TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013

በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሰንገን ኦባሳንጆ የሚመራው በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የምርጫ ትዝብቱን #የመጀመሪያ ሪፖርት ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ያቀርባል።

ሪፖርቱን #በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat መከታተል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
Audio
AudioLab
#ምርጫ2013

ምርጫውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ሕብረት ለምርጫ (CECOE) ተጠባባቂ ዳይሬክተር አበራ ኃይለማርያም የሰጡን አጭር ገለፃ።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በዘንድሮ ምርጫ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ተሳትፎ ምን ይመስላል ?

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ተሳትፎና የሚዲያዎች ሚና ምን እንደሚመስል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማህበር ሥራ አስፈጻሚዎች ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በቀጥታ በVoice Chat አጭር ገለፃ ያደርጋሉ።

ገለፃ የሚያደርጉት ፡
- ጋዜጠኛ ሲሳይ ሳህሉ
- ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ
- ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ናቸው።

(ከምሽት 2:10 - 2:40 ድረስ)

@tikvahethiopia
Audio
AudioLab
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማህበር ሥራ አስፈጻሚዎች በ #ምርጫ2013 የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ተሳትፎና የሚዲያዎች ሚና ላይ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሰጡት ገለፃ።

- ጋዜጠኛ ሲሳይ ሳህሉ
- ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ
- ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት

@tikvahethiopia
Audio
AudioLab
#ምርጫ2013

በምርጫ ወቅት የምንጠቀማቸው ቃላቶች ፦

በአሁን ወቅት በተደጋጋሚ ለሚነሱት የምርጫ ቃላቶች ማብራሪያ እንዲሰጡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስን ጋብዘናል።

ማብራሪያ የተሰጠባቸው ቃላቶች፦

- ኳራንታይን
- ውጤት ማጣራትና ማረጋገጥ

በተጨማሪም ወ/ሪት ሶልያናን ስለ ቅሬታ አቀራረብ እና ውጤት ስረዛ ጥያቄ አቅርበንላቸዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና የሰጡትን ምላሽ ከላይ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

#TikvahFamily #ምርጫ2013

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ኳራንቲን የተደረጉ /በምርመራ ላይ ያሉ ጣቢያዎች ስንት ናቸው ?

በአዲስ አበባ የመጫረሻ #ኳራንቲን ፣ ምንም የማይደረግበት ወይም ደግሞ ወደውጤት ቋት ውስጥ የማይገባ በሚል የተያዙ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አሳውቀዋል።

አንደኛው በምርጫ ክልል 24 ያለ ሲሆን ሌላኛው በንፋስ ስልክ ያለ ነው።

ከዛ ውጭ እንደገና በመቁጠር እና ሰነዶችን እንደገና በማየት የሚስተካከሉ ሊኖሩ ይችላሉ።

NB : በምርጫው ሂደት "ኳራንቲን ማድረግ" ማለት ከዋናዎቹ ውጤቶች ጋር ሳይቀላቀል ማግለል ወይም ደግሞ መለየት እና በልዩ ሁኔታ ማጣራት ማለት ነው።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ኢትዮጵያ በ2 ዙር የምታደርገው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቃ የውጤት ይፋ መሆን እየተጠበቀ ነው።

ምርጫው ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያለው ዜጋ የተሳተፈበት መሆኑ መግለፁ ይታወሳል።

ዛሬ አውሮፓ ህብረት ፣ እንግሊዝና ጀርመን፣ ጃፓንን ጨምሮ 12 ሀገራት ምርጫውን አስመልክቶ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

ምርጫውን ተዓማኒ ለማድረግ የተሻሻሉ ሕችን ማውጣትን ጨምሮ ምርጫ ቦርድ የወሰዳቸውን ርምጃዎች አድንቀዋል፡፡

ሲቪል ማኅበራት በምርጫው ሂደት ያሳዩት ጉልህ ተሳትፎ አመርቂ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ሆኖም ግን ፥ አንዳንድ ተቃዋሚዎች በታሰሩበት ፣ የፖለቲካ ምኅዳሩ በተገደበበት፣ ጋዜጠኞች በሚዋከቡበት፣ የጸጥታ ችግር ባለበትና ፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት ምርጫ ዘመቻ ለማድረግ በተቸገሩበት ሁኔታ ውስጥ ምርጫው መካሄዱን የገለጡት ሀገራቱ፣ የሀገሪቱን ችግሮች ለመቅረፍ ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ ንግግር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

አሜሪካም ከኢትዮጵያ ምርጫ ጋር በተያያዘ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል መግለጫ አውጥታለች።

አሜሪካ ምርጫው በአለመረጋጋትና ግጭት ውስጥ የተካሄደ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነጻ እና ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ነው ብላለች።

አንዳንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መታሰራቸው እና ሌሎችም ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ መግባባት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ብላለች።

በድኅረ-ምርጫ ለፖለቲካዊ ንግግር፣ ግጭቶችን ለመፍታትና ለብሄራዊ ዕርቅ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ ብላለች። የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡና ተኩስ እንዲቆም ድጋሚ ጠይቃለች። #Wezema

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ምርጫ ከተደረገባቸው 440 ምርጫ ክልሎች ውስጥ 221 የሚሆኑ የምርጫ ክልሎች ውጤቶቻቸውን መለጠፋቸውን ወይዘሪት ሶሊያና አሳውቀዋል።

ከምርጫ ክልሎቹ መካከል ከ50 % በላይ የሚሆኑት ናቸው ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶቻቸውን የለጠፉት።

በአማራ ክልል 40 የምርጫ ክልሎች ውጤት የለጠፉ ሲሆን በኦሮሚያ 125 የምርጫ ክልሎች ውጤት ለጥፈዋል ተብሏል።

አዲስ አበባ ከተማ ባሉ 10 የምርጫ ክልሎች ውጤት አሳውቀዋል፤ በከተማ ያሉ ሌሎች የምርጫ ክልሎች ቆጠራ አለመጠናቀቁ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፦ በደቡብ ክልል በቁጫ የምርጫ ክልል ሲካሄድ የነበረው ቆጠራ እንዲቆም ተወስኗል።

ቆጠራው እንዲቆም የተወሰነው በነበረው ተገቢ ያልሆነ አሰራር እና የጸጥታ ችግር ምክንያት እንደሆነ ወ/ሪት ሶልያና ሽመልስ ገልጸዋል።

ቦርሩ በቁጫ የምርጫ ክልል በሂደቱ ላይ ተገቢ ያልሆኑ አሰራሮች እንደነበሩ ቅሬታዎች ለቦርዱ ሲቀበል የነበረ ሲሆን ጉዳዩ እስኪጣራ ቆጠራ እንዲቆም ተወስኗል።

በምርጫ ክልሉ ሲቀርቡ ከነበሩት ቅሬታዎች በተጨማኢ የጸጥታ ችግር እንዳለ ቦርዱ መረጃ ስለደረሰው ቆጠራው ቆሞ የምርጫ ቁሳቁሶች ባለበት ታሽጎ እንዲቀመጥ ወስኗል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በድሬደዋ በ6 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ችግር እንዳጋጠመው ቦርዱ ገለጸ።

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ስድስት የምርጫ ጣቢያዎች የክልል ምክር ቤት ምርጫ ሳይካሄድ እንደቀረ እንዲሁም ከስድስቱ በአንዱ ጣቢያ የህዝብ ተወካዮች ምርጫ ጭምር ሳይካሄድ መቅረቱን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ገልጿል።

ሪፖርቱ አሁን እንደደረሳቸው የገለጹት የቦርዱ የኮሚውኒኬሽን አማካሪ ሶልያና ሽመልስ ''የክልል ምክር ቤት የድምጽ መስጫ ወረቀት አልደረሰንም'' በሚል ምርጫው ሳይካሄድ እንደቀረ የምርጫ ክልሉ ኃላፊ መግለጹን የጠቆሙ ሲሆን ይህንን ግን አስቀድመው ሪፖርት አለማድረጋቸውን ነው ያነሱት።

በእነዚህ ጣቢያዎች ላይ ምን ይሆናል የሚለውን ቦርዱ መመልከቱን አንስተው ''እነዚህ ጣቢያዎች ላይ አንድ ፖርቲ ብቻ ነው የሚወዳደረው። የአንድ ፖርቲ ውድድር ስለሆኑ በክልል ምክር ቤት ደረጃ የሚኖረውን ውጤት አይቀይሩትም ስለዚህ ምንም አይነት ተጨማሪ ምርጫ ማድረግ አያስፈልግም ብሎ ቦርዱ ወስኗል'' ብለዋል።

ከስድስቱ አንዱ ጣቢያ ላይ ከክልል ተወካዮች ምክር ቤት በተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም አለመካሄዱን ያነሱት ወ/ሪት ሶልያና ''...በአጠቃላይ የተወካዮች ምክር ቤት ውጤት ታይቶ ውጤቱን የሚቀይር ከሆነ ተጨማሪ ውሳኔ ቦርዱ የሚወስን ይሆናል።'' ሲሉ ገልጸዋል።

6ቱ ጣቢያዎች ከዚህ ቀደም የመራጮች ምዝገባ በትክክል ያልተካሄደባቸው ተብለው የተለዩ እንደሆኑ ያስታወሱት ወ/ሪት ሶሊያና ለዚህ ችግር መፈጠር ኃላፊነት የሚወስደው አካል የቱ ነው የሚለውን እያጣሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013_እና_አዲስአበባ

ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ምርጫ ሂደት ላይ በፓርቲዎች (በተለይ ደግሞ በባልደራስ ፓርቲ) ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች እና አቤቱታዎች በተወሰኑት ላይ ምላሽ ሰጥቷል።

ለቅሬታዎቹ እና አቤቱታዎቹ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ናቸው።

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በየምርጫ ጣቢያው በተለጠፈው የውጤት መግለጫ ወረቀት ላይ ተሰረዟል/ተደልዟል ስለሚባለው ጉዳይ ?

ወ/ሪት ሶሊያና : ምርመራ አድርገናል ፤ የየምርጫ ክልል ኃላፊዎች ስርዝ ድልዝ ተደረገበት የተባለውን ጣቢያ ተመልከትው ችግር ይኑርበት አይኑርበት የሚለውን ድጋሚ ቆጥረው እያረጋገጡልን ነው፤ የውጤት ማሳወቅ ሂደት ላይ ስርዝ ድልዝ መኖሩ ነው እንጂ ችግር ያለበት አልተገኘም፤ በቆጠራው ላይ ያለው እና የተፃፈው ቁጥር ትክልል ነው የሚል ሪፖርት ደርሶናል።

የምርጫ ቆጠራው ችግር አለበት ስለሚባለው ጉዳይ ? (ባልደራስ ፓርቲ ያቀረበው ቅሬታ)

ወ/ሪት ሶሊያና : በአዲስ አበባ አብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሁሉም ፓርቲ ወኪሎች ተገኝተው ነው ቆጠራ የተደረገው ፤ አ/አ ላይ የፓርቲ ወኪል ለምርጫ ጣቢያ ልኮ የምርጫ ጣቢያ አልቀበልም ያለበት ምንም አይነት ምርጫ ጣቢያ የለንም ፤ ሁሉም ቦታዎች የፓርቲ ወኪሎች ተገኝተዋል ፤ እራሳቸው ወኪሎቻቸውን እስከላኩና አቅማቸው ፈቅዶ ከ1 ሺህ በላይ ጣቢያዎች ላይ እስካስቀመጡ ድረስ። ወኪሎቹ የምርጫ ሂደቱ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ተከታትለው ውጤቱ ላይ ፈርመዋል ሁሉም ቦታዎች ላይ ማለት ይቻላል። ወኪሎች ያሉባቸው ፊርማዎች ኖረውን ነው የመጣነው የምርጫ ሂደቱን ስናደርግ።

ይቀጥላል👇