TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትኩረት📣

በሲዳማ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ዳግም የፀጥታ ችግር እና ግጭት ማገርሸቱን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከበንሳ ጠቁመዋል።

የዳዬ አጠቃላይ ሆስፒታል የቲክቫህ አባላት በሲዳማ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በአካባቢዎች ላይ ባገረሸው ግጭት #የሰዎች_ህይወት_ማለፉን እና ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ገልፀዋል።

ችግሩ ይፈታ ዘንድና አሁን ካለው ሁኔታ ይበልጥ እንዳይከፋ እንዲሁም አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ በሚመለከተው አካል ሁሉ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ አስገዝበዋል።

ሌሎች መልዕክታቸውን የላኩ ነዋሪዎችም ፤ የሚታየው ነገር በአካባቢው ላይ ያለን መልካም ግንኙነት በእጅጉ የሚያደፈርስ በመሆኑ ከሁለቱም ክልል የሚመለከተው አካል የህዝቡን ደህንነት እንዲያስጠብቅና ግጭቱን እንዲቆም መፍትሄ እንዲፈለግ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትም ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የራሱን ድርሻ እንዲጫወት ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

ፎቶ ፦ ከዳዬ አጠቃላይ ሆስፒታል ቲክቫህ አባላት

#ትኩረት

@tikvahethiopia
#ትኩረት_የሚሻ_የፀጥታ_ጉዳይ 📣

በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ እና በአፋር ተላላክ ወረዳ በአንድ ግለሰብ ሞት ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ወደ ተኩስ ልውውጥ ተቀይሮ ለሰዎች ሞት እና መቁሰል ምክንያት ሆኗል።

አሁን ያለው የፀጥታ እጅግ ልዩ ትኩረት የሚፈልግ ነው ተብሏል።

ችግሩ የተከሰተው ባለፈው ማክሰኞ ዕለት ሲሆን አንድ የአፋር ተወላጅ አርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ መድና ከተማ ገበያ ውሎ ሲመለስ መሃል መንገድ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከተገደለ በኃላ ነው።

ባለፉት ተከታታይ ቀናት መዲናን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች ላይ የተኩስ እሩምታ የሚሰማ ሲሆን የግለሰብ ቤቶችም መቃጠል መጃመራቸው ተነግሯል። እስካሁን ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ማወቅ አልተቻለም።

ችግሩን ለመፍታት በአፋርም አማራ ክልል በኩልም ብዙ ቢጣርም ውጤት አላመጣም ይልቅም እየባሰ ሄዷል።

በርካቶች ባለው የፀጥታ ችግር ከቄያቸው እየሸሹ መሆናቸውም ተነግሯል።

የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሰኢድ ኢብራሂም አሁን ያለው ሁኔታ ከግለሰብም አልፎ መልኩን ቀይሮ እጅግ አሰቃቂ የሆነና መጥፎ ጉዳት ሊያደርስ በሚችልበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው የክልሉ መንግስት እና የፌዴራል መንግስት መኃል ገብተው ካላስቆመው ቀጠናው በጣም አስጊ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

ከአፋር ክልል ተላላክ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት እና የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት በኩል ለቪኦኤ ሬድዮ የሰጡት ቃሎች በዚህ ተያይዟል ያንብቡ ⬇️

https://telegra.ph/Attention-06-04-2

#አርጎባ_ብሄረሰብ_ልዩ_ወረዳ #ተላላክ_ወረዳ

#ቪኦኤ

@tikvahethiopia
#ትኩረት📣

ነዋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለው የፀጥታ ችግር !

ከቲክቫህ ቤተሰብ አባል ከአጣዬ አካባቢ ፦

" እንደ ሁል ጊዜው ሁሉ አጣዬ ከተማ ዳግም ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ውስጥ ገብታለች።

ይሄም የሆነው በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ ቦታዎች ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ ነው።

ትላንት ማለትም በ02/11/2014 " የቤት እንሰሶች የተዘራ ሰብልን በሉብን " በማለት ልዩ ቦታው አርሶ አምባ የሚባል ስፍራ ፀብ የተነሳ ሲሆን አሁን ላይ አድማሱ ሰፍቶ በተለያየ አቅጣጫ ከባባድ ውጊያዎች ተከፍተዋል።

የተለያዩ የፀጥታ አካላትም ጉዳት ደርሶባቸው በአጣዬ ሆስፒታል ሲገቡም ተመልክተናል።

ቦታዎቹ ላይ ልዩ ሀይል እና ፌደራል ፖሊስ ያለ ቢሆንም እጅግ ብዙ ቁጥር ያለው ሀይል ነው ጥቃቱን እየሰነዘረ የሚገኘው።

ስለሆነም ለማብረድ እንደተቸገሩ እየተሰማ ነው የሚገኘው።

ከከሰአት ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚወስደው መንገድም እንደተዘጋ እና ከወትሮው በተለየ መልኩ የመኪኖች እንቅስቃሴ ቀንሷል።

የፌደራል መንግሥቱ እና የሚመለከታቸው አካላት ይሄንን ነገር አሁን ካለበት ሳይባባስ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል። "

በአካባቢው ግጭት መቀስቀሡን የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ለአል አይን ኒውስ ያረጋገጡ ሲሆን ግጭቱ ሳይባባስ ለማስቆም ተጨማሪ ሀይል ወደ ስፍራው ተልኳል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopia
#ትኩረት

ከማለዳው አንስቶ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ የፀጥታ ችግር መኖሩንና ንፁሃን ሰዎች ላይ በታጣቂዎች ጥቃት መከፈቱን ነዋሪዎች እየገለፁ ይገኛሉ።

እስካሁን ባለው ሁኔታ በቁጥር ያልተለዩ ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የገለፁት ነዋሪዎች አካባቢው አሁንም ባለመረጋጋቱ ተጨማሪ ጥፋት ስለሚደርስ የመንግስት የፀጥታ ኃይል ወደ ስፍራው ገብቶ እንዲያረጋጋ ተማፅነዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የጦርነት ሁኔታ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ያለውን ህዝብ ደህንነት እንዲዘነጋ ማድረጉን ፤ ሚዲያዎችም ችላ እንዲሉት እያደረገ መሆኑን በአካባቢው ቤተሰቦቻቸው ያሉ አባላት ገልፀዋል።

@tikvahethiopia @OfficialtikvahethiopiaBoT
#ትኩረት

የመተሐራ ቲክቫህ ቤተሰቦች በሚኖሩበት የመተሀራ አካባቢ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባ በላኳቸው መልዕክቶች አስገንዝበዋል።

ከዚህ ቀደም ወደ መተሀራ አካባቢ በርካታ ወጣቶች በመዝናኛ ቦታ እያሉ መገደላቸው በሚዲያዎችም ጭምር መገለፁ ይታወሳል።

እዛው " መተሐራ " አካባቢ ከአምስት ቀናቶች በፊት አንድ የቀበሌ ሊቀመንበር ተገድሎ ነበር ፤ ከዚህ ግድያ በኃላም የአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የመተሐራ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

ከሚፈፀሙ ግድያዎች በተጨማሪ ደግሞ ታጣቂዎች ሰዎችን በማገት ከፍተኛ ገንዘብ (እስከ 2 ሚሊዮን ብር) ድረስ የመጠየቅ እንቅስቃሴ እየተበራከተ በመሆኑ ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነውና ከመቼውም በላይ ልዩ ትኩረት ይፈጋል ሲሉ አስገዝበዋል።

በተጨማሪ ከአዳማ ከ50 እስከ 100 ኪ/ሜ ባለው ርቀት ውስጥ ባሉት አቦምሳ / አፐር አዋሽ አካባቢም ትኩረትን እንደሚሻ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ፤ አንድ የቅርብ ቤተሰቡ በታጣቂዎች የተገደሉበት የቤተሰባችን አባልም በተመሳሳይ መልዕክት በመላክ የአካባቢው ደህንነት ልዩ ትኩረት እንደሚሻ አስገንዝቧል።

ከአዳማ ወደ መተሀራ በሚወስደው መንገድ ላይ " ኑራሄራ " አካባቢ የሰዎች ግድያ እና እገታ እንዳለ የገለፀው ቤተሰባችን ከቀናት በፊት ዘመዱ መገደሉን አመልክቷል።

" የእናቴ አጎት ነው ለባለቤቱ ደውለው መጀመሪያ ብር አምጪ ነው የተባለችው። ብር ማምጣት አንችልም አለች ፤ ከዘመድም ቢሆን ጠይቂና አምጪ አሏት ፤ ብር ሊሰጥ የሚችል ዘመድ የለም የራሳችሁን የምትወስኑትን ውሳኔ ወስኑ ስትል ነው የመቱት " ሲል አስረድቷል።

" እኔም ለለቅሶ ወደዛ ሄጄ ነበር " ያለው ቤተሰባችን በአካባቢው የሚሰማው ሁሉ የደህንነት ስሜትን የሚነሳ ነው እና በተለይ ፌዴራል መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የአካባቢውን ድህንነት ማረጋገጥና አጥፊዎችን መቆጣጠር አለበት ሲል አጥብቆ አስገንዝቧል።

በተጨማሪም ይኸው ቤተሰባችን በቦሌ ወደ አዳማ በሶደሬ በኩል በሚወስደው መንገድ ቦፋ እና አውራ ጎዳና በሚባለው ቦታ የህዝብ ተሽከርካሪ ሳይቀር የማገት ድርጊት ተፈፅሞም እንደነበር በመጠቆም አጠቃላይ ለደህንነት ስጋት በሆኑ ቦታዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ መንግስት የተጠናከረ ስራ እንዲሰራ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የፀጥታ_ጉዳይ " የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባልን አመልክተናል " - አቶ ውብሸት አበራ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ተኩስ እንደከፈቱ ተሰምቷል። ለአል ዓይን ኒውስ የደራ ወረዳ፤ ጉንዶ መስቀል ከተማ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ፤ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው የኦነግ ሸኔ ቡድን ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ ዘልቀው በመግባት ከባድ…
#ትኩረት

በሰሜን ሸዋ ፤ ደራ ወረዳ ያለው ሁኔታ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያስፈልገው በወረዳው ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት አመልክተዋል።

" ንፁሃን በጭንቀት ውስጥ ነው ያሉት " ሲሉ የገለፁት የቤተሰብ አባላቶቻችን ዛሬ በጉንዶ መስቀል ከተማ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ እሩምታ ሲሰማ እንደነበር እና ነዋሪውም #ለደህንነቱ_በመስጋት በየቤቱ ተቀምጦ እንደነበር ተናግረዋል።

በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን አመልክተው አፋጣኝ እንዲሁም አስተማማኝ መፍትሄ እንዲፈልግ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ውብሸት አበራ ዛሬ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል ፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ደራ ወረዳ ዋና ከተማ ጉንዶ መስቀል መግባታቸውን ገልፀዋል።

ከጠዋት ጀምሮ በከተማዋ ባሉ ባንኮች፣ የመንግስት ተቋማት እና የግለሰቦች ንብረት ላይ ዘረፋ ሲፈፀም እንደነበር ጠቁመው ወረዳው የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባለት ማመልከቱን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኦሮሚያ #ትኩረት

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች አሁንም በቀጠለው የፀጥታ ችግር በርካቶች ህይወታቸው እያለፈ ፣ አካላቸው እየጎደለ፣ ንብረታቸው እየወደመ እንደሚገኝ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል።

ባለፉት ዓመት ህዝቡ በሰላም እጦት ብዙ ቢሰቃይም መፍትሄ ሳይገኝ አሁንም እየተባባሰ በመቀጠሉ ንፁሃን ክፉኛ እየተጎዱ እና ስቃያቸውም እየተባባሰ እንደሚገኝ ነው ቤተሰቦቻችን የገለፁት።

ከጥቂት ቀን በፊት የፀጥታ ችግር ባለባቸው በወለጋ የተለያዩ አካባቢች ላይ #ንፁሃን እንዲጠበቁ ፣ የህዝቡ ስቃይ ትኩረት ባለማግኘቱ የሰሜን ክፍሉን ያህል ትንሽ እንኳን ትኩረት እንዲሰጠው እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግ ቤተሰቦቻችን ተማፅኖ ማሰማታቸው አይዘነጋም።

ከሰሞኑን በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙት ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርዳጋ ጃርተ ወረዳ እና በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ውስጥ በርካቶች ህይወታቸው አልፏል፣ ንብረታቸው ወድሟል ፣ #ሰላምን_ፍለጋ ሸሽተው ወደ ሌሎች አካባቢዎችም መግባታቸውን ለመስማት ችለናል።

አንድ የቤተሰባንች አባል ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ፤ " ለንፁሃን ጭፍጨፋ ፣ ለንብረት ውድመት ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ተጠናቂነት መኖር አለበት " ብሏል።

" እውነት መንግስት / አስተዳዳሪ ነኝ ፤ የህዝብንም ደህንነት አስጠብቃለሁ የሚል ካለ የትኛው አካል ለሚፈጠሩት ችግሮች ምክንያትና መንገድ እየሆነ እንዳለ ፣ ማን ግፍ እየፈፀመ እንዳለና ለዚህም ድርጊት ተባባሪ እየሆነ እንዳለ ምርመራ በማድረግ ማሳወቅ አለበት ፤ በየዕለቱ ሰዎች እየረገፉ ፣ እየተፈናቀሉ ፣ እየተራቡ እያዩ ዝም ያሉት ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ከእንቅልፋቸው ነቅተው መፍትሄ እንዲመጣ ንፁሃንን ከሞት እንዲድኑ ድምፃቸውን ማሰማት መቻል አለባቸው ። " ብሏል።

የመንግስት ዋናው ስራ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ፤ ከየትኛውም የታጠቁ አካላት የሚደርስን ጥቃት መከላከል ፣ አጥፊዎችን መቅጣት ነው ይህን ማድረግ ባይቻል እና ንፁሃን ቢጎዱ ተጠያቂነት መኖር አለበት ሲል አክሏል።

በኦሮሚያ ክልል ባለው ፀጥታ ጉዳይ ፤ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚታዩ ችግሮች መኖራቸውን ይህም በተደጋጋሚ መገለፁን ነገር ግን እስካሁን መፍትሄ እንዳልተገኘለት ገልጿል።

" ህዝብ መንግስት አለኝ ሚለው ደህንነቱ እንዲጠበቅ እንጂ በየዕለቱ ያለበት ችግር እየተባባሰ ህይወቱን እያጣ፣ እጅግ ደክሞ ያፈራው ንብረቱ እየወደመበት እንዲቀጥል አይደለም " ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል ባለፉት ጊዜያት እሱን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸው በግጭት ቀጠና ውስጥ ያሉ ወገኖች ያሳለፉት ስቃይ በቃላት የሚገለፅ እንዳልሆነ አስረድቷል።

በኦሮሚያ ውስጥ የፀጥታ ችግሮች ባለባቸው ቦታዎች ስለሚደርሰው ስቃይ ብዙ ቢነገርም መፍትሄ ሳያገኝ ዛሬም የሰዎች ህይወት እየተቀጠፈ እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል።

የአንድ ሀገር ዜጎች ህይወታቸው በግፍ እየረገፈ እየታየ ለችግሩ መፈጠር በተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ ምክንያቶች እየተደረደሩ ፣ ጥላቻዎችም እየተሰበኩ፣ ሁኔታዎችም #ከመሻሻል ይልቅ ክፉኛ እየተባባሱ ቀጥለዋል።

ህዝቡ ሰላም ርቆት፣ ኢኮኖሚው ደቆ፣ አርሶ እንዳይበላ ሆኖ፣ እየታፈነ ሚሊዮኖች እየተጠየቀበት ፣ መውጫ እና መግቢያ አጥቶ ፣ የሚወዳቸውን እየተነጠቀ፣ ዓመታትን በገፋበት የግጭት ቀጠናዎች መፍትሄ እንዲያገኝ ግፊት ማድረግ እንደሚገባ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በዚህ ሰዓት የፀጥታ ችግር መኖሩን በወረዳው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።

ያለው ሁኔታ #እጅግ_በጣም ከፍተኛ የሆነ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለው የፀጥታ ስጋት " ለነፍሳችን ሰግተናል " ያሉ ነዋሪዎች የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እና ሁኔታው እንዲረጋጋ ጠይቀዋል።

ዛሬ በወረዳው ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፤ "ሰንበቴ በአሁኑ ሰአት ጭንቅ ውስጥ ገብታለች ፤ ዱኣ ወይም ፀሎት ትፈልጋለች!! የሚመለከተው የመንግስት ባለድርሻ አካላትን ልዩ ትኩረት ትሻለች። " ሲል አንድ አጭር ፅሁፍ አሰራጭቷል።

ወረዳው ይህንን ከማለት ውጭ ስለጉዳዩ ምንም የሰጠው ዝርዝር መረጃ የለም።

በአጣዬ በኩልም ስጋት መኖሩን ቤተሰቦቻችን እየገለፁ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአካባቢው ካሉት የቤተሰብ አባላቱ ሁኔታውን ለመከታተል ጥረት ያደርጋል።

ይህ የሀገራችን ቀጠና ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግር ሲከሰትበት እና የሰዎች ህይወት ሲቀጠፍበት ፣ ንብረትም ሲወድምበት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በዚህ ሰዓት የፀጥታ ችግር መኖሩን በወረዳው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል። ያለው ሁኔታ #እጅግ_በጣም ከፍተኛ የሆነ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል። ባለው የፀጥታ ስጋት " ለነፍሳችን ሰግተናል " ያሉ ነዋሪዎች የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እና ሁኔታው እንዲረጋጋ ጠይቀዋል። ዛሬ በወረዳው ለተፈጠረው…
#ትኩረት

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር ተባብሶ ከፍተኛ ውድመት እየደረሰ ይገኛል።

በትላንትናው ዕለት በዚሁ አካባቢ ስላለው ሁኔታ ቤተሰቦቻችን መልዕክት መላካቸው አይዘናጋም።

ዛሬ ደግሞ አጣዬና ጀውሀ እንዲሁም የኤፍራታና ግድም ወረዳ ቀበሌዎች በታጠቁ ኃይሎች ዝርፊያና ውድመት ቃጠሎ እየደረሰባቸው ሲሆን የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጥ እየተጠየቀ ነው።

የሰሞኑን ሁኔታ በተመለከተ አል ዓይን ኒውስ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ ፤ የፀጥታ ችግሩ ከአራት ቀናት በፊት መከሰቱንና ተባብሶ መቀጠሉን አመልክቷል።

ነዋሪዎቹ ችግር የተፈጠረው ቅዳሜ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም ምሳ ሰዓት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በጀውሀ ከተማ ለጸጥታ ስራ በተሰማራ የአማራ ልዩ ሀይል ላይ ጥቃት በመክፈታቸው ነበር ብለዋል።

በጥቃቱ የጀውሀ አስተዳዳሪን እና የአማራ ልዩ ሀይል አባላትን ጨምሮ በድምሩ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉን አመልክተዋል።

ሁኔታው እሁድ ዕለት ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም ትላንት በጀውሀ፣ ሰንበቴ፣ ሸዋሮቢት ከተማ እና ቀወት ወረዳ ስር ወዳሉ ቀበሌዎች መስፋፋቱ ተገልጿል።

ግጭቱን ለመቆጣጠር ተጨማሪ የአማራ ልዩ ኃይል ከአጣዬ አቅጣጫ ወደ ጀውሀ እና ሸዋሮቢት በመጓዝ ላይ እያለ ሰንበቴ ላይ ከመንገድ ዳር ባደፈጡ ታጣቂዎች ተኩስ እንደተከፈተባቸው ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።

ይሄንን ተከትሎ ግጭቱ ከጀውሀ አልፎ ወደ ሰንበቴ እና አጣዬ ሊስፋፋ መቻሉን ተገልጿል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Attention-01-24-4

NB. እስካሁን የመንግስት አካላት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ የለም።

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በሐመር ወረዳ በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተ የዝናብ እጥረት የተነሳ ድርቅ በሰው እና በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ስር በምትገኘው ሐመር ወረዳ እንደ ሶማሌ እና እንደ ቦረና ሁሉ ለወረዳው ለአርብቶ አደሮች ጊዜው ከፍቷል ተብሏል።

በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት የአርብቶ አደሩ የኑሮ መሠረት የሆኑት የቀንድ ከብቶቹ በየጫካና ጥሻዎቹ ውስጥ በተኙበት እየሞቱ ይገኛሉ።

አሁን ላይ በሐመር ድርቁ ዕለት በዕለት የአርብቶ አደሩ መተዳደሪያ የሆኑ የቁም እንስሳትን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨረሰ ነው።

ውኃ የለም፤ ሣር የለም። አርብቶ አደሩ የእንስሳት ተዋጽዖ በመመገብ ነው የሚኖረው። ዝናብ የለም በዚህ ምክንያት ብዙ ከብቶች እየሞቱ ነው።

ሰውም በጣም በከፍተኛ ሁኔታ በረሐብ እየተሰቃየ መሆኑን ከወረዳው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በወረዳው ለተከታታይ አራት ዓመት እና በላይ በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ነው ድርቁ በከፍተኛ ኹኔታ የተፈጠረው ተብሏል።

የእንስሳት መኖ አለመኖሩ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደረ ሲሆን በየትኛውም አማራጭ ውኃ ማግኘት ወደማይቻልበት ሁኔታ ተደርሷል።

ለ4 አመታትና በላይ በቂ ዝናብ ባለመዝነቡ እንስሳቱ የሚግጡት ሳር ጠፍቷል።

ወንዞች በመድረቃቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው የቀንድ ከብቶች ለሰው ልጅ የመጠጥ ውሃ የተቆፈሩ የጉድጓድ ውሃዎችን ፖምፕ እየተደረጉ ለማጠጣት ቢሞከርም ከአቅም በላይ ሆኗል።

የከርሰምድር ውሃ እየሸሸ መሄዱና የፓምፖች ብልሽት እየተከሰተ በመሆኑ በሰው ላይ ከዚህ የከፋ ችግር ከመከሰቱ በፊት መንግስትና አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ሐመር_ወረዳ

@tikvahethiopia