TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ይህ የተለየ የቪፒኤን አይነት ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም በሞባይል ቪ.ፒ.ኤን (VPN) ጥቅል አገልግሎቱ ላይ የዋጋ ማሻሻያ በማድረግ እንዲሁም ያለተገደበ አማራጭን አካቶ ማቅረቡን ገለፀ።

ድርጅቱ ፤ በቪ.ፒ.ኤን (VPN) አገልግሎቱ ደህንነቱ በተጠበቀ የዳታ አገልግሎት #የድርጅት አገልግሎት ማሳለጥ፣ #ቢሮዎችን እርስበእርስ ማገናኘት እንዲሁም በየትኛውም ቦታ የድርጅት መረጃ እና መሳሪያዎች በመጠቀም ቢዝነስ ማከናወን የሚያስችል ነው ብሏል።

ደንበኞቹ ፤ አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያቸው የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎችን መጎብኘት እንደሚችሉ ጠቁሟል።

ነገር ግን ድርጅቱ የዋጋ ማሻሻያውን በሚመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቹ ያሰራጨው መረጃ በርካቶችን ጋር ያጋባና " VPN ምንድነው ? " ብለው እንዲጠይቁ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ወራትን ካስቆጠረው የማህበራዊ ሚዲያዎች #ገደብ ጋር የሚገናኝ የመሰላቸውም ብዙ ናቸው።

ለመሆኑ ቪ.ፒ.ኤን (VPN) ምንድነው ?

(ኢትዮ ቴሌኮም)

ቪ.ፒኤ.ን (VPN) ማለት የግል እና የመንግስት ተቋማት ከተለያዩ ቅርንጫፎቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ነው።

ተቋማቱ የራሳቸውን የግል ኔትወርክ እንዲያደራጁ ያስችላቸዋል፤ መረጃን ለማጋራት እንዲሁም በቅርንጫፎች ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓቶችን በመደበኛ ወይም በተንቀሻቃሽ አማራጮች መተግበር ያስችላል።

አገልግሎቱ የሞባይል ኔትዎርክ ሽፋን ተደራሽ በሆነባቸው እና የዳታ አገልግሎትን በሚሰጡ በሁሉም ኢትዮጵያ ክፍሎች ይገኛል።

ኢትዮ-ቴሌኮም የቪፒኤን አገልግሎቶች በሁለት አማራጭ የሚያቀርብ ሲሆን እነዚህም " የሞባይል ብሮድባንድ ቪፒኤን " እና " የፊክስድ ብሮድባንድ ቪፒኤን " ናቸዉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ " ይህ የተለየ የቪፒኤን አይነት ነው። " ያለ ሲሆን " የተንቀሳቃሽ ስልክ ኔትዎርክ ሽፋን ባለባቸው አካባቢዎች ነገርግን ግን መደበኛ ባለገመድ መስመር ተደራሽነት ባሌለባቸው አካባቢዎች ልክ እንደ #ባንክ ያሉ የድርጅት ደንበኞች ቅርንጫፎቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማገናኘት የሚረዳ የግል መዳረሻ አውታር ሆኖ እንደ አማራጭ የቀረበ ነው።  " ሲል አስረድቷል

የሞባይል ቪፒኤን / VPN / ጥቅል ዋጋ ማሻሻያ የሚመለከተውም ይሄን ነው ብሏል።

Credit : #EthioTelecom

@tikvahethiopia