TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013_እና_አዲስአበባ

ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ምርጫ ሂደት ላይ በፓርቲዎች (በተለይ ደግሞ በባልደራስ ፓርቲ) ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች እና አቤቱታዎች በተወሰኑት ላይ ምላሽ ሰጥቷል።

ለቅሬታዎቹ እና አቤቱታዎቹ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ናቸው።

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በየምርጫ ጣቢያው በተለጠፈው የውጤት መግለጫ ወረቀት ላይ ተሰረዟል/ተደልዟል ስለሚባለው ጉዳይ ?

ወ/ሪት ሶሊያና : ምርመራ አድርገናል ፤ የየምርጫ ክልል ኃላፊዎች ስርዝ ድልዝ ተደረገበት የተባለውን ጣቢያ ተመልከትው ችግር ይኑርበት አይኑርበት የሚለውን ድጋሚ ቆጥረው እያረጋገጡልን ነው፤ የውጤት ማሳወቅ ሂደት ላይ ስርዝ ድልዝ መኖሩ ነው እንጂ ችግር ያለበት አልተገኘም፤ በቆጠራው ላይ ያለው እና የተፃፈው ቁጥር ትክልል ነው የሚል ሪፖርት ደርሶናል።

የምርጫ ቆጠራው ችግር አለበት ስለሚባለው ጉዳይ ? (ባልደራስ ፓርቲ ያቀረበው ቅሬታ)

ወ/ሪት ሶሊያና : በአዲስ አበባ አብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሁሉም ፓርቲ ወኪሎች ተገኝተው ነው ቆጠራ የተደረገው ፤ አ/አ ላይ የፓርቲ ወኪል ለምርጫ ጣቢያ ልኮ የምርጫ ጣቢያ አልቀበልም ያለበት ምንም አይነት ምርጫ ጣቢያ የለንም ፤ ሁሉም ቦታዎች የፓርቲ ወኪሎች ተገኝተዋል ፤ እራሳቸው ወኪሎቻቸውን እስከላኩና አቅማቸው ፈቅዶ ከ1 ሺህ በላይ ጣቢያዎች ላይ እስካስቀመጡ ድረስ። ወኪሎቹ የምርጫ ሂደቱ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ተከታትለው ውጤቱ ላይ ፈርመዋል ሁሉም ቦታዎች ላይ ማለት ይቻላል። ወኪሎች ያሉባቸው ፊርማዎች ኖረውን ነው የመጣነው የምርጫ ሂደቱን ስናደርግ።

ይቀጥላል👇
#ምርጫ2013_እና_አዲስአበባ

ማንነታቸው የማይታወቁ ጣቢያዎች ተከፍተው ነበር ? (ባልደራስ ፓርቲ ያቀረበው ቅሬታ)

ወ/ሪት ሶሊያና : ፍፁም ሀሰት ነው። አዲስ አበባ ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ ጣቢያዎች የሉንም። ሁሉም ጣቢያዎች ኮድ አላቸው፤ ኮድ የሌላቸው ያገኘናቸው 2 ጣቢያዎችን እንኳን ድጋሚ ኮድ ሰጥተን ምርጫ እንዲካሄድ አድርገናል።

አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የባልደራስ ፓርቲን ውጤት እያሳነሱ እንዲፅፉ ተደርገዋል ? (የባልደራስ ፓርቲ ቅሬታ)

ወ/ሪት ሶሊያና : ይህ ፍፁም ሀሰት ነው። ፓርቲ ወኪሎች ያሉባቸው ቦታዎች ከሆኑ የፓርቲ ወኪሎቻቸው እራሳቸው ይህን አይተው ዝም አይሉም። ወኪሎቹ እራሳቸው እንደዚህ ያለ አቤቱታ አቅርበው (በእኔ ፓርቲ ላይ ያለው ውጤት በትክክል አልተቆጠረም/በትክክል አልተፃፈም ብለው) ያቀረቡት ሪፖርት የለም። ያን አይነት አቤቱታ የቀረበበት የምርጫ ጣቢያም የለንም።

በወረቀት እጥረት የተነሳ ደጋፊዎቻችን ወደቤቶቻቸው ሄደዋል ተብሎ ስለተነሳው ቅሬታ ?

ወ/ሪት ሶሊያና : እስከ ለሊቱ 7 ሰዓት ከ10 ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት አከናውነናል። የድምፅ መስጫ ወረቀት ባለመኖሩ የተቋረጠብን ምርጫ ጣቢያ የለም። ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት ነበር ነገር ግን ባለው እያካሄዱ እያለ ተጨማሪ ወረቀቶችን ማድረስ ችለናል። ስለዚህ መሰረታዊ የሆነ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ተቋርጦ የድምፅ መሥጫ ወረቀት ባለመኖሩ የተነሳ ሰው ተበትኖ/ተመልሶ ኑ ወረቀት መጥቷል እና ድምፃችሁን ስጡ የተባለበት አንድም ቦታ የለም፤ ስለዚህ ወረቀት አልቆ ደጋፊዎቼ ተመለሱ የሚለው በከፍተኛ ደረጃ #የተሳሳተ መረጃ ነው።

ይቀጥላል👇
#ምርጫ2013_እና_አዲስአበባ

በአዲስ አበባ ድምፅ ሰጪው ረጅም ሰልፍ ነበረበት የሚልም ቅሬታ ነበር ፤ይሄ ጉዳይ እንዴት ይታያል ?

ወ/ሪት ሶሊያና : ምንም ጥያቄ የለውም ፤ በተወሰነ ደረጃ የድምፅ ሰጪዎች መንገላታት ቢያሳዝንም በሌላ በኩል ሲታይ ድምፅ ሰጪዎች በድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይ ለመሳተፍ ረጅም ሰዓት ወስደው በከፍተኛ Trunout ወጥተው ድምፅ መስጠታቸው በጣም የሚያስደስት ነው፤ ይህም በቦርዱ በጥሩ ጎኑ የታየ ነው።

በአጠቃላይ በአ/አ የነበረው ምርጫ በወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፦

"... አዲስ አበባ በጣም ጥቂት ችግር ካለባቸው ፤ አብዛኛው የምርጫ ሂደት (ሁሉም ማለት ይቻላል) ፓርቲዎች ሆኑ የግል ተወዳዳሪዎች ወኪሎቻቸውን ያስቀመጡበት ፤ በቆጠራ ሂደቱ ላይ አብዛኛዎቹ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሂደቱ እስኪጠናቀ ድረስ ታዝበው #ፈርመው የሄዱበት የቆጠራ ሂደት ያካሄድንበት ነው። በእርግጥ በአዲስ አበባ ጣቢያዎቹ ብዙ ቢሆኑም በከፍተኛ ደረጃ የፓርቲ ወኪሎች የተገኙበት ፣ ታዛቢዎች የተገኙበት፣ ዜጎች በጣም በረጅም ሰልፍ ሰዓት ወስደው የመረጡበት ፣ እስከ ለሊቱ 7 ሰዓት ሰፍል ላይ ያለው ሰው እንዳይቋረጥ ብለን ማንኛውም ድምፅ ሰጪ ድምፁን እንዲሠጥ ያደረግንበት ፣ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ከልሎች ቦታዎች በተሻለ ሁኔታ ግልፅ የሆነበት እና ሚዲያን የሲቪክ ማህበራትም ፣ የፓርቲ ወኪሎች እኛም እራሳችን እየዞርን ያየንበት ነው።"

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia