TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈው ነርስ!

በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ በነርስነት እያገለገሉ የነበሩት አንበሳአውድም ዮሃንስ በትናንትናው ዕለት (ሀሙስ ነሃሴ 28/2012) በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል።

ነርስ አንበሳአውድም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህዝቡን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል። ነርሱ የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ በትናንትናው ዕለት ህይወታቸው ማለፉ ሆስፒታሉ አሳውቋል።

ምንጭ፦ ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌደሬሽን ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አስቻኳይ ስብሰባ ነሐሴ 30/2ዐ12 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

የፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም በፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በነገው ዕለት የሚካሄደው የፌደሬሽን ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ አጀንዳው ካልታወቀ የትግራይ ክልል ተወካዮች እንደማይገኙ የክልሉ ም/ቤት ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል መንግስት ካቢኔ መግለጫ!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የትግራይ ክልል የሚያካሂደውን ምርጫ ለማደናቀፍ ውሳኔ የሚያስተላልፍ ከሆነ የጦርነት አዋጅ እንደማወጅ መሆኑን ተገንዝቦ ከዚህ የጥፋት ድርጊቱ እንዲቆጠብ የትግራይ ክልል መንግስት ካቢኔ ትላንት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

የትግራይ ክልል መንግስት ካቢኔ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የትግራይ ክልላዊ ምርጫ በህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ የሚካሄደ እስከሆነ ድረስ የማንም ጣልቃገብነትና ጫና ለደቂቃዎችም ቢሆን ሊያስቆመው አይችልም ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በውሃን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ተመለሱ!

የዉሀን ከተማ ከሰባት ወራት በኋላ ትምህርት ቤቶች ዳግም ተከፍተው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ተመልሰዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙት ከ2,800 በላይ የትምህርት ተቋማት 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ያህል ተማሪዎችን ተቀብለው ትምህርት ጀምረዋል።

የኮሮና ወረርሽኝ መነሻ በምትባለው ዉሀን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ቢጀምሩም ወላጆችና መምህራን ግን አሁንም ያላቸውን ስጋት እየገለጹ ነው።

በሌላ መረጃ፦

የዚምባብዌ መንግሥት በሚቀጥሉት ሁለት (2) ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱና በዓመቱ መጨረሻ ላይ ደግሞ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና እንደሚቀመጡ አስታወቀ።

'ካምብሪጅ' ለሚባለው ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች በፈረንጆቹ መስከረም 14 ወደ ትምህርት ቤት ይመለሳሉ ተብሏል።

ለዚምባብዌ ትምሀርት ቤት ፈተናዎች የሚቀመጡ ተማሪዎች ደግሞ መስከረም 18 ትምህርታቸው የሚጀምሩ ሲሆን ፈተናውን ደግሞ ታህሳስ ወር ላይ እንደሚወስዱ ተጠቁሟል።

መንግሥት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ከትምህርት ኃለፊዎችና የጤና ባለስልጣናት ጋር ምክክር ካደረገ በኋላ መሆኑም ተገልጿል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ እና ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቡሬ ኢንደስትሪ ፓርክ ስራ የጀመረው ሪችላንድ የመጀመሪያውን ዙር የአኩሪ አተር ዱቄት ምርት ለኤክስፓርት አዘጋጀ።

በየቀኑ አራት መቶ ቶን ኤክስፖርት ያደርጋል $200,000 እንደሚያስገኝ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል። የሀይልና የጥሬ እቃ አቅርቦቱ ልዩ ድጋፍ እንደሚጠይቅም አቶ መላኩ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጳጉሜ 3 ተማሪዎቹን ያስመርቃል!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ትምህርት ዘመን በመደበኛ የድህረ ምረቃ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብር በቅድመ ምረቃ ያስተማራቸውን 938 ተማሪዎችን ጷጉሜ 03/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በኦንላይ (Online) እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

ፖሊስ በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ አለኝ የሚለውን መረጃ ለጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም እንዲያቀርብ የመጨረሻ ቀጠሮ ተሰጥቶታል።

ፖሊስ ለዛሬ ነሃሴ 29/2012 ዓ/ም በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ አለኝ የሚለውን መረጃ እንዲያቀርብ ቀጠሮ ተሰጥቶት የነበር ቢሆንም ሳያቀርብ ቀርቷል።

በዛሬው ችሎት ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን የተከሳሾች ጠበቃ ፖሊስ በተደጋጋሚ እያስቀጠረ መረጃ ማቅረብ አለመቻሉን ጠቅሰው ተቃውመዋል።

ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ለጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም አለኝ የሚለውን መረጃ እንዲያቀርብ ተጨማሪ ሶስት (3) ቀን ሰጥቶታል።

ምንጭ፦ አስራት ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እነአርቲስት ታረቀኝ ሙሉ እስካሁን ከእስር አልተፈቱም ሲሉ ጠበቃቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል!

እነኪዳኔ ዘካርያስ በተጠረጠሩበት ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል ምስክሮች ቃላቸዉን እንዲቀይሩ ሲያባብሉ ነበር ተብለው በቀጥጥር ስር የዋሉት አርቲስት ታረቀኝ ሙሉ እና ጠበቃ ደስታ መስፍን በዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ቢያዝም ፓሊስ እንዳልፈታቸው ጠበቃቸው ለቲክቫህ አሳውቀዋል።

ጠበቃቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦

- ነሃሴ 25/2012 እና ነሃሴ 26/2012 በዋስትና ጉዳይ ሰፊ ክርክር ተደርጎ ዳኛው ጊዜ ያስፈልገኛል በሚል ሁለት ቀን ወስዶ ትላንት ብይን ተሰጥቷል፤ የዋስትና መብታቸው በህጉ የሚያስከለክል አይደለም ጠበቆችም ያነሱት የህግ መሰረት ያለው ነው በሚል የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ፍርድ ቤት ወስኗል።

- ትላንት ለዋስትና የሚስፈልጉ ሁሉንም መስፈርቶች ተሟልቶ ካለቀ በኃላ ወደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሲኬድ አቃቤ ህጓ ይግባኝ ልትል ስለምትችል በሚል ሰበብ ፌደራል ፖሊስ ቤተሰቦችን አትገቡም ብሎ ከልክሏል።

- ትላንት 6:00 ሰዓት ፍርድ ቤት ይፈቱ ብሎ ትዕዛዝ ቢሰጥም ዛሬም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ። ፖሊስ እያደረገ ያለው ድርጊት ከህግ አግባብ ውጭ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈው ነርስ! በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ በነርስነት እያገለገሉ የነበሩት አንበሳአውድም ዮሃንስ በትናንትናው ዕለት (ሀሙስ ነሃሴ 28/2012) በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። ነርስ አንበሳአውድም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህዝቡን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል። ነርሱ የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው…
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባልደረባ የነበሩት ነርስ አምበሳአውድም ዮሃንስ የአስክሬን ሽኝት በሆስፒታሉ ሰራተኞችና የስራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

ነርስ አንበሳአውድም የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተይዘው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ በ28-12-2012 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየተዋል፡፡

ምንጭ፦ ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር ደበላ ሁንዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

ፕሮፌሰር ደበላ ሁንዴ በብዝኃ ሕይወት ጥበቃ እና አስተዳደር መስክ በርካታ የጥናት እና የምርምር ስራዎችን በመስራት ይታወቁ ነበር።

ፕሮፌሰር ሁንዴ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ፣ በተመራማሪነት እንዲሁም በኮሌጅ አመራርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ፕሮፌሰሩ ሰባት የከፍተኛ ትምህርት የመማርያ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች የቀረቡ የምርምር ስራዎችን ሰርተዋል።

በተጨማሪም ከሃምሳ (50) በላይ ጥናታዊ ጽሁፎችን በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ መድረኮች አቅርበው ዕውቅና ተሰጥቷቿዋል፤ ለህትመትም በቅተዋል።

ፕሮፌሰሩ ህይወታቸው እስካለፈበት ድረስ በነበረ ያለፈውን አንድ አመት በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ማዕከል ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ፕሮፌሰር ደበላ ሁንዴ ፈይሳ ባደረባቸው ህመም ሆስፒታል ገብተው ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ቢሆንም ትናንት ምሽት በተወለዱ በ59 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ/ጅማ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በነገው ዕለት የሚካሄደው የፌደሬሽን ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ አጀንዳው ካልታወቀ የትግራይ ክልል ተወካዮች እንደማይገኙ የክልሉ ም/ቤት ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የፌደሬሽን ምክር ቤት ለነገ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የስብሰባው አጀንዳ ምን እንደሆነ በደብዳቤ የጠየቀው ምክር ቤቱ ከፌደሬሽን ምክር ቤት የተሰጠ ምላሽ ባለመኖሩ የትግራይ ተወካይ የፌደሬሽኑ የምክር ቤት አባላት በነገው ስብሰባ እንዳይሳተፉ በሙሉ ድምፅ መወሰኑ ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia