጣ ገልፀዋል። አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ዘመናዊ ተወንጫፊ ሚሳኤል ሲስተምን ወደ ዩክሬን ልካለች። አሜሪካ መሣሪያውን ብትሰጥም ዩክሬን ይህን መሣሪያ ወደ ሩሲያ ግዛት እንዳትተኩስ አሳስባ ነው።

#ቢቢሲ #ሳዑዲጋዜቴ #ኤፒ

@tikvahethiopia
#ሳዑዲ_አረቢያ

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሪያድ የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን እቃዎች ከሱቆች እና ከመደብሮች እየሰብሰበ ይገኛል።

የሳዑዲ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ያስተዋውቃል በሚል የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን አሸንጉሊቶች፣ ቲሸርቶች፣ የጸጉር ማስያዣዎች፣ ኮፊያ፣ እና የእርሳስ መያዣወችን ከየመደብሩ እንዲሰበሰቡ እያደረገ ነው።

የሀገሪቱ መንግስት ህፃናትን ለመጠበቅ ሲል " መርዛማ መልዕክት " የያዙ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚያስተዋውቁ ቀለም ያላቸውን እቃዎችን ከሱቅ እና ከመደብር እየሰበሰበ መሆኑን ገልጿል።

አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እቃዎቹ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነውን ማህበረሰብ ሞራልና እሴት የሚጻረሩ እንዲሁም አዲሱን ትውልድ ለተመሳሳይ የፆታ ግንኙነት የሚያበረታቱ ናቸው ብለዋል።

የሳዑዲ ንግድ ሚኒሰቴር በትዊተር ገፁ ፤ እቃዎቹን የመሰብሰብ ዋና ትኩረት " ለሳውዲ ህዝብ እሴቶች የማይመጥን ቀለም ያላቸው እቃዎች " ማስወገድ ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ መሰል እቃዎችን ሲሸጡ በሚገኙ ሱቆች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ከዚህ ባለፈ ሳዑዲ አረቢያ በቅርቡ ሁለት የዲስኒ እና ማርቭል ፊልሞችን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ያስተዋውቃሉ በሚል አግዳለች።

በሳዑዲ አረቢያ ምድር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ህገወጥ ሲሆን #እስከሞት ድረስ ያስቀጣል።

ቪድዮ - DW

@tikvahethiopia