TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #US የማይክ ሐመር ስለ ኢትዮጵያ ቆይታቸው ምን አሉ ? አሜሪካ የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነቷን እና #የግዛት_አንድነቷን_በማክበር ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላትን ፍላጎት እንደሚያረጋገጡ የሀገራቸውን አቋም ገልፀዋል። በአሜሪካ ህዝብ ለጋስነት ሀገሪቱ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን አመልክተዋል። ሰላምን በማረጋገጥ በኩል የጋራ ፍላጎቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት…
#USA

በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሏል።

ልዩ መልዕክተኛው ከነገ ጀምሮ ወደ እስከ መስከረም 5 /2015 ኢትዮጵያ እና ወደ ቀጠናው ሀገራት እንደሚጓዙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል።

በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ዳግም ያገረሸው ግጭት እንዲቆም እና የሰላም ንግግር እንዲጀመር ግፊት ያደርጋሉ ተብሏል።

አምባሳደር ሐመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው የኢትዮጵያ መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናትን ያነጋግራሉ።

በተጨማሪ የተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎችን ከሚወክሉ የሲቪል ማህበራት እና የፖለቲካ ተዋናዮች ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ህዝብ ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት እና ብልፅግና ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማጎልበት እንደሚቻል ይወያያሉ።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #ለግዛት_አንድነት ቁርጠኛ ነኝ ስትል በድጋሚ አረጋግጣለች።

አምባሳደር ሐመር ከሳምንታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አዲስ አበባ እና መቐለ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ህወሓት አመራሮች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ህወሓት /TPLF/ ከትግራይ ውጭ እየፈፀመ ያለውን ጥቃት ፤ የኢትዮጵያ መንግስትን የአየር ጥቃት እና የኤርትራን ዳግም ወደ ግጭት መግባቷን እንደምታወግዝ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን በኩል አሳውቃለች።

ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና በሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ የሚደረገውን ጥረት እንዲያጠናክሩ ጠይቃለች።

Via US Embassy AA

@tikvahethiopia