TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተሰጠ ማሳሰቢያ!

የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ (የዩኒቨርስቲ መግብያ ) ፈተና ከመስከረም 24/2013 ዓ/ም ጀምሮ ይሰጣል ተብሎ በማህበራዊ ሚድያና በአንዳንድ ቴሌግራም ቻናሎች ሃሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ተማሪዎችንና ወላጆችን ውዥንብር ውስጥ እየከተቱ መሆናቸውን መገንዘብ ተችሏል።

ፈተናው የሚሰጥበት 'ትክክለኛው ቀን' በመንግስት ሲወሰን በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ፣ በኤጀንሲው ድረ ገፅ ፣ በትምህርት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚድያ ፣ ድረ-ገጽ ፣ በትምህርት ሚኒስቴር የቴሌቪዥን ቻናልና በተለያዩ ሚዲያዎች መግለጫ የሚሰጥ በመሆኑ ብሄራዊ ፈተናውን የምትወሰዱ ተማሪዎች በተረጋጋ ስነ-ልቦና ጥናታችሁን ጠንክራችሁ በማጥናት እንድትጠበቁ እናሳስባለን።

ነሃሴ 29/2012 ዓ/ም
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ችሎት!

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ላይ ክስ ለመመስረት 15 ቀን ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች ለአቃቤ ህግ ክስ መመስረቻ 15 ቀን ሊሰጥ አይገባም ያሉ ሲሆን ፥ ለደንበኞቻቸው የዋስትና ጥያቄ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱም አቃቤ ህግ በጠየቀው የ15 ቀን ክስ መመስረቻ እና የተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄን መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት ለጳጉሜ 2 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሌላ የችሎት መረጃ ፦

የአቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል።

በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ክስ የመመስረቻ የ15 ቀን ጊዜ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።

ክስ እስከሚመሰረት ድረስም በፖሊስ ጣቢያ በእስር እንዲቆዩ ታዟል።

Via Tarik Adugna (FBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 29/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 434 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 15 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 4,639 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 289 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 90 ከአዳማ ከተማ
- 36 ከቢሾፍቱ ከተማ
- 32 ከፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
- 24 ከቡራዩ ከተማ
- 22 ከዱከም ከተማ
- 14 ከአርሲ ዞን
- 13 ከሻሸመኔ ከተማ ይገኙበታል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 235 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 45 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 18 ከመንጌ ወረዳ
- 12 ከሸርቆሌ ስደተኛ መጠለያ
- 5 ከጾሬ ስደተኛ መጠለያ

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 6,224 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 114 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 31 ከሰ/ወሎ ዞን
- 18 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 12 ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን
- 10 ከደ/ጎንደር ዞን
- 10 ከጎንደር ከተማ
- 9 ከደሴ ከተማ ይገኙበታል።

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 893 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,942 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰማንያ ሶስት (83) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot
"የወላይታ ዞን በክልል የመደረጀት ጥያቄ በህገ - መንግስት መሠረት በቅርቡ ምላሽ ያገኛል፤ የክልል አደረጃጀት ጥያቄ ያለ ህዝብ ፍላጎት በምንም ዓይነት ሁኔታ አይፈፀምም" ሲሉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር እንድሪያስ ጌታ አስታወቁ።

ዶ/ር እንድሪያስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ "አንዳንድ ተጨባጭ ባለሆኑ ወሬዎች የወላይታ ክልል ጥያቄ ተቀልብሷል፤ በሌላ አደረጃጀት ውስጥ ገብተዋል የሚባለው ከእውነታ የራቀ ነው። በየደረጃው ያለው አመራር ባጠረ ጊዜ የህዝቡ ጥያቄ እስኪመለስ ድረስ ይሰራል" ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 23,712 የላብራቶሪ ምርመራ 1,303 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ24 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 329 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 56,516 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 880 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 20,612 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 29/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,505 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ዘጠኝ (69) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት፡-

• ከስልጤ 22 ( 12 ከወራቤ ከተማ፣ 6 ላንፉሮ፣ 4 ምዕራብ አዘርነት)፣
• ከወላይታ 15 ( 9 ከቦሎሶ ሶሬ፣ 3 ከሶዶ ከተማ፣ 2 ከዳሞት ጋሌ እና 1 ከአረካ ከተማ) ፣
• ከጋሞ 11 (7 ከአርባምንጭ ዙሪያ እና 4 ከቁጫ አልፋ)
• ከቤንች ሸኮ 10 (6 ከሚዛን ከተማ፣ 3 ከደቡብ ቤንች እና 1 ከጉራፈርዳ)፣
• ከሸካ 5 (5ቱም ከማሻ ከተማ ) በኦሮሚያ ክልል ላቦራቶሪ ተመርምረው ውጤታቸው የታወቀ
• ከባስኬቶ 3 ፣
• ከቡርጂ 1 ፣
• ከየም 1፣
• ከኮንሶ 1 (ከካራት) ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ናቸው።

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 274 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Afar

በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 686 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 85 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 840 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 18 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት! በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ  ከአራተኛ እስከ 14ኛ  የተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎላቸው ነፃ መሆናቸውን የሚገልፅ ውጤት ለፍርድ…
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነሃሴ 22 ቀን በነበረ ችሎት ሸምሰዲን ጠሃ ያጋጠማቸውን የጆሮ ህመም በመረጡት የህክምና ተቋም እንዲታከሙ ማዘዙ ይታወሳል።

ተጠርጣሪው በመረጡት የህክምና ተቋም ህክምና እንዳላገኙና ፖሊስ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ዛሬ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተጠርጣሪው በመረጡት የህክምና ተቋም እንዲታከሙ እንደጠየቃቸውና እንዳማከራቸው አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው ምርጫቸውን ባለማሳወቃቸው ወደ ሌላ ሆስፒታል እንዳልወሰዳቸውም ገልጿል፡፡ ነገር ግን ጆሮአቸውን በመታመማቸው መጎዳት ስለሌለባቸው ወደ ፖሊስ ሆስፒታል በመውሰድ ህክምና እንዲያገኙ ማድረጉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ዐቃቤ ህግ ለአፈጻጸም እና ለክትትል እንዲያመች ተጠርጣሪው ህክምና የሚያገኙበትን ተቋም ለፍርድ ቤቱ እንዲያሳውቁ ጠይቋል፡፡

በዚህም ተጠርጣሪው 'በዋሽንግተን ሆስፒታል' ለመታከም በመምረጣቸው ይህንኑ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ መስጠቱን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት! የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ላይ ክስ ለመመስረት 15 ቀን ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። የተጠርጣሪ ጠበቆች ለአቃቤ ህግ ክስ መመስረቻ 15 ቀን ሊሰጥ አይገባም ያሉ ሲሆን ፥ ለደንበኞቻቸው የዋስትና ጥያቄ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም አቃቤ ህግ በጠየቀው የ15 ቀን ክስ መመስረቻ እና የተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄን መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት ለጳጉሜ 2 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ…
ተጨማሪ መረጃ ፦

በዛሬው ዕለት (ነሃሴ 29 ቀን 2012 ዓ/ም) ፍርድ ቤት የቀረቡለትን አራት አቤቱታዎች መርምሮ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

• 1ኛ ተጠርጣሪ አቶ ጃዋር መሀመድና 2ኛ ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ በእስር በሚቆዩበት ጊዜ ተቀላቅለው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

• 11ኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃምዛ ቦረና ሚዲያዎች ዘመቻ ጀምረውብናል በሚል ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ማንኛውም መገናኛ ብዙሃን ተጠርጣሪዎቹ ነፃ ሆነው የመገመት መብታቸውን እንዳይጥሱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

• ከዚህ ቀደም ተጠርጣሪዎች ከእምነት አባቶች ጋር ለ40 ደቂቃ እንዲገናኙ ያስተላለፈው ትዕዛዝ በጥብቅ እንዲፈጸም አሳስቧል፡፡

• ከሶስተኛ እስከ ዘጠነኛ ድረስ ያሉ ተጠርጣሪዎች የታሰርንበት ቦታ መጸዳጃ ቤት አጠገብ በመሆኑ ይስተካከልልን ብለው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ካሉበት ቦታ እንዲዘዋወሩ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለ4 እና 5 ዓመታት ሲያስተማራቸው የነበሩ አራት (4) የአፋን ኦሮሞ የ3ተኛ ዲግሪ / ዶክትሬት ተማሪዎችን ባለፈው ሳምንት አስመርቋል።

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀሰን ዩሱፍ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው 4 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን በአፋን ኦሮሞ በማቅረብ ታሪክ ሰሩ ሲሉ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

Via VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕ/ር ሳሙኤል ሳህሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሳህሌ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ከወጣትነታቸው ጀምሮ በአስተማሪነት እንዲሁም በተመራማሪነት አገልግለዋል፡፡ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐሴ 30/2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ስድስት (6) የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት የትራምፕ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ከሚያደርገው ድጋፍ ውስጥ 130 ሚልዮን ዶላር መቁረጡን ተቃውመው ደብዳቤ ፅፈዋል!

ለአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ማይክ ፖምፔዎ የተፃፈ ደብዳቤ "የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ ነው ፣ በኢትዮጵያውያን የገንዘብ አስተዋፅኦ እየተገነባ ያለ ነው።

በዚህ ወቅት የገንዘብ ድጋፍ ለማቋረጥ መወሰን የአሜሪካ መንግስት በግልፅ ለአንድ ወገን እንዳደላ መገለጫ ነው" ይላል።

Via Elias Meseret (Associated Press)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዝግ እየመከረ ነው!

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ በተመለከተ የምክር ቤቱ የህገ ምንግስት ትርጉም እና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ እየመከረ ነው።

MORE : https://telegra.ph/FANA-09-05

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia