TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተመድ ማስጠንቀቂያ‼️የአለም ሀገራት የምድራችን ሙቀት እንዳይጨምር አስፈላጊውን እርምጃ ካልወሰዱ እስከ አውሮፓዊያኑ 2030 ባለው ጊዜ የከፋ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት/ተመድ/ #አስጠነቀቀ፡፡

ድርጅቱ ይሄን ያስታወቀው ከአውሮፓዊያኑ 2030 ወዲህ የአለም ሙቀት ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ #ሊጨምር እንደሚችል ከተነበየ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ይሄም ሁኔታ እውን ከሆነ በአለም በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የከፋ ድርቅ፣ ሰደድ እሳት፣ ጎርፍ እና የምግብ እጥረት እንደሚከሰት የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል ገልጿል፡፡

ድርጅቱ እዚህ መደምደሜያ ላይ የደረሰው ለአለም ሙቀት መጨመር ምክንያት የሆነው የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት አሁን ያለበትን ደረጃ ጥናት በማድረግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

አሁን ላይ የአለም ሙቀት በ1 ዲግሪ ሴልሺየስ እየጨመረ ሲሆን ይህን ሁኔታ እንዳይባባስ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የአለም መንግስታት አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡

የአለም ሙቀት ከ1 ነጥብ 5 ድግሪ ሴልሺየስ የዘለለ እንዳይሆን እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ የአለም የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ልቀት በ45 በመቶ ሊቀንስ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ሲኤንኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia