TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ተመረጡ። የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሊዝ ትረስ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል። ትረስ እድሜያቸው 47 ሲሆን የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ሆነዋል። ሶስተኛዋ የሀገሪቱ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትርም እንደሆኑ ተገልጿል። ትረስ ተፎካካሪያቸው የነበሩት ሪሺ ሱናክን ሲሆኑ ያሸነፉት 57.4% ድምፅ በማግኘት እንደሆነ ዶቼ ቨለ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#UK #China
ሪሺ ሱናክ የዩናይትድ ኪንግደም ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው።
ሊዝ ትረስ በተሾሙ በሰባት ሳምንት ስልጣን በቃኝ ያሉ ሲሆን እሳቸውን ለመተካት በተደረገው ውድድር ሪሺ ሱናክ አሸናፊ ሆነዋል።
ሱናክ ፤ የዩናይትድ ኪንግደም #የመጀመሪያው " እስያዊ " ዝርያ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ።
ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ከሰባት ሳምንታት በፊት በተደረገ ፉክክር ሪሺ ሱናክ ተወዳድረው የነበረ ቢሆንም በሊዝ ትረስ ሊሸነፉ ችለዋል።
ሊዝ ትረስ ' ግብር እቀንሳለሁ፤ ንግድን አሳልጣለሁ " ያሉት አዲስ ፖሊሲ ፍጹም ያልተጠበቀ የገበያ ምስቅልቅልና ብሔራዊ ጦስ ይዞባቸው መጥቶ ነው ሥልጣን እንዲለቁ የሆኑት።
ለ45 ቀናት ያህል ስልጣን ላይ የቆዩት ሊዝ ትረስ በዩናይትድ ኪንግደም ታሪክ ለአጭር ጊዜ የቆዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመዝግበዋል።
በሌላ መረጃ ፥ የቻይና ገዥ የሆነው ኮሚኒስት ፓርቲ ትላንት ባደረገው ጉባኤ ዢ ዢንፒንግን ዋና ጸሓፊ አድርጎ መምረጡን ተከትሎ ለ3ኛ ጊዜ ስልጣናቸው ተራዝሟል።
የፓርቲው #ዋና_ጸሃፊ በሃገሪቱ የመሪነት ቦታ የሚያስገኝ ሲሆን መጋቢት በሚደረገው የብሄራዊ ህዝቦች ጉባኤ በይፋ ስልጣናቸው ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ አስነብቧል።
@tikvahethiopia